የጥንት ፈረዖዎች፣ በሃይማኖት መጽሓፎች ዉስጥ የጥጋበኛ ምሳሌ ሆነዉ የሚጠቀሱት ጥንታዊያን የሚመሩት ሕዝብ ነበራቸዉ ብሎ መገመት ስህተት ኣይመስለኝም።
ስለዚህ የፈረዖዎች ሕዝብ ክልል ከዚህ እስከዝያ ነበር እና ነዉ ማለት ይቻላል?
በእኔ ግምት ቃልቻዎች እና ቃሉዎች ያልተደራጁ ነገር ግን ጥንት ግዜ ጀምሮ የነበሩ ባህላዊ የሃይማኖት መሪዎች ናቸዉ።
ይህ ስህተት ካልሆነ የቃልቻዎች እና የቃሉዎች ሕዝብ ክልል ከዚህ እስከዝያ ነበር እና ነዉ ማለት ይቻላል?
በቦረና ቆንቆ ማለት ጉሮሮም ቋንቋም ማለት ነዉ። ካልዘነጋሁ የማያዉቁትን ቋንቋ የሚናገርን ሰዉ ቆንቆ ከም ዱበተ ማለት ነበረ። ምን ቋንቋ ነዉ የሚናገረዉ ማለት ነዉ።
ስለዚህ እኔ እንደ ኣንድ ሰዉ ሳሰላስል ቆንቆ ማለት እና ቋንቋ ማለት ተመሳሳይ ትርጉም ኣላቸዉ።
ይህ ስህተት ካልሆነ ቆንቆ እና ቋንቋ የሚሉ ሕዝብ ክልል ከዚህ እስከዝያ ነበር እና ነዉ ማለት ይቻላል?