Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7188
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ኣንድ የተስፋዬ ገብረዓብ ትንቢት ሲገለጥ

Post by Naga Tuma » 29 Sep 2025, 18:59

ተስፋዬ ገብረዓብ ካሳተማቸዉ መጽሓፎች ዉስጥ ኣንዱ ኣጋጥሞኝ ኣንብቤ ነበር።

መጽሓፉ ዉስጥ ከጻፋቸዉ ዉስጥ ቃል በቃል ባይሆንም የሚከተለዉን ኣስታዉሳለሁ።

ዉስጡ ያለዉን ሳታዉቁ
ዱዳ ነዉ ኣይሰማም ብላችሁ
ፈራሁላችሁ

ወደ ኋላ ተመልሼ ታሪክን ሳስተዉል ሰዉ ሰራሽ ይሁን መለኮታዊ ስለ ስዉር ስፌት የተባለዉ ተንብዮ ወይም ኣስተንብዮት ይሁን?

ሰዉ ሰራሽ ይሁን መለኮታዊ ስዉር ስፌት የተባለዉ የተሰፋዉ ኢሳያስ አፍወርቂ፣ መለስ ዜናዊ፣ እና ዮሓንስ ለታ ከኢትዮጵያ የነፃነት ድርጅቶች ኣሉን ይሉ የነበረ ዘመን ነዉ።

እኔ በዛን ዘመን እንደገባኝ ከሆነ ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ሃገርነቷ ኣይፍረስ ማለት እንጂ ከሶስታቸዉም ጋር ሌላ ጸብ የነበራት ኣይመስለኝ። የእኔ ግንዛቤ ስህተት ከሆነ ከእኔ የበለጠ የታሪኩ ዕዉቀት ያላቸዉ ልያርሙኝ ይችላሉ።

ከዛ ዘመን በኋላ ተስፋዬ ገንረዓብ ይዘራ የነበረዉን የቻልኩትን ያህል ዕዉነት ለብቻዬ እየለፋሁ ለማህበረሰቡ ለማስገንዘብ ሞክሬኣለሁ።

በዚህ ዘመን ብዙዎች አፍ ሞልተዉ ኢትዮጵያ ማለት ሲጀምሩ እነ ሆረስ እንደ ተስፋዬ ገንረዓብ ቅጥረኞች ሆነዉ እሱ ሲዘራ የነበረዉ ኮትኳቶች ሆኑ?