Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39826
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጎሳ ብሄረተኝነት ፖለቲካ ገና በሽሉ የወረደ የጂሎች መታከት ነው! ለምን?

Post by Horus » 19 Sep 2025, 11:29

በኢትዮፕያ ውስጥ 4 ታሪካዊ ክስተቶች እየገነኑ ነው ። ሌሎችም መኖራቸው እንዳለ ሆኖ ...

አንድ፣ ETHNICITY FATIGUE
ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ጎሳ ሆያ ሆዬ ፣ የጎሳ ማንገራገር ፣ የጎሳ ማለቃቀስ ፣ የጎሳ ትርክት ፣ የጎሳ ጥያቄ ፣ የብሄር ጥያቄ ቋቅ ያለው ነገር የለም!! ዛሬ በኢትጵያ ቅንጣት ታክል አዳማጭ ያጣ የቡዶንች ማለቃቀስ የጎሳ ብሎም የብሄር ጥያቄ ነው። በአንድ ቃል በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ግዜው ያበቃ ፣ ታሪኩ የተዘጋና ከአዎንታዊነት ወደ አፍራሽነት ተለውጦ የተጠላ የብሄር ጥያቄ ነው ።

ሁለት፣ ETHNIC LIBERATION FRONT FATIGUE
ዛሬ ላይ እንደ ሉሲ፣ እንደ ቅርሰ አጽም የሞተው የብሄር ጥያቄ ቅሪትና ተረፈ ሞት የሆኑ 'የጎሳ ነጻ አውጪ ግምባሮች ' እዚም እዛም ሕይወት አልባ ግን በስምና በቲክ ቶክ የሚከሰቱ ከሱማሌ ነጻ አውጪ እስከ ሸኔ ፣ ካማራ ነጻ አውጪ ፋኖ እስከ ትግሬ ነጻ አውጪ ትህነግ አሉ ። ነገር ግ ን እነዚህ በየዋሻውና በረሃው ተዘርተው የሚያግቱ ፣ የሚዘርፉ ፣ ሰላማዊ ገበሬን ነጋዴን አሮጊትን በመዝረፍ የሚኖሩ ዘርፎ አደር ሽፍቶች አይደለም ሕዝባዊ የነጻነት ንቅናቄ ሊሆኑ በመላው ሕዝቡ ዘንድ የተረሱና የተጠሉ ቡድኖች ሆነዋል ። ይህ እጅግ እጅግ ታሪካዊ ክስተት ነው።

የጎሳ ነጻ አውጪ ተብዬ ሽፍቶች እንዲያውም በሕዝብ የተጠሉ ማህባርዊ ካንሰር ነቀርሳ ሆነዋል ።

ሶስተኛ፣ RESURGENCE OF NATIONAL UNITY
ዛሬ የብሄር ጥያቄ መሞትና የብሄር ነጻ አውጪነት መጠየፍ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊያን ሆነ ብለው ፣ በእቅድ ፣ በኢንቴንሽ ፣ በአላማ ፣ በራዕይ የኢትዮጵያን አገራዊና ብሄራዊ አንድነት ለመገምባት ከዳር እስከ ዳር በልዩ ልዩ መንገድ እየተጉ ነው! ይህ አዲሱ ታሪካዊ ክስተት ነው! የዘመኑ ፈሊጥ ፣ የዘመኑ ወግ፣ የዘመኑ ፋሽን፣ የዘምኑ ማህበራዊ ትሬንድ ወይም ዝማሜ ሃገራዊ አንድነት እንጂ ጎሳዊ ክፍፍል አይደለም! ይህ ሌላው ግዙፉ ታሪካዊ ክስተት ነው ።

አራተኛ፣ RESURGENCE OF A NEW ETHIOPIAN GENERATION
ይህ አዲስ ትውልድ ከደርግ እስከ ወያኔ የነበረውን የጎሳ ብሄረተኛን ትውልድ በተቃራኒ የቆመ እና ኢትዮያን መልሶ አንድ የሚያደርግ ንቃተ ህሊና ወይም ሶቺያል ኮንሺየነስ እያጠነጠነ ያለ ወጣት ትውልድ ነው ። የዚህ ትውልድ መገለጫው ቴክኖሎጂ ፣ አሪቲፊሻል ኢንተለጀንስና ዲጂታል ሕይወት እንጂ የጎሳ ጥያቄና በረሃ ወርዶ አፈር ላይ ቅማል መቅመል አይደለም ። በሌላ አባባል የጎሳ ትያቄ በዲጂታል አለም ተገድሎ ተቀብሯል ።




Post Reply