Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11378
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

IMF and World Bank warn of Ethiopia's $10.8 billion financial black hole - Capital: Ethiopian Newspaper

Post by sarcasm » 21 Sep 2025, 17:54

ኢትዮጵያ: በ10.8 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ክፍተት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ አስጠነቀቁ

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (የአይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ በጋራ ባወጡት አዲስ ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ በተደረጉ ማሻሻያዎች እና ድርድሮች ቢኖሩም አሁንም በከባድ ዕዳ አጣብቂኝ ውስጥ እንደምትገኝ ተጠቆመ።

ሪፖርቱ ሀገሪቱ በ2024–2028 ባለው ጊዜ ውስጥ 10.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ከፍተኛ የገንዘብ ክፍተት እንዳለባት አብራርቷል።
ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፣ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ዘላቂነት የሌለው ሲሆን ይህም በዓለም አቀፍ የገንዘብ ቀውሶች፣ የዩሮቦንድ ዕዳ ክፍያ ባለመፈጸሟ እና ከኤክስፖርት ገቢ ጋር ተመጣጣኝ ባልሆነ የዕዳ መጠን ሳቢያ ነው።

ኢትዮጵያ በታህሳስ 2023 የወለድ ክፍያና በታህሳስ 2024 የ 1.1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮቦንድ ዕዳ ክፍያ መክፈል ያልቻለች ሲሆን፣ ምንም እንኳን ከኦፊሴላዊ አበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር በመጋቢት 2025 የመርህ ስምምነት ላይ ብትደርስም፣ ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ እንደሆነ ተጠቅሷል።

የዕዳ ዘላቂነትን ለመመለስ ኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ አያያዝ፣ የአይኤምኤፍ ድጋፍ እና ከልማት አጋሮች የሚገኝ ፋይናንስን ማጣመር ይኖርባታል። ፕሮግራሙ እኤአ ከ 2024 ጀምሮ ለ4 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ 10.8 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ክፍተት እንዳለ አስቀምጧል።
ይህ ክፍተት ከ3.4 ቢሊዮን ዶላር ከአይኤምኤፍ፣ 3.8 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ የሚገኝ የበጀት ድጋፍ፣ እና 3.6 ቢሊዮን ዶላር ከሁለትዮሽ እና የንግድ አበዳሪዎች የሚገኝ የዕዳ እፎይታ እንደሚሸፈን ይጠበቃል።

አይኤምኤፍ በ2024/25 የሀገሪቷ የጂዲፒ ዕድገት 7.2% እንደሚሆንና የመካከለኛ ጊዜ ትንበያውም ወደ 7.5–8% እንደሚያድግ ገልጿል።
የአይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ሪፖርት አገሪቱ ከገበያ ውጭ የሆኑ ፋይናንስን በማስወገድ፣ የግብር መሠረትን በማስፋት እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን አስተዳደር በማጠናከር ላይ እንድትሰራ መክሯል።

ሆኖም የዕዳ መልሶ ማዋቀር መዘግየቶች፣ የፀጥታ ችግሮች እና ዓለም አቀፍ የሸቀጦች ዋጋዎች ሊያስከትሉ የሚችሉ ተግዳሮቶች እንደ ዋና ስጋቶች ተጠቅሰዋል።
Please wait, video is loading...