Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

sesame
Member+
Posts: 7902
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: Sesame: እኔ በጣም ትልቅ ፌሽታ ላይ ነኝ! አትረብሽ !!!

Post by sesame » 24 Sep 2025, 01:38

Horsey,

You are pathetic! What is there to celebrate? የኢትዮጵያ ህዝብኮ በዓል ባይመጣ እያለ ነው።

Finfinne Press
1h

ከነዳጅ እስከ ስንዴ .. ከዘይት እስከ ሽንኩርት በአጠቃላይ መሰረታዊ ፍጆታዎችን ሳይቀር በውጭ ምንዛሪ ገዝታ የምታስገባ ሀገር ላይ እየኖረ የዶላር ምንዛሬ ጭማሪ ልዩነት የኢኮኖሚ ሁኔታውን አያሳይም ብሎ ይከራከርሃል 😁 ...
ቻይና ፣ ጃፓን ፣ ህንድ የገንዘባቸውን ምንዛሬ የከሰከሱት ሀገራዊ ምርታቸውን ለመሸጥ ፣ ገበያ ለማግኘትና ፣ በውጭ ንግድ ተፎካካሪ ለመሆን እንጂ ኢኮኖሚያቸው ስለወደቀ አይደለም ...

ኢትዮጵያ ግን ገንዘቧን የከሰከሰችው ሽርፍራፊ የውጭ ምንዛሬ አግኝታ ከመሰረታዊ ፍጆታዎች ጀምሮ ሁሉንም ለመሸመት ነው። ብራችን ተከስክሶ በተገኘው የውጭ ምንዛሪ ተገዝቶ የገባው ምርቶች ደግሞ የዋጋ ንረቱን ያባብሰዋል።

እንደ ሱሰኛ ከገቢዋ ይልቅ ወጪዋ የበዛው ኢትዮጵያ በየእለቱ የዋጋ ንረት ይተኮሳል ፣ የብር የመግዛት አቅም እየተዳከመ ይመጣል ፣ የዜጎችን ሰርቶ የመለወጥ ተስፋ አቀጭጮ ምግብ ላይ ብቻ እንዲያተክሩ ያደርጋል ...

መጪው ጊዜ ደግሞ ይበልጥ አስፈሪ ነው። ለውጭ ገበያ ከግብርና ምርት ውጪ የማታቀርበው ኢትዮጵያ ብሯን መከስከሷ ሳያንስ የጥቁር ገበያው የውጭ ምንዛሪ ገበያውን እየዘወረ ላይ ይሰቅለዋል። የዋጋ ንረቱ ከቁጥጥር ውጪ መውጣቱ አይቀርም።

አፄ ሀይለስላሴ ፣ ደርግ ፣ ኢህአዴግ በዚህ ደረጃ የሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ አልተጫወቱም። በዚህ መጠን ብራችንን አዳክመው የኑሮ ውድነት አላባባሱም። ወጪና ገቢያችን ይሄን ያህል ልዩነቶች አልነበሩትም። ኢኮኖሚው የተረጋጋ ነበር።
#ብልፄ ግን .. በዘመናት የከፋ ስርዓት ነው !!

https://www.facebook.com/share/p/1JrLR9byQZ/

Odie
Member+
Posts: 6013
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: Sesame: እኔ በጣም ትልቅ ፌሽታ ላይ ነኝ! አትረብሽ !!!

Post by Odie » 24 Sep 2025, 07:03

Horus wrote:
24 Sep 2025, 00:05
እውነት አይመስልም ሲያካብድ :lol: :lol:

Abere
Senior Member
Posts: 14743
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Sesame: እኔ በጣም ትልቅ ፌሽታ ላይ ነኝ! አትረብሽ !!!

Post by Abere » 24 Sep 2025, 14:29

አዎ! በጣም ፌሽታ ለይ ነህ እንጅ :lol: ። ግን ጉራጌኛ መጨፈር ትችላለህ? አይመስለኝም። :mrgreen: ለማንኛውም የወደፊቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ችሎታ ተመልከት።

Post Reply