Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6754
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የህሊናቢስነት ልክ እና ጥግ

Post by Naga Tuma » 06 Nov 2025, 15:59

የሚከተሉት ሁለት ቪድዮዎች የየራሳቸዉ ታሪክ ኣላቸዉ።

የመጀመርያዉ ቪድዮ የኣፍርካ ኣንድነት መዝሙርን የጻፈዉ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ከሃምሳ ዓመታት በፊት የጻፈዉ ነዉ።

ሁለተኛዉ ቪድዮ ተዋቂ ዘፋኝ የነበረዉ በኋላ ሉበ ሆኛለሁ ብሎ ባህላዊ ዘፈን ተዉ የማለት ሰበካ የጀመረዉ የአብተዉ ከበደ ፉፋ ነዉ።

ባህላዊ ዘፈን ዝፈኑ እና ሃይማኖት በማለት ባህላዊ ዘፈን ተዉ የምያመለክቱት ኣቅጣጫዎች መታረቅ የማይችሉ ናቸዉ።

የተለያዩ ኣቅጣጫዎችን ማሳየት ስህተት ቢሆን እንጂ ወንጀል ኣይመስለኝም።

የታወቀ ዘፋኝ የነበረዉ አብተዉ ከበደ ፉፋ ሉበ ሆኛለሁ ብሎ መዝፈን ትቻለሁ ብሎ ይሰብካል።

የድሮ ዘፈኑን ትንሽ ኣንጎርጉሮ ወድያዉ ሌላ ሉበ መጥተዉ በዱላ ሳይቀጡኝ በፊት ኣቁሜኣለሁ ይላል።

መዝፈንን ለምን እንደተወ ደብዳቤዉን የምያዉቀዉ ባለቤቱ ነዉ ብሎ ይቋጫል።

ይህ የኣንድ ግለሰብ ዉሳኔ ከሆነ መዝፈንን ሆነ መዝፈንን መተዉ መብቱ ነዉ።

የባህል ዉዝዋዜን ኢትዮጵያ ለምዳ አሜሪካ ዉስጥ ኣይቼ የተደሰትኩኝ ልጅ አሜሪካ ደርሳ ብዙ ሳትቆይ ባህል ተይ ተብላ እርግፍ ኣድርጋ ተወችዉ ማለትን ሰምቼ ደነገጥኩኝ።

ስምን እግዝኣብሔር ያወጠዋል እንዲሉ ስሟ አመርቲ ነዉ።

የትኛዉ የገዳ ስርዓት ዉስጥ ኣልፎ ሉበ ሆኛለሁ ማለቱን እና መዝፈንን ትቻለሁ ማለቱን ሳልሰማ በፊት ነበረ የኢትዮጵያ ባህላዊ ዘፈኖችን ተዉ የሚል ዘመቻ ኣለ መባሉን ሰምቼ መዝፈንም መብት ኣለዉ የሚል ትግል ጀመርኩኝ።

ከሃያ ዓመታት በፊት የባህል ዘፈን ተዉ የማለት ዘመቻ ላይ የነበሩት ዘፋኞች እየመሰሉ ብቅ ማለት ጀመሩ።

ከነበሩበት የኣትዝፈኑ ኣቅጣጫ ወደ መዝፈን እንችላለን ኣቅጣጫ መመለስም ወንጀል ኣይዴለም።

ህልናቢስነቱ ከኣትዝፈኑ ኣቅጣጫ ወደ መዝፈን እንችላለን ኣቅጣጫ ከተመለሱ በኋላ መዝፈን ኣንተዉም ብለዉ የታገሉትን በዘፈን አሽሙር መዉቀስ ነዉ።

ይህ የህሊናቢስነት ልክ እና ጥግ ኣይዴለም?

ይህ ህሊናቢስነት ነዉ ማለት የማይችሉት የዳበረ ባህል ኣላት የምትባለዉ የኢትዮጵያ ሰዎች ናቸዉ?


አደጌን ቃሉ ጄቹ ህን ቤክኔ
አደጌን ቃሉ ቤካ ህን ሴኔ
አደጌን ቤካ ህን ቤክኔ
አደጌን ቤኩምሰ ህን ቤክኔ
አደጌን መዳን ጉረ ህንሴኔ
ጄቴ በር አደዊን ደቺ ሴኔ