Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4928
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Finally, Zerai Derres honoured in Rome.

Post by Meleket » 27 Feb 2026, 06:26

ወዳጃችን Selam/ እኤአ ጁን 14, 1938 ተርሚኒ ስቴሽን ላይ ምን እንደተፈጠረ፡ እዚህ ታች ያስነበብሽን የእንግሊዞች እይታን በቅጡ አንብበነዋል።
Selam/ wrote:
25 Feb 2026, 05:55
አቶ መለከት
ሆኖም የታይምስ ጋዜጣ የረብሻው ዕለት ያተተውን ይዘት . . .

Selam/ wrote:
26 Feb 2026, 13:07
አቶ መለከት
- ውሸት ነው የፃፍከው። . . .

- የዚያንው ዕለት . . . የለንደን ታይምስ የፃፈውን በደንብ ደጋግመህ እንድታጣጥመው ከታች ለጥፌሎሃለሁኝ።


LONDON TIMES:
“ABYSSINIAN SHOT IN ROME - An Interrupted prayer”
“Rome, June 15 “Romans hurrying to lunch today saw a negro, presumably an Abyssinian, praying before the large gilt Lion of Judah which now reposes at the foot of the monument in honour of the 500 Italians who were killed at the battle of Dogali… “A crowd gathered, and when an army officer attempted to prevent the negro from continuing his devotions, the latter produced a scimitar from his clothing and slashed at him, inflicting a serious wound. A butcher’s boy who intervened was also slashed, whereupon two soldiers fired four shots at the negro and put him out of action, but not before he had wounded the soldiers”.
መልካም ነው የለንደን ታይምስን ጽሑፍ አጣጥመንዋል። ከሱ ጋር ቀላቅለሽ ልታስጐነጭንና ልታስግችን የምትጥሪው ይህ የፈጠራ ድርሰትስ ማን ነው የጣፈው መቼስ ነው የጣፈው። እንደ ብላታው ደብዳቤ እኮ ዕለተቢስ ሆነ። በእርግጠኝነት ለመናገር “የንግስና” ፍቅር ያላቸው እንግሊዞችና ስደተኛው አጤ በመናበብ የጻፉትና ያስጻፉት መሆን አለበት። የዘርአይ መፍለቂያ ሀገሩ በስም ተጠርታ፡ አቢሲኒያም በኢትዮጵያ ተተክታ፡ ወዘተ የናንተን የፍጻሜው እይታ ከለንደን ታይምስ ጽሑፍ ጋር አስታካችሁ ዘርአያውያንን ልታስጎነጩን መሞከር እማ እንዴት ይቻላል? አይቻልም።
Selam/ wrote:
26 Feb 2026, 13:07
አቶ መለከት
- ውሸት ነው የፃፍከው። . . .

. . . .
The hero of the incident, who lived on to learn of the liberation of Ethiopia in 1941 and of the Allied occupation of Italy in 1943-4, but died in his land of captivity before the restoration of the Lion of Judah statue, was a young Eritrean, Zerai Deress, a former post-office clerk, then in his early twenties. During one of the many fascist demonstrations in Rome, his obituary in the Ethiopian Herald states, Zerai, [standing] by the Lion of Judah statue “bowed down to pray. Naturally all the spectators were distracted from the main purpose of the display and the humble Ethiopian became the pivot of their attention. A Fascist officer went over to him and asked him to get up and end his prayer. Not wishing to be disturbed Zerai continued his bowing posture. Rougher measures were applied by the officer. “In religious anger his sword was unsheathed and in a rage somewhat similar to the divine fury induced by the priestess Apollo, he fell on the would-be mockers of his country’s national symbol and killed them, uttering the words, ‘The Lion of Judah is avenged!’. Animated by this passion and burning with enthusiasm to protect the emblem of his country, he gave no quarter until he was run down by a motor cycle and arrested”.

Meleket
Member
Posts: 4928
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Finally, Zerai Derres honoured in Rome.

Post by Meleket » 27 Feb 2026, 06:58

ወዳጃችን Selam/ ታሪኩ እንዲድበሰበስስ አንሻም። እኛኮ ትረካችን ዘርአይን በቅጡ ከሚያዉቁት አብረውት ከተማሩ ጓደኞቹ አፍም የሱን ጸባይ ሆነ ባህርይ ይበልጥ ከሚያውቁ የሃገሩ ሰዎች በምናገኘው መረጃም ተመርኩዘን ነው የምናቀርበው። “የፋሽት ካቶሊክ ሰሚናር” የሚባል ነገር ኤርትራ ውስጥ አልነበረም የካቶሊክ ቤተክርስትያን ሰሚናሪ ግን ነበር አሁንም አለ። ይህ ነው ሓቁ። አስቀድመን እንደነገርንሽ የዘርአይን ልክና ሚዛን ያላወቀው የዘበኞች አለቃ፡ አፉን አላግባብ ስለከፈተ ክብረነክ ነገር ስላደረገ፡ ዘርአይ “በቃርያ ጥፊ” አጩሎታል በጐራዴ ሆነ እንጂ!

እውቀቱ ካለህ ከፋሽስት እኩል ሳይሆን ከፋሽስቶች የበለጠ ሊከፈልህም ይችላል እኮ፡ የተከፈልከውን ምን ላይ ታውለዋለህ ነው ቁምነገሩ። ወጣቱ ዘርአይ ደግሞ ስንትና ስንት ቋንቋ የሚናገር የስንት ሰው ልክ እንደነበር አስቀድመን ገልጸናል። የዘርአይን አስከሬን ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ንጉሱ አልቻሉም ሳይሆን አልተባበሩም ቢባል ምን ነዉር አለው። ቢያንስ ቢያንስ ወደ ኢትዮጵያ ሊመልሱት አይችሉም ነበሩን? ነው ወይስ ‘ኤርትራዊው ዘርአይ’፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ በፌደሬሽን ከተያያዙ በኋላ ነው ‘ኢትዮጵያዊ’ የሆነው? ሃወልቱን ታዲያ እንዴት መለሱት? ነው ወይስ ኢትዮጵያም “የእንግሊዝ ግዛት ነው የነበረችው!” እንደሚታወቀው የእንግሊዝ ሃይሎች ናቸው አሉ አዲስ አበባን ጣሊያንን እያሳደዱ ከንጉሱ በፊት ቀድመው የተቆጣጠሯት።

የነ አብርሃም ደቦጭ እና መጐስ ኣስገዶምንም ስም ለማንሳት ሞክረሻል። እነዚህ ሁለት ብርቅ ኤርትራውያን ጀግኖችንስ ማን አስገደላቸው ለምን? እንዴትስ ? መቼም ታሪክን ታሪክ ያነሳዋል። በ1942 አጤው አዲስ አበባ ላይ፡ የካቲት 19 1937 በግራዚያኒ ላይ በተካሄደው ጥቃት ምክንያት አለቁ ለሚባሉት 30,000 ዜጎች ሃወልት አስተክለው ነበር። ነገር ግን አጤ ሃይለስላሴ በወቅቱ የአብርሃን ሆነ የሞገስን ጀግንነት አልገለጹም ተብለውም ይታማሉ። ለቀጣይ 7 ዓመታት አንድም ግዜ አብርሃ ደቦጭና ሞጐስ አስገዶም አልተጠቀሱም ነበር። በኋላ ግን የኤርትራ ጉዳይ መልክ ይይዝ ዘንድ 'ኢትዮጵያዉያን' ጀግኖች ተብለው እነሱም እንደ ዘርአይ ደረስ ሲወዳደሱ አስተውለናል። ቀይባሕረኛ ጀግናን ማን ሞኝ አለ የሚጠላ!

Selam/ wrote:
27 Feb 2026, 05:25
አቶ መለከት
አንተ ለመረጥከው ትርክት ብቻ መከላከያ ስለሰጠህ ታሪኩ ተድበስቦሶ አይቀርም።፣

- ዘርዓይ ደረስ በቆዳ ቀለም ልዩነት በሚደርስበት በደል ምክንያት ከፋሽቱ የካቶሊክ ሰሚናር ሸሽቷል በኋላም የዘረኝነት በደል ስለበዛበት ወደ ሃገሩ ለመመለስ እንደሚፈልግ ገልጿል። ስለዚህ ይኸንን በመንፈሳዊ ትምህርት የበለፀገን ወጣት አንድ መናጢ ዘበኛ በቃላት ልውውጥ ደሙን አፍልቶ ወደ ጎራዴ ፍልሚያ ከተተው የሚለው ትርክት የትም ያልተፃፈ ነጭ ውሸት ነው።

- ንጉሡ በእንግሊዝ አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ ገብተው መንግስቷ ፈርሶባት በትርምስ ውስጥ ከምትገኘው ጣልያን ሃገር “ከፋሽስቶች ዕኩል” ደሞዝ እየተከፈለው ተቀጥሮ ይሰራ የነበረውን ሟች ኤርትራዊ ወደ እንግሊዝ ግዛት ማስመለስ አልቻሉም ማለት አንድ ዕውነትን የታከክ ትርክት ነው። አይ አይደለም አውቀው ለሸር ነው ጥረት ያላደረጉት የሚለውም ሌላ የካድሬዎች የለየለት ቅጥፈት ነው። ምንም ብታንከባልለው ፣ ብታለሰልሰው ወይንሞ ብታከረው ሁለቱም አቀራረብ ከእውነት ፍፁም የራቀ ክህደት ነው። እንዲያውም የነአብርሃም ደቦጭንም ታሪክ አብሮ የሚያጣምም ፣ እርስ በእርሱም በብዙ ደረጃ የሚጣረስ ከዚህ ትርክት የከፋም ሌላ የሻዕቢያ ፕሮፓጋንዳ አንብቤያለሁ - ዘርዓይ ደረስ በፍፁም ከኢትዮጵያ ስነ-ልቦና፣ ባህልና ፖለቲካ ጋር ግንኙነት የሌለውና በፋሽስቷ ጣልያን ግዞት ስር ብቻ የተቀረፀ የኤርትራ ነፃ አውጪ እንደነበረ የሚገልፅ። ታዲያ እንደዚያ ከሆነ ጃንሆይ ምን ይፍጠሩ ነው የምትሉት ሲባሉ ግን መልስ የላቸውም።

Meleket wrote:
27 Feb 2026, 03:25
ወዳጃችን Selam/ የአንዱ ጽሁፍ ለአንዱ ውሸት፡ ለአንዱ ደግሞ እውነት መሆኑ የታሪክ ሓቅ ነው። አንቺን ውሸት ጽፈሻል አንልሽም፡ ነጻ እይታሽን ግን እናከብራለን።

ዘርአይ በካቶሊክ የካፑቺን ገዳም ከሌሎች መሰል እኩዮቹ ጋር “ካህን” ለመሆን ነበር ይኮሰኮስ የነበረው፡ እንደምታውቂው ክህነት ደግሞ መንፈሳዊ ጥሪ ነው። አብረውት ከተማሩት በርካታ ልጆች መካከል፡ አንድ ወይም ሁለት ናቸው እስከመጨረሻው በክህነት ጥሪ የሚዘልቁት። ሌሎቹ ግን ካህን መሆን ካልፈለጉ፡ ትምህርታቸውን ቀስመው በፈለጉት የህይወት ጎዳና ይቀጥላሉ፡ ቀጥለውማል። ዘርአይና የጉምቱው ኤርትራዊ የነጻነት ታጋይ የጴጥሮስ ሰለሙን አባትም፡ ትምህርቱን ተከታትለው በተክሊል መቀጠል ከመረጡት መካከል ይመደባሉ። ታሪኩ ይህ ነው! እነ ዘርአይ የተማሩበት ትምህርት ቤት የፋሽስት ጣልያን ካቶሊክ ትምህርት ቤት ውስጥ ሳይሆን የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ሁለቱን መቀላቀልና ማወናበድ መልካም አይደለም፡ ፋሽስቱ ሌላ ቤተክርስትያኗ ሌላ። ፋሽስቶቹ ታሪክ ሆነው አልፈዋል፡ ቤተክርስቲያኒቱ ግን የሰው ልጆች የድኅነት (የመዳን) ታሪክ ውስጥ የበኩሏን ድርሻ እና ታሪካዊ ሃላፊነቷን እዬተወጣች አሁንም እዬተጓዘች ነው።

ዘርአይን የመሰለ ትልቅ ሙያን ያነገበ ዜጋ፡ በትልልቅ ፋሽስቶችም የተከበር ዜጋ፡ በማንም ተራ ዘበኛ መሰደቡ፤ በዘርአይ ዓይን “የቃርያ ጥፊ” ነው የቀመሰው በጐራዴ ሆነ እንጂ!

ብላታው “ነጻ ከወጣችው” ኢትዮጵያ የተስፋ ጭላንጭል ስላዩ፡ ለጣልያኖች ታደላ የነበረችውን እንግሊዝ መለማመጥ በፍጹም አልመረጡም። እንዴ ወንድማቸው እኮ “’ለይሁዳ አንበሳ’ ክብር፡ ለሰንደቃቸው ክብር፡ ለታላቋ ኢትዮጵያ ክብር ነው የተሰዋው” እኮ ነው እዬተባለ ያለው። ይህ ‘የይሁዳ አንበሳ ግን፡ የልጁን አስከሬን እንኳን ከጣልያን ኢትዮጵያ ማስገባት አልቻለም። እኛ የምናውቀው የይሁዳ አንበሳ ደግሞ ዓለምን ሁሉ ያዳነ፡ ሞትንም ድል የነሳ መሆኑን አስቀድመን ገልጸናል። ወንድማችን አልዓዛር ይህ ሃቅ አልገባው ወይም በእንግሊዞቹና በእናንተ ትርክት ተወናብዶ፡ የልጁን አስከሬን ከጣልያን ኢትዮጵያ ማስገባት የተሳነውንና እንግሊዝ ሃገር የሸሸውን “የኢትዮጵያ የይሁዳ አንበሳ” ማሞካሸት መርጧል። ምርጫውንም እናከብርለታለን፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Selam/ wrote:
26 Feb 2026, 13:07
አቶ መለከት
- ውሸት ነው የፃፍከው። ዘርዓይ በፋሽስት ጣልያን ካቶሊክ ትምህርት ቤት ነው የተማረው፣ ግን በኋላ በዘረኝነት ጫና ምክንያት ጥሎ እንደወጣ ይታወቃል። ከዚያም በኋላ ጣልያን ሃገር ውስጥ የዘረኝነት ውርጅብኝ እንዳስመረረው ለወንድሙ በደብዳቤ ገልጦለታል። ስለዚህ የአንድ ተራ ዘበኛ ስድብ ነው ዘርዓይን ጎራዴውን ያስመዘዘው ብሎ መዋሸት ፣ የማስተዋሉንና (intellect) የስነ-ልቦናውን ጥንካሬ ማኮሰስ ነው።

- ብላታው ንጉሡን አክብሮና አግዝፎ ከማንዴታቸው ውጪ እንዲረዱት መጠየቁ ለዘውዱ ያለውን ታማኝነት ያሳያል። ሆኖም በኋላ ታሪኩን ጠምዝዞ ፣ ዕርዳታ ያላገኘነው ኤርትራውያኖችን ለመለየት በተደረገ ሴራ ነው ማለቱ ነጭ ውሸት ነው። እንዲያውም የኢትዮጵያ ህዝብ ደግ ደጉን ስለሚመለከት ነው እንጂ፣ ዘርዓይ ደረስ እኮ ተኮትኩቶ ያደገውና ሲሰራ የነበረው ለፋሽስቶች ነው።

- የዚያንው ዕለት ለ The Times ከባዝ ወደ ለንደን ደውለው “ዘበኛ ስለሰደበው ሳይሆን ዙፋኑ ስለተዋረደ ነው ብላችሁ ፃፉ“ ብለው ዜናውን ዶክተር አስደረጉት ብለህ ስትዋሽ ትንሽ እንኳን አለማፈርህ በደንብ ስለማውቅህ አላስገረመኝም። የለንደን ታይምስ የፃፈውን በደንብ ደጋግመህ እንድታጣጥመው ከታች ለጥፌሎሃለሁኝ። በተጨማሪም ለውሸትህ ሃራራ ማርኪያ እንዲሆንህ በኤርትራዊው ፀሐፊ ዓላዛር ተስፋ ሚካኤል ጣፈጥ ብላ የተከሸነችውን ሪፖርት ጨምሬልሃለሁኝ።



LONDON TIMES:
“ABYSSINIAN SHOT IN ROME - An Interrupted prayer”
“Rome, June 15 “Romans hurrying to lunch today saw a negro, presumably an Abyssinian, praying before the large gilt Lion of Judah which now reposes at the foot of the monument in honour of the 500 Italians who were killed at the battle of Dogali… “A crowd gathered, and when an army officer attempted to prevent the negro from continuing his devotions, the latter produced a scimitar from his clothing and slashed at him, inflicting a serious wound. A butcher’s boy who intervened was also slashed, whereupon two soldiers fired four shots at the negro and put him out of action, but not before he had wounded the soldiers”. The hero of the incident, who lived on to learn of the liberation of Ethiopia in 1941 and of the Allied occupation of Italy in 1943-4, but died in his land of captivity before the restoration of the Lion of Judah statue, was a young Eritrean, Zerai Deress, a former post-office clerk, then in his early twenties. During one of the many fascist demonstrations in Rome, his obituary in the Ethiopian Herald states

Selam/
Senior Member
Posts: 17268
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Finally, Zerai Derres honoured in Rome.

Post by Selam/ » 27 Feb 2026, 09:24

እንዲያው እኝህ ንጉሥ እንዴት ብልሃተኛና ኃይለኛ ነበሩ እባክህ። በዘርዓይ ዙሪያ የሚፈጠረው ዜና ፣ በስልጣናቸው ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተፅዕኖ ፣ ልጁ መኖሩን እንኳን ሳያውቁት ቀድሞ ተገልጦላቸው ነበር።
የታይምስ ጋዜጣን በጉቦ ደልለው “የኤርትራውን የ neger ታሪክ ወደ ዙፋናዊ የኢትዮጵያ የ neger ታሪክ” ባያስለውጡት ኖሮ ንግሥናቸውን ያጡት ነበር።

ወንድሙ ብላታ ተስፋፅዮን የፃፈው ደብዳቤም ከታይምስ ጋዜጣ ይዘት ጋር ምንም ልዩነት የሌለው ፣ ለእሱም ጉቦ ሰጥተውት ነው ማለት ነው። :lol: እርጥባንና ጉቦ የለመደ ሰው ደግሞ እንደ ስጦታው ብዛትና እንደ አየሩ ጠባይ ስለሚቀያየር፣ ከርሞ ታሪኩን ለናይ ናይፅነት ኤርትራ ብሎ ቢያንሻፍፈውና ቢቀያይረው ምን ይደንቃል።





[/quote]

Meleket
Member
Posts: 4928
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Finally, Zerai Derres honoured in Rome.

Post by Meleket » 27 Feb 2026, 11:12

ወዳጃችን Selam/ ንጉሥ ኃይለሥላሴማ በጣም ብልህ እንደነበሩ ግልጽ ነው። የኢትዮጵያ የሥልጣን ቁንጮ ላይ እንዴት ቁጢጥ ለማለት እንደበቁ እናውቃለን። ብልህ ባይሆኑ ኖሮ ይህ የሚቻል ባልሆነ ነበር። መቼም በሌላ በኩልም ካገኙት ትምህርት ጋር የነዚህ የካቶሊኮች ትምህርት ለንጉሱ ብልህነት አስተዋጽኦ እንደነበረው ግልጽ ነው። ሕይወታቸውን ሰውተው ከሞትም ያዳኗቸው እነ አባ ሳሙኤል አይደሉምን? ራሳቸው በቃላቸው የሰጡት ምስክርነት “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ” ብለው በሰየሙት መጸሃፋቸው ገጽ ፬ ላይ ቁልጭ አድርገው ጽፈውታል።
"ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ” በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠንገሥት ዘኢትዮጵያ ፩ኛ መጸሓፍ ገጽ ፬

አባቴ በቶሎ የፈረንሳይ ቋንቋ እንዳውቅላቸው ቸኩለው ነበርና ዶክተር ቢታልያ በቀን አንዳንድ ሰዓት ብቻ የሚያስተምረን ወደ ፍጻሜ እንደማያደርሰን ስለ ተረዱት በሐረር ከተማ ውስጥ ካሉት ከኣባ ኣንድሪያስ ጋር ተነጋግረው በዚያው በሚሲዮናቸው ቤት እየተማረ ያደገውን አባ ሳሙኤል የሚባለውን ኢትዮጵያዊ አመጡልንና እርሱ በትጋትና በጥንቃቄ ያስተምረን ጀመር። ስለሆነም ከዶክተር ቢታልያ በቀን አንዳንድ ሰዓት መማራችንን አልተውንም ነበር።

አባ ሳሙኤል የሚባለው አስተማሪያችን የአለቃ ወልደ ካህን ልጅ ነው። ወልደ ካህን ማለት የኢጣልያ ሚሲዮን አባ ማስያስ ወደ ሸዋ በመጡ ጊዜ ወደ ካቶሊክ ሃይማኖት የገቡ ናቸው። ልጃቸው አባ ሳሙኤልም በካቶሊክ ሚሲዮን ቤት ገብቶ የተማረበት ምክንያት ስለዚህ ነው። አባ ሳሙኤል ትልቅ ዕውቀት ያለው፡ ለመማርም ለማስተማርም የሚተጋ፡ በደግነትና በትሕትና ከማንም ሰው ዕውቀትን እንደ ንብ የሚቀሥም፡ በፍቅረ እግዚአብሄርና በፍቅረ ቢጽ የተጠመደ፡ የነፍሱን እንጂ የሥጋውን ጥቅም ለማግኘት የማይጥር ደግ ሰው ነበር። ይህንን ማለቴ ዐሥር ዓመት ያህል አብረን በመኖራችን በጣም ስለ ዐወቅሁት ነው

AI Overview
Emperor Haile Selassie I was educated in Harar by French missionaries, specifically from the Lazarist (Vincentian) Order, who were hired by his father, Ras Makonnen. In addition to French tutors, he was instructed by Ethiopian Capuchin friar Abba Samuel Wolde Kahin and Dr. Vitalien, a surgeon from Guadeloupe, which contributed to his early, cosmopolitan education.

አጤ ኃይለሥላሴ እንደ ዘርአይ የካፑቺን ማኅበር አባል ለነበሩት ኢትዮጵያዊው አባ ሳሙኤል ምስክርነታቸው እንደለገሱት ሁሉ ለዘርአይ ደረስም ስለጠባዩ ስነምግባሩና ባህርዩ ሊገልጹ የሚችሉ ኤርትራዉያን አብሮ አደጎቹ አሉ ነው ያልነው። የኛ መረጃ የነዚህ እማኞችን ምስክርነትም ያካትታል። ከዚህ በመለስ፡ ዘርአይን በተመለከተ፡ “ሃውልት ያክል ከጣልያን ኢትዮጵያ ሲያስመልሱ፡ የዘርአይን አስከሬን ወደ ትውልድ ቀዬው ለመመለስ በወንድሙ በብላታ ተስፋጽዮን አማካኝነት የተደረገ ጥረትን ግን በሞራል ሆነ በገንዘብ ድጋፍ ሲያደርጉ አልታዩም።” ማለት ንጉሱን መክሰስ አይደለም። ይህም ሆኖ “ዘርአይ ለንጉሱ ክብር፡ ለባንዴራቸው ክብር፡ ለይሁዳ አንበሳ ክብር ነው የተሰዋው!” ተብሎ ሲተረክ ስንሰማ ትንሽ ለሚመረምርና ለሚመራመር ሰው ስሜትን አይሰጥም ነው ያልነው።

ብላታው በወቅቱ ለጣልያኖች ያደሉ ከነበሩት እንግሊዞች ይልቅ፡ የነጻነት ተስፋ ያዩ የነበሩት በ”ነጻይቱ አዲሲቱ ኢትዮጵያ” ሆኖ ሊሆን ይችላል። ዘርአይም የተሰዋው ለጥቁሮች ክብር ሆኖ ሳለ፡ እንግሊዞቹን ማለትም ነጮቹን መማጠን ምንም ፋይዳ እንደሌለው ብላታው ገብቷቸው ነበር ማለት ይቻላል። ቢያንስ ቢያንስ እንደኔ ጥቁር የሆነ ጐረቤቴ ንጉሠነገሥት ሊሰማኝ ይችል ይሆናል ብለው ነበር ያሰቡት ለማለት ይቻላል።

ከዚህ ወዲያ ውይይቱን መለጠጥና ወደ ሌላ አቅጣጫ ማምራቱ ፋይዳው አልታዬንም።

ዘርአይ ሆነ አጤው የየበኩላቸውን ታሪክ ሰርተው አልፈዋል። አምላኽ በቀኙ ያቁማቸው። የኛ እዚህ ነገሮችን ከተገቢው በላይ ማመንዥኽ ምንም ፋይዳ ስሌለው፡ ሌላ ይበልጥ ልንተጋበት ዬሚገባ አንገብጋቢ ቁምነገርም ስለሚኖረን፡ እላይ የተገለጹት የጨዋ ውይይታችንን ለአንባቢ እና ታሪክ አፍቃሪ ዜጎቻችን ግንዛቤና ምርመራ ትተንላቸዋል። ለወዳጃችን Selam/ደግሞ ለተወሰኑ ጊዜያት ጠፍተሽ ቆይተሽ በመመለስ ይህን የመሰለ ውይይት ስላጋራሽን መልካም መልካሙን ሁሉ ተመኝተንልሻል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።



Selam/
Senior Member
Posts: 17268
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Finally, Zerai Derres honoured in Rome.

Post by Selam/ » 27 Feb 2026, 12:11

አቶ መለከት
“ዘርዓይ ለንጉሡ ክብር፡ ለሰንደቅ ዓላማችን ክብር፡ ለይሁዳ አንበሣ ክብር ነው የተሰዋው” ብለው የተረኩት እኮ በብልሁ ንጉሥ መዳፍ ስር የወደቁት እነ The Times እና የንጉሡ ክብር የከበባቸው እነ አቶ ተስፋፅዬን ናቸው። ማስተባበያው ካለህ ደግሞ ጋዜጣውን “ጉቦ በልታችኋል” ብለህ ከሰህ ካሳ እንዲከፍሉህ መጠየቅና ፅሁፉን እንዲያስተባብሉ ማድረግ ነው። አለበለዚያ ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ እንደሚለው በማያልቅ የፕሮፓጋንዳ አዙሪት መጦዝ ነው።

ተስፋፅዬን ደረስ በፊት የፃፈውን ደብዳቤ እንዳላየ አልፈህ፣ በኋላ በደም ፍላት ያተታቸውን ቅጅዎች ብቻ አንብብልኝ ከሆነ የምትለኝ ፣ እኔ ሰላም ግራውንም ቀኙንም የማመዛዝን ሰው እንጂ ተራ ካድሬ አይደለሁም።







Meleket
Member
Posts: 4928
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Finally, Zerai Derres honoured in Rome.

Post by Meleket » 28 Feb 2026, 05:29

ወዳጃችን Selam/የግል አመለካከትሽን እናከብርልሻለን። ንጉሱ ብልህ ነበሩ፡ መጨረሻቸው ግድም ግን ሥልጣንን የሙጥኝ ብለው “ንግሥናቸውን” ለማስቀጠል ሳይበቁ በማለፋቸው፡ ብልህነታቸው በእርጅናቸው እንደተሸነፈ አጢነናል።

ከዚያ በተቀረ የብላታዉን ሁለተኛ ገጽ ደብዳቤ ውይይቱን አገባድደናል ባልንበት ማግሥት በማምጣሽ አሁንም ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። በርቺ ተራ ካድሬ ባለመሆንሽ እንዲሁም የግራዉንም የቀኙንም የምታመዛዝኝ ሰው በመሆንሽ በእርግጥ ልትኮሪ ይገባሻል። ወላጆችሽ መምህራኖችሽ እንዲሁም ያሳደገሽ ማኅበረሰብም አንቺን ዬመሰለ የኅብረተሰብ ቅመም በማፍራቱ ሊመሰገን ይገባዋል።

ዘርአይን ንጉሡን እንዲሁም ብላታዉን፡ እዉነተኛው የይሁዳ አንበሳ፡ የእምዬ ድንግል ማርያም ልጅ፡ መድኃኔዓለም በቀኙ ይቀበላቸው በማለት ለግዜው ተሰናብተንሻል። ቸር ሰንብች።

Selam/
Senior Member
Posts: 17268
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Finally, Zerai Derres honoured in Rome.

Post by Selam/ » 28 Feb 2026, 07:47

አቶ መለከት
መቼም የሰው ልጆች ስንባል የራሳችን ጉድፍ ምንም አይታየንም።

የውይይቱን ዋና ርዕስ ለጥጠህ ንጉሡ በስተርጅናቸው ዘመን ስለፈፀሙት ስህተት ካነሳህ አይቀር፣ ልክ እንደርሳቸው ንግስናውን ጥግ ለማድረስ ወደ መጨረሻው አስርት ዓመታት ውስጥ እየተንሸራተተ ስላለውና አሁን ንጉሡ ሲሞቱ ከነበራቸው ዕድሜ ጋር ተቀራራቢ ስለሆነው የእናንተው ጉምቱ መሪ ፍፃሜ ምን ሊሆን እንደሚችል አንድ አንድ ነገር ጀባ በለና።

መቼም ዘርዓይ ከሞተበት ወቅት ጀምሮ የኖረ ስለሆነ፣ ከንጉሡ ስህተቶች ብዙ ሳይማር አይቀርም ብዬ እገምታለሁ።



Post Reply