Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Post
by Za-Ilmaknun » 16 Sep 2025, 12:28
በጥቅለላ እና መስፋፋት አጀንዳ የተጠመደው የ ኦህዴድ አገዛዝ ፣ ሶዶ ጉራጌን በቀላሉ እንደጠቀለለው ሁሉ፣ ሶማሌዎችን ቢሞክር ጊዜ፣ ሰፊ አፍንጫውን ነስር በነስር እያረጉለት ነው፣፣ በቅርቡ የ ሶማሌ ክልል መንግስት ክልሉን በ አዲስ ሁኔታ በማዋቀር ፣ ይመቸኛል ያለውን አሰራር በመዘርጋቱ፣ የተቆጡት የ አብዲሳ ልጅ ሽሜ ፣ ከጌታቸው አብዮት አህመድ የተሰጣቸውን የወረራ እቅድ ለማሳካት ቢከጅሉም፣ ሶማሌዉ የሚቀመስ አልሆነም፣፣
ከ ቦረና እስከ ባቢሌ በተዘረጋው ሰፊ ቀጠና የ ሶማሌ ክልል ልዪ ሃይል ክልሉን ከተስፋፊ እና ጠቅላዮች እየተከላከለ በለስ የቀናው ሲሆን፣ መከላከያ ተብዬው መንጋ በ አማራ ፋኖ ተወጥሮ በመያዙ፣ ለ ኦህዴድ ልዪ ሃይል ሊደርስለት አልቻለም፣፣
በ አረብ ኢሚሬትስ ውትወታ እና ዳረጎት አቅራቢነት ኤርትራን እወራለሁ የሚለው ፣ ዝባዝንኬ በገጠመው አውደ ዉጊያ በሙሉ እየተዝረከረከ ከመፈርጠጥ እና እጁን አንጨፍሮ ከመበርከክ ሌላ ፋይዳ እንደሌለው እየተመለከትን ነው፣፣ እነ ኮሪደሩ በልፈፋ እና በሬ ወለደ ወሬ ደግፈው ሊያቆሙት የሚተጉለት መንግስታቸው፣ በየቦታው በዚህ መልኩ ተዋርዶ መፈርከሱ ፣ የዘመናችን ታላቅ መሳለቂያ እንዲሆን አድርጎታል