Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6758
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ራጂ ፊ ራጁ፣ ነቢ ፊ ነብይ

Post by Naga Tuma » 16 Sep 2025, 04:21

ራጂ ማለት ተዓምር እንደማለት ይመስለኛል።

ራጁ ማለት ትንቢት መናገር ማለት ይመስለኛል። የወደ ፊት ክስተትን በትክክል መገመት መቻልም እንደ ተዓምር የሚታይ ነዉ። ትንቢቱ ከተከሰተ ማለት ነዉ።

ራጂ ሆነ ራጁ እጅግ ጥንታዊ ቃላት መሆን ኣለባቸዉ። ምክንያቱም ሕንዶች ጭምር ያልረሱዋቸዉ ናቸዉ።

ነብይ ማለት የተለመደ ቃል ነዉ።

ነቢ ባህል ዉስጥ የሚታወቅ እና የሚከበር ነበር። ከፋሲካ በኋላ ቤተሰብ ተሰባስበዉ የምያከብሩት ባህላዊ በዓል ነዉ።

ነቢ እና ነብይ ለምን የሚመሳሰሉ ቃላት እንደሆኑ ኣላጠናሁም።

ራጂ እና ነቢ ከጥንት ግዜ ጀምረዉ የሚታወቁ እና ዕዉነት ያላቸዉ ከሆነ በሰፊዉ ኣለመታወቃቸዉን እንዴት ነዉ ማብራራት የሚቻለዉ?

ኣሳማኝ ተዓምራት ከተከሰቱ እና እስከ ኣሁን የተጻፉት መጽሓፎች ተዓምሮቹን ማብራራት ካልቻሉ ምን ማድረግ ይቻላል?

ኣዲስ የተዓምሮችን መጽሓፍ መጻፍ ያስፈልጋል ማለት ነዉ?