ጄነራል ሰዓረ መኮንን እንዴት እንደ ተገደሉ እና ማን እንደ ገደላቸው ፍንትው አድርጎ የሚያጋልጥ የምርመራ ዘገባ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ።
ጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ብ/ጄነራል ገዛኢ አበራን በተቀመጡበት በጥይት የደበደባቸው ማን እንደሆነ እና ለምን እንደ ተገደሉ በስፋት የሚዳስሰው ይህ የምርመራ ዘገባ የፍርድ ቤት ውሎ፣ የምስክሮችን ቃል፣ የፎረንሲክ ምርመራ ውጤት፣ እና በወቅቱ የነበሩ ሰዎችን ቃለመጠይቅ አድርጎ የተሰነደ የምርመራ ዘገባ መጽሐፍ ነው።
ጄነራሎቹ በተገደሉበት ዕለት የግቢውን ካሜራ ሲከታተል የነበረው ጠባቂ ወታደር ዛሬ የብርሀኑ ጁላ የግል ጠባቂ ሲሆን ቦሌ ክፍለ ከተማ መኖሪያ ቤት በስጦታ ተበርክቶለታል።
የምርመራ ስራውን ለማዘጋጀት ሁለት ዓመት እንደ ፈጀበት ተገልጿል። ጋዜጠኛው ኢትዮጵያ ውስጥ በመሆኑ ለጊዜው ማንነቱ እንዳልተገለፀም ታውቋል።
መጽሐፉን በአማዞን ያገኙታል
መጽሐፉን የሚያገኙበት ሊንክ
https://a.co/d/jkk5fH0