ምረጡኝ ምረጡኝ ለአምስት አመት
ኮሪደር ኮሪደር የምርጫዮ ትኬት
ምንም እንኳ አገር ባላረጋጋ
ኢኮኖሚው ወድቆ ብር ቢያጣ ዋጋ
ሚልዬኖች ቢሞቱ ስልጣኔን ሳረጋጋ
እክሳለሁ እጥፍ ቀኑ ሲነጋጋ
አገሩቱ አድፋ በሙስና ተጨማልቃ
ተረኛ ኬኛ ብሎ አደረጓት የእርሱ እቃ
ምን አገባኝ እኔ ሚልሻ ይጠበቃ
7ኝው ንጉስ ስልጣኑን አይለቅም
በምርጫም በሜንጫም አለው ሙሉ አቅም
ብትመርጡኝ ይሻላል በግድም በውድም
ፋኑዬ ፥ OLA፥ TDF ግቡልኝ በሰላም
በስልጣን አምሮት ናላው የዞረበት
ቀይ ካርድ ይገባዋል አውሩዱት በቅፅበት