Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7174
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኢትዮጵያ ዉስጥ የኖሩ የፈረኦዎች ኣሻራዎችን ያጠኑ የኢትዮጵያ ምሁራን ኣሉ?

Post by Naga Tuma » 18 Dec 2025, 16:29

የጥጋበኛ ምሳሌ ተደርገዉ የሃይማኖት መጽሓፎች ዉስጥ የተሳሉት የኣፍርካ ፈረኦዎች ምድር ላይ ግዙፍ የሆኑትን ፒራሚዶች ከማንም በፊት ቀድመዉ የገነቡ ወይም ያስገነቡ ነበሩ።

ፒራሚዶቹን የምያክሉ እስከዚህ ዘመን ድረስ ምድር ላይ የሚታዩ ቅርስ ያላቸዉ ፈረኦዎች ሌሎች ጉልህ ኣሻራዎች እንዳላቸዉ መጠራጠር ኣይቻልም።

መጠራጠር ባይቻልም ከስደት ዘመን በፊት ጀምሮ ያልተዳሰሱትን ማጥናት እና ኣሻራዎቹ እነዚህ ናቸዉ ማለት ትልቅ ምሁራዊ ችሎታ እና ጥልቅ ጥረት ያስፈልጋል።

በምሁራዊ ችሎታቸዉ እና ጥልቅ ጥረታቸዉ እነዚህ የፈረኦዎች ኣሻራዎች ናቸዉ የሚሉ ምሁራንን ጥናቶች ማግኘት ይቻላል?

እኔ የታሪክ ተማሪ እና ተመራማሪ ባልሆንም በርካታ መጽሓፎችን እና የተለያዩ መጣጥፎችን ኣንብቤ ሙሴ እስራኤላዊ ሳይሆን ከስደት በፊት አክናተን የተባለ ታላቅ የኣፍርካ ፈረኦ መሆኑን ከብዙ ዓመታት በፊት ተገንዝቤኣለሁ።

ይህ ታላቅ ፈረኦ ምድር ላይ ሞኖቴይዝምን ወይም ኣንድ ኣምላክ ማለትን ለመጀመርያ ግዜ ጀምሮ ያስተማረ መሆኑ ይታወቃል።

ሞኖቴይዝም የዚህ ታላቅ ፈረኦ ኣንዱ ኣሻራ ነዉ።

ከብዙ ዓመታት በፊት መነቡና የተባለ መድረክ ላይ ዋቀ ቶክቸ ኤንደ ሞኖቴይዝም ብዬ የዘገብኩኝ ረጅም ርዕስ ሞኖቴይዝም እና ዋቀ ቶክቸ ማለት በጽንሰሀሳብ ተመሳሳይ መሆናቸዉን ለማመልከት ነበር።

የዚህ ታላቅ ፈረኦ ሌላ ኣሻራ ከስደት በኋላ እስራኤሎችን ለመጀመርያ ግዜ ግርዛትን ማስተማሩ ነዉ።

ከበርካታ ዓመታት በኋላ ኣንድ የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንን ስራ በኣጋጣሚ ሰምቼ ሎሬቱ ከእኔ በላይ በጥልቅ ኣጥንቶት የዚህን ታላቅ ፈረኦ ኣሻራ በቅኔዎቹ የመዘገበዉ ይመስለኛል።

ሎሬቱ

እደ እዶ ምድር
ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ
ተነባቢ የአስር ምስጥር
ለካ ኣንተ ነህ

ያለዉ ስለ ታላቁ ፈረኦ አክናተን ይመስለኛል። ይመስለኛል የምለዉ የሎሬቱን ቃላት በመስማት ብቻ ያለዉን ማረጋገጥ ስለማልችል ነዉ።

ተነባቢ የአስር ምስጥር ያለዉ የሙሴን አስርቱ ትዕዛዛት መሆኑ ከተረጋገጠ ሎሬቱ ቃሉ ያለዉ ታላቁ ፈረኦ አክናተን መሆኑ ነዉ።

እንደ ኣዲስ ግኝት ለካ ኣንተ ነህ ማለቱ እስራኤላዊ ሳይሆን ኣፍርካዊ ነበረ ማለት መሆኑን መገመት ይቻላል።

ይህን ማረጋገጥ ከተቻለ አስርቱ ትዕዛዛት የታላቁ ፈረኦ ሌላ ኣሻራ ይሆናል ማለት ነዉ።

ካልተሳሳትኩ የኢትዮጵያ ፊደል የፈረኦዎች ኣሻራ ነዉ ማለት ይቻላል።

ሌላም ካልተሳሳትኩኝ አስርቱ ትዕዛዛት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ታቦት የሚሸከመዉ እና የሚጠብቀዉ ነዉ።

ይህም ከተረጋገጠ ሎሬቱ በቅኔ የተናገረዉ ታቦቱ የሚሸከመዉ እና የሚጠብቀዉ ያታላቁ ፈረኦ ትዕዛዛትን ነዉ ማለት ይሆናል።

ለዚህ ሁሉ ኣሻራዎች ቁልፍ ማስረጃ መሆን የሚችለዉ የኢትዮጵያን ታሪክ በሰፊዉ ኣጥንቶ መጽሓፍ ያሳተመዉ ፕሮፌሰር ዶናልድ ኤን ለቪን ነዉ።

የፕሮፌሰሩ መጽሓፍ ዉስጥ የአክሱም መሪዎች የነበሩት ሴሜትክ ሳይሆኑ በሃይማኖት ምክንያት ቀድሞ የምያዉቁትን ማንነት መተዉም ሆነ አዲስ ማንነት መቀበል ቸግሯቸዉ ያዘገመ የማንነት ትግል ዉስጥ የገቡ ነዉ ይላል።

ይህም እራሱን የቻለ ኣሻራ ነዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

የእኔ የተወሰነ ጥናት የምያመለክተዉ መለኮታዊ የሆነ የጎሳዎች ጽድቅ እና እርግማን የሚል ጽንሰሀሳብ ከታላቁ ፈረኦ አክናተን ስደት በኋላ የመጣ እንጂ ከዛ በፊት ያልነበረ መሆኑን ነዉ።

ለማጠቃለያ ያህል እላይ የጠቀስኩኝ የፈረኦዎች ኣሻራዎች ሞኖቴይዝም፣ ግርዛት፣ አስርቱ ትዕዛዛት፣ ፊደል፣ እና የማንነት ትግል ናቸዉ።

እነዚህ ሁሉ እኔ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ስል ስለምን እንደሆነ ኣመልካች ናቸዉ።

የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ የጎደስ አቴና ዘመን የነበሩትን ኣሻራዎችን በሰፊዉ ኣጥንቶ የተነሳ ነዉ።

በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ ታላላቅ ሳይቲስቶች ከሚባሉት ዉስጥ የአርኪሚዲስ ግኝት በመጀመርያ ሬይነሳንስ ዘመን የተገኘዉ በጎደስ አቴና ዘመን ኣሻራ ዉስጥ ነዉ።

ይህ ማለት የታላቁ ፈረኦ አክናተን ዘመን ኣሻራን መፈተሽ አቧራ ለብሰዉ የኖሩትን አቧራዉን እያራገፉ ማግኘት እና ማወቅ ይቻላል ማለት ነዉ።

የሬይነሳንስ መሠረቶች ከክርስትና ሃይማኖት በፊት ተፈጽመዉ ከክርስትና መወለድ በኋላ ኣሻራ ሆነዉ የኖሩ ስለሆነ ሬይነሳንስ ማለት እና ክርስትና ማለት ኣይጣጣሙም ማለት ይቻላል።

እንዲጣጣሙ የምያደርገዉ ኣሻራዎቹን እያጠኑ የሃይማኖት መጽሓፍ ዉስጥ የሰነበቱትን ስህተቶችን በማረም ነዉ።

የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ የማይጣጣሙትን ለየብቻ ማድረግ ነዉ የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰ።

አሜሪካ ዉስጥ ሴፓሬሽን ኦፍ ቸርች ኤንደ ስቴት የሚለዉ ይህ መሆኑ ከሁለት መቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት የተጻፈዉ ሕገመንግስት ያመለክታል።

የሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ከክርስትና ጋር ኣለመጣጣም ቁልፍ መሰናክል በኣንድ በሉል የታላቁ ፈረኦ አክናተንን አስርቱ ትዕዛዛት እየጠበቀ እና እያከበረ በሌላ በኩል ታላቁ ፈረኦኑን ማዉገዝ መሆኑ ነዉ።

ለዚህም በፈረኦኖቹ ዘመን አርገመኒ ቆሬ ያረመዉ ኣሻራ ኣለ። ምናልባትም የአርኪሚዲስ ግኝት በመጀመርያዉ ሬይነሳንስ ዘመን የጎደስ አቴና ዘመን ኣሻራ ሆኖ እንደተገኘዉ የአርገመኒ ቆሬ አርገ ዸጌቲ በሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ዘመን የታላቁ ፈረኦ አክናተን ዘመን ኣሻራ ሆኖ ይታወቅ ይሆናል።

ቦረና ዉስጥ የሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን አርገ ዸጌቲን እንደ ባህል ጠብቀዉ የኖሩት ለህያዊ እና ምድራዊ ብለዉ የቃሉ እና የገዳ ባህላዊ ድርጅቶች ለየብቻ ናቸዉ ያሉ ናቸዉ።

ስለ መለኮታዊ ነገር ጥልቅ ዕዉቀት የሌለኝ ቢሆንም ይህም ጥንታዊ ኣሻራ ጥንታዊ የሆነን ስህተት ማረም የምያስችል ይመስለኛል።

የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ ቫቲካንን ጭምር ኣጠነከራት እንጂ ኣላዳከማትም። በሳይንሳዊ መንገዶች ኣዳዲስ ዕዉቀቶችን ስለጨመረላት ነዉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሆነ ባህላዊ የቃሉ ድርጅቶች በሳይንሳዊ መንገዶች ኣዳዲስ ዕዉቀቶችን ብያገኙ ግልጽ የሆኑ ስህተቶችን ኣርመዉ መጠንከር እና ምናልባትም መጣጣም የሚችሉ ይሆናል።

ግልጽ የሆኑ ስህተቶችን ማረም ብሉይ ኪዳን በኣዲስ ኪዳን እንደተተካዉ ኣዲስ ኪዳንም ታድሶ በሌላ ኪዳን የሚተካ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሆኗል።

ይህ ማለት ደግሞ የቀዳማዊት ኢትዮጵያ የሃይማኖት ድርጅት ቫቲካን በተጸነሰ የጽድቅ ሃይማኖት መጽሓፍ ሳይሆን እራሱ ስህተቶቹን ሁሉ መርምሮ በማረም ባዘጋጀዉ የጽድቅ ሃይማኖት መጽሓፍ ይሆናል ማለት ነዉ።

ምናልባትም ይህን የምያመላክት የቀዳማዊት ኢትዮጵያ ኣምላክ ከቫቲካን ጋር ያልተገባደደ ጉዳይ መኖሩን ቢጠቁም ይሆናል።

ስለዚህ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተገኙትን የፈረኦዎች ኣሻራዎችን ማጥናት መሠንበት ያልነበረበት፣ ጥልቅ ጥረት መሆን የነበረበት ይመስለኛል።