የሰሜን ወሎ ዞን አመራሮች ወልድያ ከተማ አናድርም በሚል ምሽቱን ወደ ሐራና ጭፍራ መጓዛቸው ተሰምቷል።
አመራሮቹ፡ ዛሬ በፋኖ ከመማረክ የተረፉ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ወታደሮችንና የጦር መሣሪያዎችን ከእያሉበት በመለቃቀም ታጅበው ነው የተጓዙት ተብሏል።
አመራሮቹ፡ ፋኖ ዛሬ አዳሩን ወልድያ ከተማን ሊቆጣጠር ይችላል በሚል ስጋት ነው ከተማዋን ለቀው እየወጡ የሚገኙት ሲሉ ምንጮቻችን ገልፀዋል።
በተያዘ ዜና!
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌ/ጄነራል አሰፋ ቸኮል የቁም እስረኛ መደረጉ ተሰምቷል።
ሌተናል ጄነራሉ ከሳምታት በፊት በአፋር ሰመራ ከተማ ምክትል ኢታማዦር ሹሙ በተገኙበት የግምገማ መድረክ ላይ ከፍተኛ የሆነ ትችት አስተናግዶ እንደነበር መረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ አይዘነጋም።
በግምገማ መድረኩ ነሐሴ 03/2017 ዓ/ም ራያ ቆቦ ላይ በፋኖ ስለተማረከው ዙ23 ጉዳይ ተነስቶ ኢታማዦር ሹሙ አበባው ታደሰ፡ ፀያፍ ቃላቶችን በመጠቀም ጭምር አሰፋ ቸኮልን በስድብ እንደወረፉት ነው በዘገባችን አካትተን የነበረው።
በዛሬው ውጊያ ደግሞ በፋኖ የተገደለውንና የተማረከውን የዕዙን ጦር መሣሪያ እና ሰራዊት ውለድ ተብሎ ምሽቱን የቁም እስረኛ ተደርጓል ሲሉ የመረጃ ምንጮቻችን ገልፀዋል።
ሌ/ጄነራሉን የሚዘውሩት በስሩ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ የበታች አመራሮች "ማዕረግህን በሳንጃ ቆርጠን እንጥልልሀለን" በሚል ቃል በቃል እንደተናገሩት ነው የተሰማው።
"አሰፋ ቸኮል ምሽቱን የቁም እስረኛ ተደርጓል፡ ነገ ወደ አዲስ አበባ ይወሰዳል እዛ ከደረሰ በኋላ ወይ ማዕረጉን ተነጥቆ ይታሰራል አልያም ሊረሸን ይችላል" ሲሉ ነው መረጃውን ያደረሱን ምንጮቻችን የገለፁት።
አፋብሃ እንደዘገበው፣
https://www.facebook.com/share/p/1CoV1K ... tid=wwXIfr