በቅርቡ ፕሮፌሰር ቃሎ የሚል ስም ወጣልኝ።
ማስረጃዉ እዚህ ኣለ፥
ክርስትናን እያስፋፉ ሬይነሳንስ ማለት የዕዉቀት ማነስ ወይም የኣዕምሮ ጉድለት ወይም ቅጥረኛ ሆኖ መዋረድ ነዉ።
ከዓመታት በፊት እዚሁ መድረክ ላይ ሜጋ ቱማ የሚል ስም ወጥቶልኝ ለዛን ያህል በቂ ኣይዴለሁም ብዬ ሳላስመዘግብ ኣለፍኩት።
ብዙ ዓመታት ኣልፈዉ የወጣልኝ ሜጋ ለሃገሬ ሲሰጥ ባስመዘግብ ኖሮ ለስሙ ትንሽ ይከፈለኝ ማለት እችል ነበር ኣልኩኝ። ለሃገር የሆነ ስም ኣይጸጽትም።
ከኣሁን በፊት ፕሮፌሰር ቃሎ የተባለ ኣልሰማሁም። ስለዚህ የመጀመርያዉ ፕሮፌሰር ቃሎ የተባለ ብዬ ኣለማስመዝገብ ለወደፊት እንዳይጸጽተኝ ኣሰብኩ።
ይህን ስም ያገኘሁኝ ጽዮን ተራራ ላይ ቆሜ ሳይሆን ኤልያስ ክፍሌ ዩኒቨርዚቲ ዉስጥ በፈቃደኝነት ከአስራ ስምንት ዓመታት በላይ በማስተማር ነዉ።
ፕሮፌሰር ቃሉ መባል ዕቅዴ ዉስጥ ኣልነበረም። በልጅነቴ ነጭ ሽንኩርት እንደማልወድ የሰሙ ቤተ ዘመድ ቃሉ ተኡፊ ብለዉ ቢቀልዱ ስላልገበኝ ዝም ብዬ ማለፍ እንጂ ኣልተከታሉኩትም።
ፕሮፌሰር ቃሎ ማለት ቃሉ የማይቀለበሰዉ ቃሉ የተባለዉ ኣይዴለም።
ቀጥሎ የሚመጡ ፕሮፌሰር ቃሎዎች የተሻለ ማስተማር እንደሚችሉ እገምታለሁ።
ስለዚህ ፕሮፌሰር ቃሎን እና እንደ ፕሮፌሰር ቃሉ፣ ፕሮፌሰር ቃልቻ፣ ብሮፌሰር ቃሎ የመሳሰሉት ስሞች ዕዉቅና የተሰጠዉ የመጀመርያዉ መሆኔን እንዲመዘገብልኝ እፈልጋለሁ።
ይህን ስም አፍረን ቃሎ በመባል የታወቁት ይገባናል የሚሉ ከሆነ ማመልከቻቸዉን በጥሞና ኣንብቤ ኣሳማኝ ከሆነ ፕሮፌሰር ቃሉ የሚገባዉ ለእነሱ ነዉ ለማለት ዝግጁ ነኝ።
ማመልከቻዉን በሚከተሉት በኩል መላክ ይቻላል።
1) የጥንት ቃሉ የተባለዉ ታላቁ ፈረዖ አክናተን ወይም ነብይ ሙሳ የተባለዉ ቃላት ተሸካሚ እና ጠባቂ ከተባሉት ዉስጥ ታዋቂዉ እና በቅርባቸዉ ባለዉ ቁሉቢ ገብርኤል ታቦት በኩል
2) ሰብን ኩን ሰበ ጋሪ ዻ፣ ዱአኒፍስ ኦማ ምት ባለዉ በኩል
3) ኣጠፈ ተብሎ የተቀጣ ተማሪ ማጥፋቱ ሳይረጋገጥ እንዴት ይቀጠል ክርክር ተደርጎ የክርክሩን መሪ ኣብሮ የቀጣ ዩኒቨርዚቲ የወቅቱ አመራር በኩል
4) አፍረን ቃሎ ቢጠና የጥንት ቅርሶች ኣሉት ባለዉ የዋስነት ባለዉለታ የገለምሶ ሰዉ በኩል
5) አከ ዼርነ ኬፍ ሚለ ኬ ጀለ ከን ጂሩ ከን አርግቱ ፈካተ በተባለዉ በኩል
6) ኩንስ ሁበ ቀበ፣ ሱንስ ሁበ ቀበ ጄኔ ባለዉ በኩል
ይህ ማስመዝገብ ያሰብኩኝ ስም የሚጸና ከሆነ እና ይህን ፋና ለመከተል ምክር ወይም ርኮመንዴሽን የሚፈልጉ ካሉ የሚከተሉትን ከማንበብ መጀመር ይቻላል።
1) የፕሮፌሰር ዶናልድ ኤን ለቪን ግሬት ኢትዮጵያ የታሪክ መጽሓፍ ዉስጥ የጥንት ግዜ ኢትዮጵያዊያን በእግዝኣብሔር ፈቃድ የተረገሙ የሚል የሃይማኖት ሰበካ በሰሙ ግዜ የቀድሞ ማንነታቸዉን ላለመተዉ እና የተባረኩ የተባሉትን ለመሆን መካከል ግራ በመጋባት ያዘገመ የማንነት ትግል ዉስጥ ገቡ የሚለዉን በጥሞና ማንበብ እና ማስተዋል።
ፕሮፌሰር ቃሉ ወይም ቃልቻ ወይም ቃሎ ለመሆን ይህን የጥንት ግዜ ሰበካ በጥሞና ካነበቡ እና ካስተዋሉ በኋላ እርግማን የተባለዉ እንዲነሳ ጪሳ ጭስ ማጨስ ያስፈልጋል። ይህ የጥንት ግዜ እርግማን የተባለ እንዲነሳ ቃሉ ለመሆን ቀርቶ ጪሳ ጭስ የማያጨስ የሰዉ ልጅ ማን ኣለ?
2) በሁለተኛዉ የዐለም ጦርነት ዋዜማ ኣዉሮፓ ዉስጥ ይኖር የነበረ ጅዉሽ የተባለ ስግመንድ ፍሪዩድ የተጻፈ ሞሰስ ኤንደ ሞኖቴይዝም የተባለ መጽሓፍ
3) እንግሊዝ ሃገር የኖረ ግብጣዊ አህመድ ኦስማን የተባለ የስግመንድ ፍሪዩድን መጽሃፍ ተከትሎ የጻፈዉ ሞሰስ ኤንድ አክናተን የተባለ መጽሓፍ
4) ከሃያ ዓመታት ገደማ በፊት መነ ቡና የተባለ ሌላ የዉይይት መድረክ ዉስጥ ከሃያ ዓመታት ገደማ በኋላ ፕሮፌሰር ቃሎ የተባለዉ የጀመረዉ ዋቀ ቶክቻ ኤንድ ሞኖቴይዝም ረጅም የዉይይት ርዕስ
5) የቦረና ሰዉ ደበሳ ጉዮ ነምን ህን ሶበ፣ ኡርጂን ህን ሶቡ ማለት
6) የታወቀዉ የኢትዮጵያ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ከሃምሳ ዓመታት በፊት ድሬ ሊበን፣ ቦረና፣ ጫርኩት ያለዉን
እደ እዶ ምድር
ተነባቢ የአስር ምስጥር
ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ
ለካ ኣንተ ነህ!
እነዚህን ሁሉ በጥልቀት ያጠና እና በጥሞና ያዳመጠ የወደፊት ፕሮፌሰር ቃሉ ወይም ቃልቻ ወይም ቃሎ መሆን ተስፋ ኣለዉ። ለተመኛችሁ ሁሉ መልካም ጥናት እንድሆንላችሁ እመኛለሁ።