Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6768
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ፥

Post by Naga Tuma » 10 Sep 2025, 13:48

ሬይነሳንስ ማለት ቃሉ የፈረንሳይ ቢሆንም ታሪካዊ ገድሉ ከሁሉም በላይ የጣልያን ነዉ። ለጣልያን ቅዱስ የሆነ ታሪክ ነዉ።

ለጣልያን ሬይነሳንስ ማለት ኢትዮጵያ ኣለኝ ከምትለዉ አደዋ ገድል ሺህ ግዜ በላይ የሚበልጥ ነዉ።

ስለ ሁለቱ ታሪኮች በጥልቅ ማወቅ ብቻ የኢትዮጵያ ሬይነሳንስ ማለት ምን ማለት ነዉ ብሎ ህጻን ልጅ መጠየቅ ይችላል። የጣልያንን ቅዱስ ታሪክ የኢትዮጵያ ስም ላይ መለጠፍ ምን ማለት እንደሆነ ብዙ ማሰላሰል ኣያስፈልገዉም።

ይህ ታሪካዊ እና ዘላለማዊ ስህተት ነዉ የማይል ኣዕምሮ በዐለም ዉስጥ ማግኘት ይቻላል?

ጣልያናዊዉ ወንድ ልጄ እዚህ ኣለ ነዉ ያለዉ?

ፍርዱን ኣዕምሮ ላላችሁ ሁሉ እተዋለሁ።

ይህን ታሪካዊ እና ዘላለማዊ ስህተትን በቀላሉ ማረም ይቻላል። ይህም መለኮታዊ አሰራር ያለበት መሆኑን ኣላዉቅም።

የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ እና ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ እያልኩ ስጽፍ የሰነበትኩኝ ያለ ምክንያት ኣይዴለም።

የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ የጣልያን ብሎም የአዉሮፓ ሲሆን ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የጥንት ኢትዮጵያ እና የጥንት ግብጥ የሚሆን ነዉ ለማለት ነዉ።

እዉነታዉ ሁለቱም ሬይነሳንሶች እየሱስ ሰዉ ነበረ ከሚለዉ ድምዳሜ ይጀምራሉ። ሁለቱም ሬይነሳንሶች እየሱስ ነብይ ኣልነበረም ኣይሉም። ሁለቱም ሬይነሳንሶች እግዝኣብሔር ዬለምም ኣይሉም።

ሀይማኖት ለሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ ስያስተምር የኖረዉን የሚጻረር ዕዉቀት ይዘዉ የተነሱት እጅግ ምጡቅ ኣዕምሮ የነበራቸዉ የሬይነሳንስ ሰዎች ተባሉ። ዕዉቀቱን ማግኘት በቀላሉ እንደማይገኝ ኣዉቃለሁ።

የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ የጣልያን ቅዱስ ታሪክ መሆኑ ከታወቀ እና ሁለተኛዉ ሬይነሳምስ መንገድ ላይ ያለ የኢትዮጵያ ቅዱስ ታሪክ መሆኑ ከተስተዋለ ዳግማዊ የዉጫሌ ዉልም በቀላሉ መሠረዝ ወይም መቅደድ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ግራንድ ሬይነሳንስ ግድብ ሲባል ሬይነሳንስ ስንል ስለ መጀመርያዉ ሬይነሳንስ ነዉ ወይስ ስለ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ነዉ የሚለዉን ጥያቄ መመለስ ይበቃል።

ይህን ጥያቄ ወንድ ልጄ እዚህ ኣለ ያለዉን ጣልያናዊ ከመጠየቅ መጀመር ይቻላል።

መልሱ ስለ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ነዉ ከሆነ ለምንድነዉ የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ ስለ ጎደስ አቴና ታሪክን ኣጥንቶ እንደተነሳዉ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ስለ ፈረኦ አክናተን ታሪክ ኣጥንቶ የማይነሳዉ ብሎ መጠየቅ ይቻላል።

ፈረኦ አክናተን ከጎደስ አቴና አምስት መቶ ዓመታት ገደማ በፊት የኖረ እና እጅግ የበለጠ ገናና ነበር።

ስለዚህ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ከመጀመርያዉ ሬይነሳንስ በላይ እጅግ ገናና የሚሆን ነዉ።

ጣልያን የጣልያን ቅዱስ ታሪክ የሆነዉ የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ ይሀዉላችሁ ካለ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ቅዱስ ታሪክ የሚሆነዉ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ይሀዉላችሁ ማለት ትችላለች።

ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ግራንድ ነዉ ማለት ትችላለች። የጣልያንን የኢትዮጵያ ነዉ ከማለት የኢትዮጵያ ግራንድ የሆነ ዐለም አቀፍ ነዉ ማለት ትችላለች።

ይህን ማለት የምትችለዉ በኣንድ አፍ ሬይነሳንስ እና እየሱስ በማለት ሳይሆን ጣልያን ከአምስት መቶ ዓመታት ገደማ በፊት በኣንድ አፍ ሬይነሳንስ እና እየሱስ ማለት ኣይቻልም ብላ ጎደስ አቴና ብላ እንደተነሳችዉ ኢትዮጵያ በዚህ ዘመን፣ ከአምስት መቶ ዓመታት በኋላ እና ከአድዋ ድል በኋላ፣ በኣንድ አፍ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ እና እየሱስ ማለት ኣይቻልም ብላ ፈረኦ አክናተን ብላ መነሳት ያስፈልጋታል ማለት ነዉ።

ካልሆነ ጣልያን የምያወራዉን ያዉቃል፣ ኢትዮጵያ የምታወራዉን ኣታዉቅም ይሆናል። በዐለም ፊት።

ፈረኦ አክናተን፣ ከስደት በኋላ ሙሴ የሆነዉን፣ ብሎ መነሳት ማለት ኣሁን ያለዉ ባይብል የሚታረም ወይም የሚታከም ይሆናል ማለት ነዉ።

በዐለም ፊት የምያወሩትን የማያዉቁ ለዳግማዊ ዉጫሌ ዉል የምያጨበጭቡ ናቸዉ ተብሎ ከመዋረድ ፈረኦ አክናተን ብሎ በመነሳት ኣሁን ያለዉን ባይብል ማረም ወይም ማከም በዐለም ዙርያ እጅግ ያስከብራል።

ለዚህም ነዉ የጣልያን ቅዱስ ታሪክ የሆነዉን የመጀመርያዉን ሬይነሳንስ ኢትዮጵያ ላይ መለጠፍ ሳይሆን መንገድ ላይ ያለዉ የኢትዮጵያ ቅዱስ ታሪክ የሚሆነዉ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስን ለማመልከት ግራንድ ሬይነሳንስ ተብሎ ቢታረም ያልሉኝ። ከዓመታት በፊት። ጣልያናዊዉ ወንድ ልጄ እዚህ ኣለ ያለዉን ሳልሰማ በፊት።

ይህ ትንታኔዬ ለታሪክ ይቀመጥ።