Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7160
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

እጅግ ብዙሃን ኢትዮጵያዊያን የማያዉቁት ጥንታዊ እና ቀዳማዊ የኢትዮጵያ ነብይ

Post by Naga Tuma » 03 Feb 2026, 22:29

ከቦረና እስከ ሀማሴን፣ ከሐረርጌ እስከ ወለጋ ቃሉ ወይም ቃልቻ ማለትን እጅግ ብዙሃን ኢትዮጵያዊያን ያዉቃሉ።

የክርስትና ሃይማኖት ሆነ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ፕሮፌት ሙሴ ተባለ ፕሮፌት ሙሳ ተባለ ሁሉም ያዉቃሉ።

የፕሮፌት ሙሴ አስርቱ ትዕዛዛትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተሸካሚ እና ጠባቂ ነዉ።

እጅግ ብዙሃን ኢትዮጵያዊያን የማያዉቁት ከስደት በኋላ ፕሮፌት ሙሴ የተባለዉ ከስደት በፊት ቃልቻ ወይም ቃሉ የተባለ ጥንታዊ እና ቀዳማዊ ነብይ ታላቅ ፈረዖ አክናተን መሆኑን ነዉ።

ይህ ዕዉቀት ኣዲስ ኪዳን ዉስጥ የሚገኝ ኣይመስለኝም።

ከጥልቅ ምርምር በኋላ የሚደረስበት ነዉ። መለኮታዊ ስምርት ለዚህ ዕዉቀት የምያበቃ መሆኑን ኣላዉቅም።

ነብይ ተባለ፣ ኣዳኝ ተባለ፣ መሳያ ተባለ ስለ መለኮታዊ ግላፄ ነዉ። ይህ ግላፄ ከሰዉ ልጅ የመተንተን ዐቅም በላይ ነዉ።

እንደዚህ ሲገለጽ ግን ቃልቻ ወይም ቃሉ ወይም ነብይ ማለትን የሰማ ኣለማመን ቀላል ኣይሆንም።