እኔ መልዕክቱን የጻፍኩኝ ኣይዴለሁም። ገልጬ እያነበብኩ የምጠይቅ ነኝ።
የአስርቱ ትዕዛዛት አባት የጥንት የጠዋቱ ቀዳማዊ ነብይ የተባለዉ እስራኤላዊ ሳይሆን የጥንት ኢትዮጵያ ታላቅ ፈረዖ ነበረ ተብሎ በኢትዮጵያ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ከተጻፈ ሃምሳ ዓመታት ኣልፈዋል።
የሎሬቱ ጥናት መኖሩን እኔ ሳላዉቅ የታሪክ መዛግብቶችን ኣንብቤ ተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ መድረሴን ከጻፍኩኝ ሃያ ዓመታት ገደማ ሆኗል።
ያ የጥንት ነብይ በቅርብ ዘመናት ቃልቻ ወይም ቃሉ ከሚባሉት ጋር ተመስሏል።
የጥንት የጠዋቱ ነብይ ወይም ፕሮፌት የተባለዉ ሆነ የቅርብ ዘመናት ቃልቻ ወይም ቃሉ ስለ መለኮት ነገር እናዉቃለን ብለዋል።
ይህ ማለት የአስርቱ ትዕዛዛት ጠባቂ የኢትዮጵያ ታቦት ከጥንት ከጠዋቱ እስከዚህ ዘመን ድረስ ያልተቋረጠ መለኮታዊ መስመር ላይ ነበረ ማለት ይቻላል። ኣይዴለም?
ከተቻለ ታቦትን ወይም አስርቱ ትዕዛዛትን ብቻ መሪህ ወይም ሬፈረንስ ኣድርገን በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተከሰቱትን መለኮታዊ ወይም መለኮታዊ መሳይ ነገሮችን እንመርምር።
ኤርትራዊያን ከኢትዮጵያዊያን ለየት ተደርገዉ ተስለዉ የሚንበረከኩት ሁለት ግዜ ብቻ ነዉ ኣሉን። ሲተኩሱ እና ሲጸልዩ ብቻ ነዉ ተባልን።
መፈክሩን በቅርብ ግዜ እንደገና ኣንብቤዉ ኣንድ ኣጭር ጥያቄን ኣስጠየቀኝ።
ሲጸልዩ ምን ብለዉ እንደሚጸልዩ ቃል በቃል ለማወቅ ፈለኩኝ። ኣሁን ድረስ መልስ የሚሰጥ ኤርትራዊ ነኝ የሚል ስዉ ኣላጋጠመኝም።
ሲጸልዩ ከእግዝኣብሔር ጋር ማገናኛቸዉ መንገዱ በኢትዮጵያ ኣምላክ በኩል ነዉ ከተባለ ሲተኩሱ በምን ላይ እንደነበረ እና ሲጸልዩ ለምን እንደነበረ ላስተዋለ ሰዉ እርስ በእርስ የሚጋጩ ይሆናል።
ስለዚህ ዘመን መለኮታዊ አሰራር ይህ ኣንድ ምልክት ነዉ። እኔ እንደገባኝ ከሆነ ማለት ነዉ።
በአደዋ ማግስት የምዕራባዊያን ምሽነሪዎች ምዕራብ ኢትዮጵያ ገብተዉ ኣርሶ እና ኣርብቶ ኣደሮችን የፕሮቴስታንት ክርስትና ያስጀመሩት ስር ካደጉት ዉስጥ ኣንዱ የኢትዮጵያን ታቦት ጣዖት ነዉ የሚል ሆኗል።
ይህ ሰዉ ዕድሜ ልኩን ለኦሮሞ ሕዝብ የታገልኩኝ ነኝ ባይ ነዉ ቢባል ስህተት ኣይመስለኝም።
ይህ ሰዉ ዕድሜ ልኩን ታገልኩለት ለሚለዉ ሕዝብ ቃሉ ባህላዊ መንፈሳዊ መሪዉ ነዉ።
ይህ ማለት የጥንት ኢትዮጵያ ቃሉ የተባለን ቃላት ጠባቂን ጣዖት ነዉ ማለት እርስ በእርስ የሚጋጩ ይሆናል።
ስለዚህ ዘመን መለኮታዊ አሰራር ይህ ሌላ ምልክት ነዉ። እኔ እንደገባኝ ከሆነ ማለት ነዉ።
ጉራግኛ ተናጋሪዉ ኢትዮጵያዊም ስለ ምዕራባዊያን ምሽነሪዎች የፕሮቴስታንት ትምህርት ሰምቶ ታቦት ጣዖት ነዉ ካለ ጋር የዋለ እንደሆነ ኣብሮት የዋለዉ መለኮታዊ ብይን ካገኘ ጉራግኛ ተናጋሪዉ ኢትዮጵያዊም ኣብሮ መለኮታዊ ብይን ኣገኘ ማለት ይሆናል።
ስለዚህ ዘመን መለኮታዊ አሰራር ይህም ሌላ ምልክት ነዉ። እኔ እንደገባኝ ከሆነ ማለት ነዉ።
ለኢትዮጵያ ዘብ የቆምኩኝ ታቦትን የምሳለም ነዉ ያለ ኢትዮጵያዊ ሌላ ኢትዮጵያዊ ስለ ታሪክ ዕዉነት እና ዘበት ለይቶ የምትሳለመዉ ታቦት አስርቱ ትዕዛዛት አባት የጥንት የጠዋቱ የኢትዮጵያ ነብይ እንጂ እስራኤላዊ ነብይ ኣልነበረም ሲባል ለኢትዮጵያ ዘብ የቆምኩኝ ነዉ ማለቱ እና የጥንት ኢትዮጵያዊ ነብይ እስራኤላዊ ነብይ ነበር ማለት እርስ በእርስ የሚጋጩ ናቸዉ።
ስለዚህ ዘመን መለኮታዊ አሰራር ይህም ሌላ ምልክት ነዉ። እኔ እንደገባኝ ከሆነ ማለት ነዉ።
በአደዋ ዋዜማ ዉዳሴ የሚለዉ ቃልቻ እና ዌድሴ የሚለዉ ቃሉ ሃገርን ከቃልቻ እስከ ቃሉ ኣብረዉ ኣደራጅተዉ አደዋ ከዋሉ መቶ ዓመታት በኋላ ታቦት ጣዖት ነዉ ከሚለዉ ጋር ከዋሉ የጥንት የጠዋቱን የቃሉ አስርቱ ትዕዛዛትን በኣንድ መቶ ዓመታት መርሳት ይሆናል።
በተጨማሪም በቀላሉ መረሳት የማይቻለዉ ቃሉ ባልተደራጀ ሁኔታ ዌድሴ ሲል ቃልቻ ኣደራጅቶ ዉዳሴ ሲል ኖሮ ድርጅቱን የሚመራ ከሆነ የማደራጀት እና የማደራጀት ማነስ እርስ በእርስ ግጭት ይሆናል።
ስለዚህ ዘመን መለኮታዊ አሰራር ይህም ሌላ ምልክት ነዉ። እኔ እንደገባኝ ከሆነ ማለት ነዉ።
የባህር ማዶ ነብይ እያለ ቀዳማዊ የባህር ማዶ ነብይ ሙሳ የሚለዉ ኢትዮጵያዊም የባህር ማዶ ነብይ ሙሳ የተባልከዉ የጥንት የጠዋቱ የኢትዮጵያ ነብይ ነበረ የሚል ዕዉነትን ሲሰማ የባህር ማዶ ነብዮችን ፍለጋዉ እርስ በእርስ የሚጋጭ ይሆናል።
ይህን ዕዉነት እጅግ የምያጎላዉ ከብዙ ዓመታት በፊት ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ የመጀመርያዉ የዋቄፈና ስብሰባ የተባለ ላይ ቀመር ዩሱፍ የጠየቀዉ ጥልቅ ጥያቄ ነዉ። አረብ ሃገሮችን ተዘዋዉሮ የጎበኘ መሆኑን እና እራሱ ሲከተል የኖረዉ ነብይ በምያስተምረዉ ምክንያት ሀራሙ የሚባሉ ልጆችን መንገድ ላይ ተመልክቻለሁ ብሎ ነበር። ጥያቄዉን ቃል በቃል ባላስታዉስም የእኛ ሕዝብ ጥንት ግዜ ዕዉቀቱን ኣግኝቶ ከባህሉ ዉጪ ማድረግ የቻለዉ እንዴት ነዉ የሚል ነበር።
መልሱን ለማግኘት ስለ የጥንት የጠዋቱ የኢትዮጵያ ነብይ፣ ታላቅ ፈረዖ የነበረን፣ ታሪክ ዕዉነት በማወቅ ማግኘት ይቻል ይሆናል። ምናልባት ከሙዚቀኛዉ ትምህርት እና የኣዕምሮ ችሎታ በላይ ከሆነ ምሁራን ብሎ የምያዉቃቸዉን ማማከር ይችል ይሆናል።
ስለዚህ ዘመን መለኮታዊ አሰራር ይህም ሌላ ምልክት ነዉ። እኔ እንደገባኝ ከሆነ ማለት ነዉ።
እዚህ ሁሉ ዉስጥ የጋራ የሆነዉ ቀዳማዊዉ የጥንት የጠዋቱ የኢትዮጵያ ነብይ ወይም ፕሮፌት የተባላዉ ታላቁ ፈረዖ አክናተን ነዉ።
በእኔ አስተሳሰብ ከሁሉም የባሰ የሚገርመዉ ይህን አስተያየት የጻፍኩኝ የኢትዮጵያ ክርስትያኖች ነን የሚሉት ታቦት ጣዖት ነዉ ሲሉ እኔ እ አ አ ከ1992 ጀምሮ የሃይማኖት ቤት ያልሄድኩ ሰዉ አስርቱ ትዕዛዛት የጥንት ኢትዮጵያ ነብይ፣ ታላቁ ፈረዖ አክናተን፣ እንደነበረ ለማስረዳት መጣር ነዉ።
Re: የኢትዮጵያ ኣምላክ መለኮታዊ አሰራር ግልጽ ኣልሆነም?
የአስርቱ ትዕዛዛት ጠባቂ የኢትዮጵያ ታቦት ከጥንት ከጠዋቱ እስከዚህ ዘመን ድረስ ያልተቋረጠ መለኮታዊ መስመር ላይ የነበረ ከሆነ ዘላለማዊነቱንም ለማስመስከር መስመር ላይ ነዉ ማለት ይቻላል።
ስለዚህ ኢትዮጵያ ዉስጥ አስርቱ ትዕዛዛትን ተደራጅቶ ማክበር መቼ እንደተጀመረ ይታወቃል?
ስለዚህ ኢትዮጵያ ዉስጥ አስርቱ ትዕዛዛትን ተደራጅቶ ማክበር መቼ እንደተጀመረ ይታወቃል?