Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6757
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የእግዝኣብሔር አሰራር እግዝኣብሔር ባዩ አበረን እራሱን የታሪክ ምስክር ኣድርጎ ኣላሳፈረዉም?

Post by Naga Tuma » 27 Sep 2025, 18:59

እኔ ለአካዳሚ እንጂ ለፖለትካ ዝንባሌ ያልነበረኝ ተማሪ ነበርኩ።

ህወሓት ሃገር ኣቋርጦ፣ ከጎጃም ወደ ወለጋ ተሻግሮ፣ አዲስ አበባ ሳይደርስ በፊት መቃወም የጀመርኩኝ ተማሪ ነበርኩኝ።

አሜሪካ ደርሼ ትምህርት እየተከታተልኩኝ ግዜ ሳገኝ ደጃ ኒዉስ ላይ ይካሄድ የነበረን የኢትዮጵያዊያን ንትርክ እያነበብኩኝ ከልጅነቴ ጀምሮ በደንብ ያላጠናሁኝን ታሪክም እያስተዋልኩ የኢትዮጵያ ፖለትካ መቃወም ሆነ መደገፍ ለእኔ ኣይዴለም ብዬ ነበር።

ከዛ በኋላ ኣንድ ቀን ዶክተር አለማየሁ ብሩ የተባለ የሆሮ ጉዱሩ ሰዉ ከዛ በፊት ሰምቼ የማላዉቀን ታሪክ ኣንድ መድረክ ዉስጥ ጽፎ በኣጋጣሚ ኣነበብኩኝ።

ኣስቦ የመጻፍ ችሎታ ያለዉ ነዉ ብዬ እያሰብኩ የእሱ ጽሑፎች ከማነባቸዉ ዉስጥ ነበሩ።

በአጋጣሚ ያነበብኩኝ ታሪክ ስለ ኢትዮጵያ ፖለትካ ወደ ሀሳብ መስጠት መለሰኝ።

ዶክተር አለማየሁ ብሩ ስለጻፈዉ ከዛ በፊት ሰምቼ የማላዉቀዉን ታሪክ ከብዙ ዓመታት በኋላ አበረ እዚህ ፎረም ላይ ጽፎ የእሱንም ጽሑፍ በአጋጣሚ ኣነበብኩኝ።

የአበረ ጽሑፍ ዶክተር አለማየሁ ብሩ ከብዙ ዓመታት በፊት ስለጻፈዉ ምስክር ሆነ ማለት ነዉ።

አበረ እና እኔ በአካል ኣንተዋወቅም። ዶክተር አለማየሁ ብሩ ኣንድ ቀን እንቆቅልሽ በሚመስል ሁኔታ ሀዘን ላይ ተገናኘን።

በአካል ሳንገናኝ ከበርካታ ዓመታት በፊት የሃገር ሰዉ ቤት ከቤተሰብ ጋር ተጋብዘን ሄድን።

ተጋባዦች ሲወያዩ ስለ ኢትዮጵያ የቅርብ ግዜ ታሪክ ኣንድ ስህተት ሲደጋገም ሰማሁ። በዕድሜ የገፉ ተጋባዥ ዘመድ ስለነበሩ ይታዘቡኛል ብዬ ከመናገር እየተቆጠብኩ ኣንድ ኣጭር የታሪክ ጥያቄ ጠየኩኝ።

የዶክተሬት ድግሪ የነበረዉ ባለቤት ጥያቄዉን ሰምቶ ፊቱን ከእኔ ስያዞር ትምህርት ቤት ሄዶ መማሩን የማለዉቅ ሸምገል ያለ ሰዉ ጥያቄዉ ገብቶት ወደ ተወያዮቹ ዞሮ ኣስተዉሉ ማለቱን ሰማሁኝ።

ከዛ በኋላ የታሪክ ዉይይቱ መቀጠሉን ኣላስታዉስም።

በርካታ ዓመታት ኣልፈዉ በቁም ነገር ስለ ሳይንስ ስራ ታሪካዊ ፎቶ ይቀመጥልኝ ብዬ የሃገሬን ሰዉ ብደዉልለት ችላ ብሎኝ ያሰብኩትን ፎቶዎች ለብቻዬ ሄጄ ኣነሳሁዋቸዉ።

ተጋብዘን የታሪክ ጥያቄ ከጠየኩኝ በኋላ ስለ ኢትዮጵያ ፖለትካ ዉሎዉ ባላዉቅም ከብዙ ዓመታት በኋላ በድንገት ማረፉን ሰምቼ በጣም ደንግጬ ኣዘንኩኝ። የፖለትካ ዉሎዉ ዉስጥ ተሳስቶ ይሁን ኣሳስተዉት ይሁን ማወቅ ኣልቻልኩም።

የእሱ ማረፍ ከእኔ በላይ የከነከነዉ ሰዉ ኣለ ማለት ባልችልም እኔን የከነከነኝ ለብቻ ነዉ።

ምክንያቱም የእኔ ጥያቄ ገብቶት ቢሆን ኖሮ ይተርፍ ነበር ብዬ ከልቤ ኣስባለሁ።

ይባስ ብሎ ሀዘን ላይ የዉሽት ሙሾ መቺ የመሰለኝን ያስተዋልኩ መስሎኝ ጀግነቱ አከነት ዴመ ብል በቅጽበት ደንግጦ ኩኖ ብሎ ፊቱን በፍጥነት ወደ ሌሎች ኣዞረ። በምንም ምክንያት ይሁን ያረፈዉ ክብሩን ጠብቆ ስለሄደ ጀግነቱ አከነት ዴመ ኣስብሎኛል።

የቤተሰብ እና የታዳጊ ልጆች አባት የነበረዉ ኢትዮጵያዊ በባዕድ ሃገር የቦረነ ሰዉ ይሁን የጉሙዝ ሰዉ ክርስትያን ነኝ በሚል ኣዝካሪነት፣ በቢዛሞዎች ሙሾ መቺነት፣ በኣዕምሮ ሳይሆን በብዕር ለቅላቂነት፣ ከዐይኖቻቸዉ ዕንባ ያላነሳቸዉ ጆሮዎች ጠባቦች ወይም የማሰላሰል ኣዕምሮ የምያንሳቸዉ ወይም ጀግነቱ አከነት ዴመ ሲባል ኩኖ ያለን ምን ማለትህ ነዉ የማለት ወኔ ያነሳቸዉ መንጋ ተሸኝቶ ባዕድ ሃገር ኣረፈ። ታሪኩ ይሄ ነዉ ተባለ።

ኣሁንም ድረስ የረፈዉም ሆነ ዶክተር አለማየሁ ብሩ የቦረና ሰዎች መሆናቸዉን ኣላዉቅም።

ያረፈዉ ምናልባትም ገበሮዎች ከተባሉት ይሆን የሚል ግምት ኣለኝ።

ዶክተር አለማየሁ ብሩ እኔ ያላወኩኝን ታሪክ እንዴት ልያዉቅ ቻለ እንቆቅልሽ ሆኖብኝ ከሰነበተ በኋላ ወለጋ ዉስጥ ቢዛሞ የሚባል ማህበረሰብ መኖሩን ከዚህ ዘመን በፊት ሰምቼ የማላዉቀዉን ሌላ ታሪክ ኣነበብክኝ።

ሁለቱም ሰዎች ከቦረና ጎሳ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የኢትዮጵያ ጎሳዎችም የተወለዱ ከሆነ የሁለቱም ሰዎች ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ሳይሆን እንደ ቦረና ጎሳ ብቻ መሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ እና ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሁሉም ኢትዮጵያዊያንን የኣዕምሮ ብክነት ኣመልካች ኣይዴለም?

እግዝኣብሔር ባዩ አበረን እንዴት ነዉ እግዝኣብሔር ዶክተር አለማየሁ ብሩ ለጻፈዉ ታሪክ ምስክር ኣድርጎ በሰፊ ሃገር ዉስጥ የአዲስ አበባ እና የወለጋ ቆጣሪ ኣድርጎ የምያዋርደዉ?

ይህ ታሪክ ዉስጥ መለኮታዊ አሰራር ዬለም የሚልን ሰዉ ማግኘት ይቻላል?