Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6757
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ግርማ ብሩ ማነዉ?

Post by Naga Tuma » 06 Sep 2025, 16:21

ኣንድ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት መሪዎች ዉስጥ የላቀ ኣዕምሮ የነበራቸዉ ሁለት ሰዎች መለስ ዜናዊ እና ግርማ ብሩ ናቸዉ ተብለዉ ነበር። ይህን ያለዉ ሃገር ዉስጥ ሲኖር የነበረ ኣንድ ሰዉ ነዉ።

እኔ ግርማ ብሩ ሲናገርም ሆነ ቃለመጠይቅ ሲደረግለት ሰምቼ ስለማላዉቅ ስለ እሱ የራሴ ግምት ዬለኝም።

የላቀ ኣዕምሮ የነበራቸዉ ሁለቱ ግለሰቦች ናቸዉ ከተባሉ በኋላ ጀምሮ ያለኝ ጥያቄ የኦሮምያ ክልል ርዕሰ ከተማ ወደ አዳማ ይዛወር የተባለዉ ዉሳኔ 96 ዉስጥ ግርማ ብሩ ምን ያህል ሚና እንደነበረዉ ነዉ።

መለስ ዜናዊ እና ግርማ ብሩ ኣብረዉ ተወያይተዉ የወሰኑት ነበር ወይስ ግርማ ብሩ ለመለስ ዜናዊ ስጋት ሆኖበት መለስ ዜናዊ ግርማ ብሩን ሳያማክር ኣስወስኖ ግርማ ብሩ እሺ ብሎ የተቀበለዉ ነበር?

ይህን ታሪካዊ ጥያቄ በትክክል መመለስ የሚችሉት ሁለቱ ብቻ ናቸዉ።

ኣንዱ በህይወት ዬለም። ሌላዉ በህይወት ስላለ የዚህን ታሪካዊ ጥያቄ መልሱን ለታሪክ ኣስቀምጦት ይሆን?

Naga Tuma
Member+
Posts: 6757
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግርማ ብሩ ማነዉ?

Post by Naga Tuma » 23 Sep 2025, 13:18

ከዉሳኔ 96 በኋላ ዶክተር መረራ ጉድና አዲስ አበባ ዉስጥ ትልቅ የተቋዉሞ ሰልፍ መርቶ ነበር የሚል ዜና ኢንድያን ኦሽን መዘገቡን ኣስታዉሳለሁ።

በዚህ ግዜ የፖለትካ ሳይንስ ፕሮፌሰሩ የዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያንን ዉይይት ምን ያህል እንደሚከታተል ኣላዉቅም።

የሚከታተል ከሆነ በዛ ዉሳኔ ዙርያ የነበረዉን የመንግስትም ሆነ የፖለትካ መሪዎች እንቅስቃሴን ለታሪክ ዘግቦ ይሆን?

በእኔ አስተሳሰብ ዉሳኔ 96 እና ምርጫ 97 የሃገር ታሪክ ዉስጥ ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል።

የዳያስፖረ ኢትዮጵያዊያንን ዉይይት የምትከታተል ከሆነ ኢትዮጵያ እያለሁ በሶስት ነጥብ አረት ያለፍኩኝ ነኝ ብለህ ስትመጻደቅ ታዝቤህ ነበር።

ከምርጫ 97 በኋላ የምኖርበት አከባቢ መጣህ ሲባል እንተርኔት ላይ ያስተዋልኩኝን መጣጥፎች ለቃቅሜ ይጠቅሙሃል ብዬ መንገድ ተጉዤ ስመጣ በፍጥነት ፎቶ እንነሳ ስትል ቅንነት ስጋት መሆኑን ታዝቤህ ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ።

ኣሁን ደግሞ ይህን ሁሉ ግዜ የኢትዮጵያ ፖለትካ ዉስጥ ኖረህ በእኔ ሳይሆን በሌላ ግለሰብ ሚዛን ድሮ ሳይሆን ዘንድሮ ከሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መሪዎች ቁጥር ዉስጥ የማትገባዉ ምን ተዓምር ቢኖር ነዉ?

የኦሮሞ መብት ተከራካሪ ነኝ የሚል የሌላ ግለሰብ አስተያየትን እዚህ የዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን የዉይይት መድረክ ላይ ነዉ ኣምና በኣጋጣሚ ኣንብቤ የተገረምኩኝ።

መረራ የሀመቺሳ ስምህ ይሆን?

Abere
Senior Member
Posts: 14743
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ግርማ ብሩ ማነዉ?

Post by Abere » 23 Sep 2025, 16:22

Naga Tuma,

የሰው ልጅ ምስክሩ ሥራው ብቻ ነው። ሥም ከመቃብር በላይ ይቀራል ይባላል። ግርማ ብሩ እራሱን በእራሱ ማንቆለጳጰሱ ሳይሆን የሰራው ስራ አፍ አውጥቶ ይናገራል ወይ?

የዚህ ዓመት ህዝባዊ ኢንተርኔት መረጃ እንደሚጠቁመው ከሆነ ግርማ ዶላር በማንኪያ ብር እንደ እንጀራ መጋገሪያ የባህር ዛፍ ቅጠል በጆንያእንድሆን ከፍተኛ የአእምሮ ግብዐት አበርክቷል ይባላል።
He is from the same village as Huresa/Horus/ :mrgreen:

Naga Tuma
Member+
Posts: 6757
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግርማ ብሩ ማነዉ?

Post by Naga Tuma » 24 Sep 2025, 05:12

Abere:

መለስ ዜናዊ ታምራት ላይኔን የስኳር ነጋዴ እንዳለዉ ቀልድ ነዉ ማለት ነዉ? ስለ ሁለቱም ኣላዉቅም። ስለ ግርማ ብሩ ኣንድ ቀን አጭር ወሬ ሰምቻለሁ።

ግርማ ብሩ ማን ነዉ ያልኩኝ ዋና ምክንያቱ ስለ አከባቢዉ ታሪክ የሚከተለዉ ቪድዮን በማስታወስ ነዉ።

ታሪኩ ከቦረና ተነስቶ መጀመርያ ወልሶ ስለደረሰ ሰዉ ታሪክ ነዉ። በግራኝ ዘመን መሆኑ ነዉ።

የቦረና ሰዉ ጎሳ ነዉ ወይስ ከሌላ ጎሳ ነዉ ወይስ ከሁለቱም ጎሳዎች ነዉ?

ይህ ስለ ጎሳዉ ወይም ጎሳዎቹ ለመጠየቅ ሳይሆን የጎሳ ፖለትካ ኢትዮጵያ ዉስጥ ጥያቄ ዉስጥ በገባበት ዘመን ምን ያስባል ለማለት ነዉ።


Post Reply