Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7160
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ገዳ ስለ ቦረና ማህበረሰብ ምድራዊ ስርዓት የምያስተምር ከሆነ ቃልቸ ወይም ቃሉ ስለ መለኮታዊ ነገር የምያስተምረዉ ምንድነዉ?

Post by Naga Tuma » 11 Jan 2026, 19:46

ገዳ ስለ ኣንድ ማህበረሰብ ምድራዊ መተዳደርያ ስርዓት ነዉ።

በየስምንት ዓመታት ስልጣን ከኣንድ አባ ገዳ ወደሚቀጥለዉ አባ ገዳ በሰላማዊ መንገድ እንዲተላለፍ ማድረግ መቻሉ ዋነኛ ስኬቱ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

ቃልቻ ወይም ቃሉ ስለ መለኮታዊ ነገር የምያስተምረዉ ዋነኛ ነገር ምንድነዉ?

በጥንት ዘመን ሆነ በዚህ ዘመን ቃልቻ ወይም ቃሉ የምያስተምረዉ ልዩነት ሊኖራቸዉ ይችላል?

በእኔ አስተሳሰብ ተመሳሳይነት ይኖራቸዋል። ምክንያቱም ስለ መለኮታዊ ነገር ግንዛቤ ዘመን በቀላሉ የማይሽረዉ ስለ ሆነ ነዉ።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ ያለዉ ከስደት በፊት ታላቅ ፈረዖ የነበረዉ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ፕሮፌት የሆነዉ ሙሴ መሆኑ ከተረጋገጠ በጥንት ዘመን ቃልቻ ወይም ቃሉ ለምያስተምረዉ ኣመላካች ወይም ሬፈረንስ ኣለን ማለት ነዉ።

አስርቱ ትዕዛዛት በአለም ዙርያ የታወቀ ኣመላካች ነዉ።

በኢትዮጵያ የኦርቶዶክ ክርስትና የአስርቱ ትዕዛዛት ተሸካሚ እና ጠባቂ ነዉ።

በእስልምናም ሙሴ የታወቀ ነዉ። ይህ ማለት የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ጥናት ትክክል ከሆነ እስልምናም የጥንት ኢትዮጵያ ቃልቻ ወይም ቃሉን የምያዉቅ ብቻ ሳይሆን የምያወድስ ነዉ ማለት ነዉ።

ዋቄፈና በማለት ማስተማር የጀመሩትም ቃሉዎች እና ቃልቻዎች ስለምያስተምሩት መለኮታዊ ነገር መሠረታዊ ግንዛቤ ሊኖራቸዉ የሚችል ይመስለኛል።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ያደረሰበትን እኔ የእሱን ጥናት ሳላዉቅ ነዉ ከሃያ ዓመታት ገደማ በፊት የደረስኩበት።

ጀስቶ በሚል ስም እዚህ መድረክ ላይ የሚሳተፍ ኤርትራዊ እንዴት እንደደረሰበት ባላዉቅም ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዳለዉ በቅርቡ እዚህ መድረክ ላይ ጽፏል።

የጀስቶ ግንዛቤ ከስደት በኋላ ሙሴ የተባለዉ ከስደት በፊት የግብጥ ፈረዖ የነበረ ነዉ የሚለዉ የበለጠ ኣሳማኝ መሆኑን ነዉ።

ሙሴ እስራኤላዊ ሳይሆን የተሰደደ የግብጥ ፈረዖ ነበር ማለት በሁሉም ኢትዮጵያን እና ኤርትራዊያን ዘንድ ኣዲስ ግንዛቤ ነዉ ማለት ይቻላል። ኣዲስ የታሪክ ግኝት ነዉ ማለት ይቻላል።

እስከ ኣሁን ድረስ ብያንስ ሶስት ሰዎች፣ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን፣ ጀስቶ፣ እና እኔ ተመሳሳይ ግንዛቤ ላይ ደረስን ማለት ወደፊት ተመሳሳይ ግንዛቤ የምያካብቱ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን በርከት በማለት በሃገሮቹ ደረጃ ግንዛቤዉ እየሰፋ ይሄዳል ማለት ነዉ።

ሳይንሳዊ ምርምር ኣዲስ ነገር ስያመጣ የወደፊት ኣቅጣጫን የሚጠቁም ይሆናል።

ስለ መለኮታዊ ነገርም ይሁን ታሪካዊ የሆነ ኣዲስ ግንዛቤ ሲሰማ ኣቅጣጨዉን ኣስተዉሎ ስህተትን ኣርሞ ማስተማርን የምያስከትል ይመስለኛል።

በመጀመርያዉ ሬይነሳንስ ዘመን ስለ ጎደስ አቴና ዘመን ኣዲስ ታሪክ መዉጣቱ ቫቲካንን የበለጠ ኣጠነከራት እንጂ ኣላዳከማትም ማለት ይቻልል። ኣንድ የነበረ የካቶሊክ ቤተክርስትያን ወደ ሶስት ቤተክርስትያኖች መከፋፈልን ያስከተለ ቢሆንም ማለት ነዉ።

በሁለተኛ ሬይነሳንስ ዘመን ስለ ፈረዖ አክናተን ዘመን ኣዲስ መለኮታዊ ታሪክ መዉጣቱ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የበለጠ መሠረት ላይ የምያቆመዉ ይመስለኛል።

የኢትዮጵያ እስልምናንም ሙሳ ተብሎ ስለሚወደሰዉ ጥንታዊ ቃልቻንም የበለጠ ግልጽ የምያደርግ ይመስለኛል።

ዋቄፈና ብለዉ የምያስተምሩትም ሙሴ እስራኤላዊ ሳይሆን ምናልባት ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ ያለዉ ታላቁ ፈረዖ አክናተን ሊሆን ይችላል ከተባለ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አደረጃጀት ልምድ ማግኘት ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ መስማማት ላይ የሚደርሱ ይመስለኛል።

ምናልባትም ተመሳሳይ መሠረት ያላቸዉ ይሆናል።

ከደነቁኝ ተመሳሳይነታቸዉ የኣርባ ቀን ተዝካር እና የቦረና ሰዉ ደበሳ ጉዮ ሰዉ ህይወቱ ካለፈ በኋላ እግዝኣብሔር ጋ ቀርቦ ፍርዱን የምያገኘዉ በኣርባኛዉ ቀን ነዉ ያለዉ ነዉ።

ኣብሮ ሄዶ ፍርዱ መቼ እንደሚሰጥ ያየ ማን ኣለ ብዬ በዉስጤ ብገረምም የኣርባ ቀን ተዝካር እና የኣርበኛ ቀን ፍርድ ቀናት ኣንድ መሆን ያልጠበኩት ነገር ነበር።

ይህ ሁሉ የምያመለክተዉ ሶስቱም ድርጅቶች ኣንድ ኣዲስ ግንዛቤን ከሰሙ ኣሁናዊ እና ተገቢ እርምጃ መዉሰድ ይችላሉ ብዬ ኣስባለሁ።

ይህን ኣዲስ ግንዛቤ የሶስቱ ድርጅቶች መሪዎች፣ ማለትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት፣ የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት፣ እና የቃሉማ ወይም ዋቅፈና ሃይማኖት መሪዎች ሙሴ ቃሉ የተባለ ከሆነ ምንን ያመለክታል መባባል የሚችሉ ይመስለኛል።

ይህ ኣዲስ ታሪካዊ ግንዛቤ በሃገር የወደፊት ፖለትካ ላይም ተጽዕኖ ሊኖረዉ እንደሚችል መገመት ይቻላል።

የፖለትካ ሳይንስ ፕሮፌሰር መረራ ጉድና ስለ ቃልቻዎች እና ቃሉዎች ያጠነዉ ያለዉ መሆኑን ኣላዉቅም።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ቃሉ ስላለዉ ሳጠያይቅ በቅርብ ግዜ በደንፋ የምን የነበሩ ሰዉን የምያዉቅ ሰዉን በቀጥታ እንደምያዉቅ ኣስተዋልኩኝ።

ለዚህ ነዉ መለኮታዊ ነገር ምናልባት ለበጎ ነገር ያንዣበበዉ ነገር ያለ ከሆነ ያጤነዉ ነገር ይኖር ይሆን ያስባለኝ።

ኣንዲት ጥያቄ ለመመለስም ይሁን የሶስቱን የሃይማኖት ድርጅቶች መሪዎችን ከማወያየት የሚገለጥ መለኮታዊ ነገር ይኖር ይሆን?

ከተገለጠ የካዉንስል ኦፍ ኒስያ ዐይነት ስብሰባን የሚገብዝ ይሆን?