ባዶ የሆነ ነገርን ማደስ ኣይቻልም።
ስለዚህ ህዳሴ ማለት የሚቻለዉ መታደስ የሚችል ቁስ ወይም ታሪክ ሲኖር ነዉ።
ሬይነሳንስ ማለት በፈረንሳይኛ ቋንቋ ዳግም ልደት ማለት ነዉ።
ከክርስትና መጀመር በፊት የነበረን የጥንት ግሪክ ስልጣኔን የደረሱበት ኣዉሮፓዊያን ዳግም ተወለደ ያሉት ነዉ።
ከክርስትና መጀመር በፊት የነበረ የጥንት ኢትዮጵያ ስልጣኔ በፈረዖዎች ዘመን የነበረ ስልጣኔ ነዉ።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ዳግም ልደት ወይም ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ከተባለ የፈረዖዎች ዘመን የነበረ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ዳግም መወለድ ማለት ነዉ።
ይህ ትምህርት ያልገባቸዉ ሰዎች፣ ምሁራን ነን የሚሉትን ጨምሮ፣ ህዳሴ የሚሉት ነዉ።
ህዳሴ ለማለት በወሬ ብቻ ሳይሆን የሚጨበጥ የታሪክ ቅርስን ማወቅ ግዴታ ነዉ።
ኣንድ የሚጨበጥ የታሪክ ቅርስ የተገኘዉ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት በኩል ነዉ።
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ደርሶበት ጨብጦ ለካ ኣንተ ነህ! ያለዉ አስርቱ ትዕዛዛት የጥንት ኢትዮጵያ ታላቅ ፈረዖ የነበረዉ አክናተን መሆኑን የሎሬቱ ቃላት ያመለክታሉ።
እኔም የሎሬቱን ጥናት ሳላዉቅ ኣንብቤ ከጨበጥኩዋቸዉ ዉስጥ ዋቀ ቶክቸ ብዬ የዛሬ ሃያ ዓመታት ገደማ ዉይይት የጀመርኩኝ ለዚሁ ነበር።
ሎሬቱ የጥንት ግዜ ቃሉ ያለዉ እና እኔ ዋቀ ቶክቸ ያልኩኝ ህዳሴ ወይም ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ለማለት ያስችላሉ።
ይህ ማለት በኣጭሩ ታቦት የጥንት ኢትዮጵያ ታላቅ ፈረዖ እንደ ቃልቻ ወይም ቃሉ ቃላት ተሸካሚ እና ጠባቂ ለህዳሴ ወይም ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የሚጨበጥ ታሪክ የያዘ ነዉ ማለት ነዉ።
ስለዚህ በኣንድ አፍ ግራንድ ሬይነሳንስ ከማለት እና ታቦት ጣዖት ነዉ ከማለት የበለጠ ኣንድም መሃይምነት ኣልያም የዕዉቀት መቃወስ ኣለ?
ሃገር ሰዉ ተምሮ ምሁር ይሁን ብላ ስትለፋ የዚህ ያህል የዕዉቀት መቃወስ ምንጭ ምንድነዉ?