Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39783
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አቢይ አህመድ ርዕዮተ ዓለም ምን እንደ ሆነ አያውቅም

Post by Horus » 07 Jun 2023, 23:27

እኔ ሆረስ ቃላት በመፍለጥ ሰው አላሰለችም። አቶ አቢይ አህመድ መደመር የሚባል ርዕዮተ ዓለም አለ ብሎናል ። አለ ብሎም ባለብዙ ዝባዝንኬ መጻህፍት አሳትሟል ። ታዲያ አይዲኦሎጂ ምንድን ነው? አይዲኦሎጂ ከየት ነው የሚመጣው?

አይዲኦሎጂ የሁለት ቃላት ጥምር ነው ፤ አይዲያ እና ሎጎስ። የአማርኛው ቃል ርዕዮተ ዓለም ሎጎስ የሚለውን በአለም ተክቶታል። በጣም ጥሩ ነው። ሎጎስ ቃል ወይም ጥናት ወይም የአንድ ነገር ሎጂክ ማለት ስለሆነ እሱን እንተወው ።

ዋናው ቃል አይዲያ ወይም ርዕዮት የሚለው ቃል ነው ። ይህ ቃል ከግሪክ ስልጣኔ ጀምሮ እስከ ዛሬ ብዙ ፍልስፍና የተቀመረበት ስልሆነ ማንም በቀላሉ የሚያምታታው ጽንስ አይደለም ። ቃሉ ፕሌቶ እንዳለው ባዶ፣ ንጹህ፣ ከምንም ነባራዊ ነገር ያልተያያዘ ሃስብ ሳይሆን አሪስቶትል እንዳረመው የነገር ቅጂ ምስል ማለት ነው ።

አይዲያ ወይም ርዕዮት የአንድ ነገር ማለት ነባራዊ ነገር፣ የአንድ ሪያሊቲ ግልባጭ ፣ ቅጂ፣ ኮፒ ፎርም፣ ቅርጽ፣ ምስል፣ ስዕል ማለት ነው። በአንድ ቃል የሌለ ነገር፣ ህያው ያልሆነ ነገር፣ ህልውና የሌለው ምናብ ምስል የለውም። ኢሉዝን፣ ወይም ንጹህ ኢማጂኔሽንልብ ወለድ ፋንሲ ርዕዮት አይደለም ። ስለዚህ ርዕዮት ከሰዎች አይምሮ፣ ከሰዎች ህልም በዘፈቀደ ተመኝቶ ያንን ባዶ ምናብ የሪያሊቲ ቅርጽ ነው፣ የአለም ፎርም ነው፣ የነዋሪ ነገር ምስል ነው ማለት ፍጹም ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛ የሳይኮሎጂ ፓቶሎጂ ነው ።

ስለሆነም ስለ አንድ የማሀበረ ሰብ ርዕዮተ ዓለም ወይም ምስለ አለም፣ ወይም ስዕለ አለም ስናወራ ያ ምስል ህያው ከነበረ ፣ ከኖረ ፣ ሊኖር ከሚችል ማህበራዊ ስርዓት የተቀዳ ምስል እንጂ ከሰው አይምሮ የተፈበረከ ኢሉዝን ፣ ሚራክል ወይም ታምር የሚቀዳ አይደለም ። ስለዚህ ነው ስለ ፖለቲካ ር ዕዮተ አለም (ምስለ አለም) ስናስብ በአለም ላይ የነበሩና ያሉ ፖለቲካ ሲስተሞችን ምሳሌዎች፣ ምስሎች የምናጠናው እንጂ ከባዶ አንጎላችን ህልምና ኢሉሽን እያየን ያንን እንደ አይዲኦሎጂ መስበክ ድንቁርና ብቻ ሳይሆን እብደት ነው።

ስለዚህ የአቶ አቢይ መደመር ርዕዮተ ዓለም አይደለም ። ከምንም ነባራዊ አገር፣ ፖለቲካ ፣ ስራዓት የተቀዳ ምስል አይደለም ፣ የምንም ስራት ስዕል አይደለም፣ የአንድ ሰው ባዶ ሃስቦች በፊደል የተጻፈ ህልምና ምናብ ነው ።መደመር የሚባል የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ ሶሺያል ርዕዮተ ዓለም፣ ምስለ ፖለቲካ፣ ርዕዮተ መንግስት በየትኛውም አገር አልኖረም ።

ኢትዮጵያ ውስጥ እከሌ የሚባሉ ምሁራን ካሉ ይህን መረን የለቀቀ ኢሉዥን መርምረው ጸሃይ ላይ ማስጣት አለባቸው ። በኢትዮጵያ ምንም ነገር የማይሰራው መደመር በተባለ የአንድ አላዋቂ መሪ ጭለማ ውስጥ አገር ስለሚታመስ ነው ።

በአለም ላይ ያሉት የኢኮኖሚና ፖለቲካ ስርዓት አይነቶች ይታወቃሉ ። መደምር የሚባል ግን የለም !

eden
Member+
Posts: 9973
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Post by eden » 27 Oct 2025, 19:40

I must say, your command of written Amharic is superb. You’re gifted in articulating your ideas. Not only that, your ability to breakdown complex concepts for us average folks is unmatched.

The thing is you persuade us, then you change your mind. It’s okay to change your mind but you make no effort to persuade us why you change your mind on issues you feel very strongly about such us this very subject.

Polar opposite views on Abi Ahmad from one individual:

የአንድ አላዋቂ መሪ

የኢትዮጵያ ከማል አታቱርክ

Misraq
Senior Member
Posts: 16521
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: አቢይ አህመድ ርዕዮተ ዓለም ምን እንደ ሆነ አያውቅም

Post by Misraq » 27 Oct 2025, 21:37

eden wrote:
27 Oct 2025, 19:40
I must say, your command of written Amharic is superb. You’re gifted in articulating your ideas. Not only that, your ability to breakdown complex concepts for us average folks is unmatched.

The thing is you persuade us, then you change your mind. It’s okay to change your mind but you make no effort to persuade us why you change your mind on issues you feel very strongly about such us this very subject.

Polar opposite views on Abi Ahmad from one individual:

የአንድ አላዋቂ መሪ

የኢትዮጵያ ከማል አታቱርክ
:lol: :lol: post of the month. Super smart Eden calling herself average while elevating the lackluster Huressa to IQ125 level. Very classic :lol: :lol:

ሁሬሳ ዥዋዥዌ ው ፡ አወዛገብከን እኮ የተለያየ፡ ሃሳብ እያንፀባረቅክ : ። በአብዛኛው የምትለው ፡ ነገር እርስ በርሱ : ይጋጫል

Horus
Senior Member+
Posts: 39783
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አቢይ አህመድ ርዕዮተ ዓለም ምን እንደ ሆነ አያውቅም

Post by Horus » 27 Oct 2025, 22:10

ምስራቅ የተባልሽ ጠጣር ዝንጀሮ!
ዛሬ ላይ አቢይ አህመድን የምደግፍባቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች በዝርዝር ቆጥሬ ያስቀመጥኩኝ የራሴ ማኒፌስቶ ያለኝ የነቃ የፖለቲካ እንሰሳ ነኝ። እኔ መደመር የሚባል አይዲዮሎጂም ሆነ መጽሃፍ በአይኔ አይቼ አላውቅም ። አቢይ አህመድ ዛሬ የአገሪቱን ጥቅሞች ለማራመድ የሚሰራቸውን ስራዎች ለመስራት መደመርም ሆነ ሌላ አይዲዮሎጂ አያስፈልጉትም ። ዛሬም ቢሆን አቋሜ ነው መደመር የሚባል አይዲዮሎጂ በአለም ላይ የለም ። የብልጽኛ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ካፒታሊስት አይዲኦሊጂ ሲሆን ጥንካራ መንግስት መር የሆነ ካፒታሊዝም ነው ! አለቀ።

አንቺ ግን መሃይም የጠላት መሳሪያ ያገር ጠላት ካንሰር ነሽ! አማራን የሻቢያና ወያኔ ትግሬ መሳሪያ በማድረግ ያማራ አገር የሆነውን ወልቃይትና ራያን ለትግሬ ተስፋፊዎች በመሸጥ አማራን ከጀርባ የምትወጊ ቅጥረኛ የግብጽ ገረድ ነሽ! አበቃሁ!

Misraq
Senior Member
Posts: 16521
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: አቢይ አህመድ ርዕዮተ ዓለም ምን እንደ ሆነ አያውቅም

Post by Misraq » 27 Oct 2025, 22:24

ሁሬሳ ይህ የEden thread ስለሆነ የኤደንን መልስ እንጠብቅ

Naga Tuma
Member+
Posts: 6754
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: አቢይ አህመድ ርዕዮተ ዓለም ምን እንደ ሆነ አያውቅም

Post by Naga Tuma » 28 Oct 2025, 00:18

Horus wrote:
07 Jun 2023, 23:27
እኔ ሆረስ ቃላት በመፍለጥ ሰው አላሰለችም። አቶ አቢይ አህመድ መደመር የሚባል ርዕዮተ ዓለም አለ ብሎናል ። አለ ብሎም ባለብዙ ዝባዝንኬ መጻህፍት አሳትሟል ። ታዲያ አይዲኦሎጂ ምንድን ነው? አይዲኦሎጂ ከየት ነው የሚመጣው?

አይዲኦሎጂ የሁለት ቃላት ጥምር ነው ፤ አይዲያ እና ሎጎስ። የአማርኛው ቃል ርዕዮተ ዓለም ሎጎስ የሚለውን በአለም ተክቶታል። በጣም ጥሩ ነው። ሎጎስ ቃል ወይም ጥናት ወይም የአንድ ነገር ሎጂክ ማለት ስለሆነ እሱን እንተወው ።

ዋናው ቃል አይዲያ ወይም ርዕዮት የሚለው ቃል ነው ። ይህ ቃል ከግሪክ ስልጣኔ ጀምሮ እስከ ዛሬ ብዙ ፍልስፍና የተቀመረበት ስልሆነ ማንም በቀላሉ የሚያምታታው ጽንስ አይደለም ። ቃሉ ፕሌቶ እንዳለው ባዶ፣ ንጹህ፣ ከምንም ነባራዊ ነገር ያልተያያዘ ሃስብ ሳይሆን አሪስቶትል እንዳረመው የነገር ቅጂ ምስል ማለት ነው ።

አይዲያ ወይም ርዕዮት የአንድ ነገር ማለት ነባራዊ ነገር፣ የአንድ ሪያሊቲ ግልባጭ ፣ ቅጂ፣ ኮፒ ፎርም፣ ቅርጽ፣ ምስል፣ ስዕል ማለት ነው። በአንድ ቃል የሌለ ነገር፣ ህያው ያልሆነ ነገር፣ ህልውና የሌለው ምናብ ምስል የለውም። ኢሉዝን፣ ወይም ንጹህ ኢማጂኔሽንልብ ወለድ ፋንሲ ርዕዮት አይደለም ። ስለዚህ ርዕዮት ከሰዎች አይምሮ፣ ከሰዎች ህልም በዘፈቀደ ተመኝቶ ያንን ባዶ ምናብ የሪያሊቲ ቅርጽ ነው፣ የአለም ፎርም ነው፣ የነዋሪ ነገር ምስል ነው ማለት ፍጹም ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛ የሳይኮሎጂ ፓቶሎጂ ነው ።

ስለሆነም ስለ አንድ የማሀበረ ሰብ ርዕዮተ ዓለም ወይም ምስለ አለም፣ ወይም ስዕለ አለም ስናወራ ያ ምስል ህያው ከነበረ ፣ ከኖረ ፣ ሊኖር ከሚችል ማህበራዊ ስርዓት የተቀዳ ምስል እንጂ ከሰው አይምሮ የተፈበረከ ኢሉዝን ፣ ሚራክል ወይም ታምር የሚቀዳ አይደለም ። ስለዚህ ነው ስለ ፖለቲካ ር ዕዮተ አለም (ምስለ አለም) ስናስብ በአለም ላይ የነበሩና ያሉ ፖለቲካ ሲስተሞችን ምሳሌዎች፣ ምስሎች የምናጠናው እንጂ ከባዶ አንጎላችን ህልምና ኢሉሽን እያየን ያንን እንደ አይዲኦሎጂ መስበክ ድንቁርና ብቻ ሳይሆን እብደት ነው።

ስለዚህ የአቶ አቢይ መደመር ርዕዮተ ዓለም አይደለም ። ከምንም ነባራዊ አገር፣ ፖለቲካ ፣ ስራዓት የተቀዳ ምስል አይደለም ፣ የምንም ስራት ስዕል አይደለም፣ የአንድ ሰው ባዶ ሃስቦች በፊደል የተጻፈ ህልምና ምናብ ነው ።መደመር የሚባል የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ ሶሺያል ርዕዮተ ዓለም፣ ምስለ ፖለቲካ፣ ርዕዮተ መንግስት በየትኛውም አገር አልኖረም ።

ኢትዮጵያ ውስጥ እከሌ የሚባሉ ምሁራን ካሉ ይህን መረን የለቀቀ ኢሉዥን መርምረው ጸሃይ ላይ ማስጣት አለባቸው ። በኢትዮጵያ ምንም ነገር የማይሰራው መደመር በተባለ የአንድ አላዋቂ መሪ ጭለማ ውስጥ አገር ስለሚታመስ ነው ።

በአለም ላይ ያሉት የኢኮኖሚና ፖለቲካ ስርዓት አይነቶች ይታወቃሉ ። መደምር የሚባል ግን የለም !
Horus wrote:
27 Oct 2025, 22:10
… የራሴ ማኒፌስቶ ያለኝ የነቃ የፖለቲካ እንሰሳ ነኝ።
ቃላት በመፍለጥ ሰዉ ኣላሰለችም ብለህ ጀምረህ ሀሳብ ማለት ኣይድያ ማለትን ስንት ቦታ ፈልጠህ ፈላልጠህ ኣንባቢህን ኣሰለቸህ።

ሀሳብ በለዉ ኣይድያ ከኣንድ ሰዉ ኣዕምሮ ሊመነጭ ይችላል። ኣልያም የሌላ ሰዉ ኣዕምሮ ያመነጨዉን ሌሎች ኣዕምሮዎች መገንዘብ ይችላሉ።

የነቃ የፖለትካ እንስሳ ነኝ ስትል መንቃትህ ኣዕምሮህ ካመነጨዉ ሀሳብ ወይም ኣይድያ ነዉ ወይስ የሌላ ሰዉ ኣዕምሮ ያመነጨዉን ሀሳብ ወይም ኣይድያ ከመገንዘብ ነዉ?

Abere
Senior Member
Posts: 14740
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አቢይ አህመድ ርዕዮተ ዓለም ምን እንደ ሆነ አያውቅም

Post by Abere » 28 Oct 2025, 10:48

eden,

Did you experience a temporary glitch? Someone full of contradictions - just laying down a bunch of words like bricks -doesn’t necessarily build on the foundation of truth. Huresa is one of the most inconsistent people I have seen, with no meaningful ideas or coherent concepts formed in his mind.
የኢህአፓ ሰዎች እኮ ማነብነብ እውቀታቸው ምላሳቸው ላይ እንጅ አንጎላቸው ላይ የለም። ከገሀዱ አለም ጋር ያልተዛመደ፤ በግብር ላይ ያላተኮረ መነባነብ ውስጥ የነበረ የቅዠት ትውልድ ነው - ኢትዮጵያን ገደል ያስገባ።

ሁሬሳን ሙልጭ አድርገሽ አጥበሽ ብታጥኝው ንጹህ ሰው አይሸትም። ኪስ ማውለቅ እድገቱ፤ መቀደድ ችሎታው ነው። ሊቀ መርካቶ-ኪስ አውላቂ

Post Reply