Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39769
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ፕሮጀክቶችና የተቀጣጠለው የኢኮኖሚ እድገት!

Post by Horus » 16 Nov 2025, 18:42

Ethiopia is beyond the turning point, beyond the tipping point. What is happening? ለምን? ይህን ሁሉ የኢኮኖሚ እድገት የሚነዳው ነዳጅ ምንድን ነው?

ለምሳሌ 3 የገንዘብ ምንጮችን ማሰብ እንችላለን፡
(1) የአገር ውስጥ ቁጠባና ትርፍ
(2) ከውጭ ወደ ውስጥ የሚገባ ኢንቨስትመንት
(ሃ) ሬሚታንስ
(2) ኢቨስቲመንት
(3) ብድር

ስለ አገር ቁጠባና ትርፍ ፣ በአገር ውስጥ ስለሚፈጠረው የሃብት መጠን ብዙ የተነገረ እስታስቲክስ ስለሌለ እንለፈው።

ስለ ሬሚታን ብዙ ተብሏል ። ለምሳሌ በ2025 ከዲያስፖራ በሃላዋ፣ ንብረት በመግዛትና ኢንቬትመንት በመጀመር እስከ 12 ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ይገባል ተብሎ ይገመታል። ይህ ፍጹም አስደናቂ ቁጥር ነው። ለቤተሰብና ዘመድ መደጎሚያ የሚላከው ቢሊዮኖች ብቻ ሳይሆን ባዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ገጠሮች የሚበነቡት እጅግ ቅንጡና ውድ ቤቶችን የሚገዙት ያገር ውስጥ ሃብታሞች ብቻ ሳይሆኑ የዲያስፖራ ኢንቬስተሮች ናቸው።

በዚህ የተነሳ የኢትዮጵያ ሪል እስቴት ጉድ በሚያሰኝ ደረጃ እየተቀጣጠለ ነው ።

ሌላው ከፍተኛ የኢንቬትመንት ፍሰት ከአረብ አገር ፣ ከኤሲያ ፣ ከአውሮፓና ሰሜን አሜሪካ እየጎረፈ ያለው ሃብት ነው ። ከዚህ በታች ያሉትን ፕሮጀክቶች ፣ ተቋሞችን ተመልከቱ!

(1)የኢትዮጵያ ባህር በር እና ባህር ኃይል ጥያቄ ፤ መርከቦችና ጀልባዎችን ለኢትዮጵያ የሚያቀርቡት አገሮች
(2) የህዳሴ ግድብና ሌሎች አባይ ላይ ስለሚገነቡ ግድቦች ፤ ግድብ ገምቢ አለም አቀፍ ድርጅቶች ፣ አገሮች ፣ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ የሚገዙ አገሮችና የዳታ ማይኒግ ግዙፍ አለም አቀፍ ኩባኛዎች ።
(3) የኢትዮጵያ የውሃ ህብትና የውሃ ኃይል ጥያቄ ፤ የዉሃ ፋብሪካዎችና የዉሃ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች
(4) የአረንጓዴ ኢትዮጵያና አገር አቀፍ የደን ልማት ጥያቄ ፤ የአረንጓዴ ልማት እራሱን የቻል የችግኝ ፣ የዉሃ ፣አፈርና ያየር ንብረት እንዱስትሪነት!
(5) ኮሪደርና የኢትዮጵያ ከተሞች ዝመና ጥያቄ ፣ የከተማ ኮሪደር ሌላ አንድ ሙሉ የስራ ቀጣሪና ለመገመት የሚታክት የብረታ ብረት፣ እንጨት፣ ሲሚንቶ ወዘተ አቅርቦት ኢኮኖሚ መሆኑ !
(6) የኢትዮጵያ እርሻ ዝመናና የመስኖ ልማት ጥያቄ ፣ ዘመናዊ እርሻ በሳይንስና ምርምር ብቻ ሳይሆን የመስኖ ማሺነሪዎች ከውጭ በመግዛት ዙሪያ ያለው ለመገመት የሚታክት ፖቴንሺያ ያለም ሻጮችን ሁሉመሳቡ!
(7) የማዳበሪያ ፋብሪካ ግምባታ ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመክፈር ዳንጎቴ ያፈሰሰው 3 ቢሊዮን ዶልላር!
(8) የእርሻ ትራክተር ፋብሪካ ግምባታ እና ከውጭ የሚሸጡልን አገሮች እንደ ምስራቅ አውሮፓዎች
(9) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፣ ጥንትም የሚታወቀው እኤሌክትሪክ ኃይላችን አሁን ደሞ ለግዙፍ ፋብሪካዎች ማደግ ምንጭ መሆን!
(10) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ አየር መንገድ ከቦዪንኛ ጄኔራል ኤሌክትሪክ ሞተር ጋር ያለው የቢሊዮኖች ኢቨስትመንት ፣ አሜሪካና ስዊስ 12 ቢሊዮን ዶልላር በማፍሰስ ሜጋ ቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግምባታና ይህ ፕሮጀክት የሚፈጥረው የስራና ቴክኖሎጂ በረከት!
(11) የኢትዮጵያ ቴሌኮም ፣ አስደናቂው የኢትዮቴሌኮንም እና ኢትዮጵያን ዲጂታላይዘድ አድርጎ የተቀጣጠለው ዘመናዊ ግብይትና ኮሚኒኬሽን
(12) የዲጂታል ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ፣ ጠቅላላው የኢትዮጵያ ሲስተሞች ዲጂታል መሆንና ያ የፈጠረው አዲስ እራሱን የቻለ ዲጂታል ኢንዱስትሪና የስራ መስክ
(13) የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ ክህሎት ፕሮጀክት ፣ ኤ አይ ያመጣቸው አዲስ የስራ መስክ
(14) የኢትዮጵያ እስፔስ ሳይንስ ምርምር ጉዳይ፣ ያየር ንብረትና ሳተላይት ቴክኖሎጂ ያመጣው አዲስ የስራ መስክ
(15) የኢትዮጵያ ኑክሊየር ኃይል ምርመር ጉዳይ ፣ የኢትዮጵያ ንክሌር ኃይል ፕሮጀት የሚፈጥረው አዲስ የእውቀትና ሥራ መስክ
(16) የኢትዮጵያ እስቶክ ማርኬት ጉዳይ ፣ የኢትዮጵያ እስቶክ ንግድ ሲስተም ያመጣው የሃብት ፈጠርና ዘመናዊ ፊናንስ እድገት ፣ በዚህ ምክኛት ከውስጥ ብቻ ሳይሆን ከዲያስፖራና ውጭ ኢቬስተሮች ወደ አገር የሚፈሰው ቢሊዮኖች ዶላር!
(17) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮጀክት ፣ በኢንዱስትሪው መስክ መገመት የማይቻል የውጭ ኩባኛዎች ካብሪካቸውን በኢትዮፕያ መትከልና ሚሊዮኖች ያገር ወስጥ ሕዝብ መቅጠር
(18) የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ፣ የቱሪዝም መሻሻል
(19) የኢትዮጵያ እስታጽቲክስ ሳይንስ እድገት ፣ የስታጽቲካል አገልግሎት መፋፋት
(20) የኢትዮጵያ አርትና ስነጽሑፍ እድገት ጉዳይ ፣ አለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ማተሚያ ድርጆቶች ወደ ኢትዮጵያ መግባትና ለ30 ሚሊዮን ተማሪዎች በቢሊዮን የሚቆጠሩ መጻህፍት አገር ውስጥ ማተም
(21) የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ እድገት ጉዳይ ፣ በወርቅ ልማት በ2026 ኢትዮጵያ ያፍሪካ 1ኛ ወርቅ አምራች ትሆናለች!
(22) የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮሊየም ኢንዱስትሪ ልማት፣ የቻይናው ኩባኒያ የከፈተው የ3 ቢሊዮን ዶላር ነዳጅ ማጣሪያና ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ነጋጅ ኤክስፖርተር መሆን
(23) ከአፍሪካ 1ኛ የሆነ ያገር መከላከያ ፣ ያገር መከላከያ የራሱን ጦር መሳሪያ ማረትና ለሌሎች ሁሉ መሸጥ
(34) የሲሚንቶ ኢዱስትሪ ። ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ የራሷን ሲሚንቶ ማምረትና

እና ሌሎችም የእድገት መስኮች ናቸው ያገራችንን እድገት በዚህ መልክ እያቀጣጠሉት ያለው ።



Post Reply