Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40158
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጎላ ሰፈርን ስንቶቻችሁ ታውቁታላችሁ?

Post by Horus » Today, 16:45

ጎላ ሚካሌል ያለበት ጎላ ሰፈር (የጦር ሰፈር ማለት ነው) ድሮ የምኒልክ ፊት በር ቤተ መንግስት ሲሰራ ድብን ያለ የጅብ ጫካ ስለነበር ብዙ ሰው በጅብ የተበላበት ቦታ ነው ። ያለው ከጥቁር አምበሳ ሆስፒታል ፣ ሴጣን ቤትና ቴዎድሮስ አደባባይ እስከ ተክለ ኃይማኖትና የኤርትራዎች ሰፈር እስከ ነበረው ደቀ መሃሪ ያለው ነው። የኤርትራና ትግሬ ሰዎች በብዛት ስለሚኖሩበት የትግሬ ጠላ (ጽራይና ድቋይ) በንጉስ ሚካኤል የቀንድ ዋንጫ የምንጠጣው እዚያ ነበር ። ከመርካቶ ካምቦሎጆ ውለን ማታ የምንመለሰው በዚያ ነበር ። አማራ ጉራጌ ትግሬ ሕዝብ ድብልቅ መኖሪያ ነበር። ዛሬ ይህን ይመስላል!!! ይህ ፎቶ የተነሳው ቴድሮስ አደባባይ ላይ ወደ ሰንጋ ተራ አስመልክቶ ነው ። መሃል ላይ ያሉት ደሳሳ ቤቶች አሁንም አሉ



Dama
Member+
Posts: 6416
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: ጎላ ሰፈርን ስንቶቻችሁ ታውቁታላችሁ?

Post by Dama » Today, 17:19

What's the debt to future generations? Many have been asking this question since Corridor. Ethiopians want answers.
:twisted: :evil:

Post Reply