Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 14770
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

መለሥ ዜናዊ ሀቅ የሸመጠጠ ወያኔ/ እንኳን ከእርሱ በፊት ስለነበሩት መሪዎች እውነት አንቆት ተናግሯል - ስለ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናነት ንትርክ። ቀኃሥ እና መንግሥ ኃ/ማርያን አምስግኗል

Post by Abere » 09 Sep 2025, 10:09



መለሥ ዜናዊ ሀቅ የሸመጠጠ ወያኔ/ሻዕብያ/ ቢሆንምከእርሱ በፊት ስለነበሩት መሪዎች እውነት አንቆት ተናግሯል - ስለ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናነት ንትርክ። ቀኃሥ እና መንግሥ ኃ/ማርያን አምስግኗል። ዐብይ አህመድ እራሱን አንቆለጳጵሶ ቁጭ። ስህተት ነው - ይህን በማድረጉ የእርሱን የምስጋና ድርሻ ህዝብ ይነፍገዋል።

ከዚህ ፎረም ላይ ሳያስብ እና ሳያጤን ለኦሮሙማ በእጅ እና በእግሩ የሚያጨበጭበው ሆረስ እራሱን ስመኜው በቀለ (ትጉህ መሀንዲስ) አድርጎ ሳይመለከት ይቀራል ብላችሁ ነው። :lol:

በእርግጥ በአባይ ወንዝ ግድብ ዙሪያ በቋሚነት መለሥ ዜናዊን የምተቸው ለምን ከእርሱ በፊት የነበሩት እንደ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የነደፉትን ፕላን (blue print) ተግባር ላይ ውሎ ነፍስ እንድኖረበት አደረገ ሳይሆ ኢትዮጵያን ቀይ ባህር እና አሰብ በማሳጣት የአባይ ግድብ ከአንገት በላይ እራስን (ጭንቅላት) ተማቶ እግር እንደ ማሻሸት አድርጌ ስለምወስደው ነው።

መለስ ዜናዊ Arab Spring የአረብ ስፕሪንግ/የግብጽ እስላማዊ ወንድማማቾች) ሁከት አጋጣሚ በመጠቀም የግብጽን የልብ ትርታ መዳከም ተመልክቶ አባይ ወንዝን እንደገደብ አደረገ- ነጠቃቸው። እንድሁም የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነት መዳከም አይቶ ቀይ ባህር አሰብ ከኢትዮጵያዊያን ነጥቆ ለሻዕብያ ሰጠ። 1 ነጥብ አግኝቶ በርካታ ነጥቦች ጣለ። ሲጣፋ ውጤቱ ምን እንደ ሆነ እራሳችሁ ፍረዱ። እውነት ግን መነገር የግድ ይላል።