Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sesame
Member+
Posts: 7903
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Jawar is Exposing How Abiy and his PP Cronies are Stealing Billions Using a front called Ovid

Post by sesame » 08 Sep 2025, 16:08

On top of all his crimes, Abiy is turning out to be a Mega-Thief!
Finfinne Press
14m

🚨 ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ፣ በኦቪድ ኮንስትራክሽን ዙሪያ ያነሳውን የሙስና ውንጀላ ተከትሎ በመንግስት ሚዲያዎች የቀረቡትን ማስተባበያዎች "ሀሰት" ሲል አጣጥሎ፣ ኩባንያው እንዴት እንደተቋቋመ እና ከባንኮች እንዴት ብድር እንዳገኘ ያሳያሉ ያላቸውን አዲስ የማጋለጫ ሰነዶች ይፋ አደረገ።

ጃዋር በማህበራዊ ገጹ ላይ ባወጣው አዲስ መግግለጫ፣ ኦቪድ "በሰራተኞች የተቋቋመ የሼር ኩባንያ ነው" የሚለውን ክርክር በማድረግ እና ኩባንያው ከሲንቄ ባንክ ያገኘውን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብድር ህጋዊ አሰራርን ያልተከተለ መሆኑን የሚያሳይ የብሔራዊ ባንክ የኦዲት ሪፖርት ነው ያለውን አጋልጧል።

የኦቪድ ባለቤት አቶ ዮናስ ታደሰ፣ ኩባንያው በ40 ሰራተኞች ባለቤትነት የተያዘ የሼር ኩባንያ መሆኑን መናገራቸውን ያስታወሰው ጃዋር፣ ይህ "ሙሉ በሙሉ ሀሰት ነው" ብሏል።

ለዚህም ማስረጃ አድርጎ ያቀረበው ከብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው ያለው ሰነድ እንዲህ ይላል፦ "ኦቪድ ኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣ በ2013 ዓ.ም. በ500,000 ብር የተከፈለ ካፒታል የተቋቋመው በአቶ ዮናስ ታደሰ እና በወ/ሮ ወሰንየለሽ አሊ ነው።"

ይህንን ተከትሎም ጃዋር፣ "ታዲያ የተቀሩት ባለአክሲዮኖች እነማን ናቸው? መቼስ ነው አክሲዮን የገዙት? መልሱ በሰነድ ይደገፍ" ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ከዚህም በላይ ጃዋር፣ አቶ ዮናስ "ከመንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም" የሚሉትን ምክንያት በመሞገት፣ ኩባንያው ከሲንቄ ባንክ ያገኘውን ብድር በተመለከተ የብሔራዊ ባንክ የኦዲት ሪፖርት ነው ያለውን ግኝት ይፋ አድርጓል።

የኦዲት ሪፖርቱ ግኝቶች (በጃዋር እንደቀረበው)፦

• ባንኩ ለኦቪድ 300 ሚሊዮን ብር ብድር የፈቀደው፣ የኩባንያው ሀብት ከ90% በላይ በዕዳ የተያዘ መሆኑ እየታወቀ ነው።

• ባንኩ የሰጠውን የ300 ሚሊዮን ብር የተጨማሪ ገንዘብ ማውጫ ፈቃድ (overdraft) በጊዜው አልሰበሰበም ወይም አላሳደሰም።

• ባንኩ ብድሩን ሲፈቅድ፣ የኦቪድን የገንዘብ ፍሰት እና ብድር የመክፈል አቅም አልተነተነም።

• ክትትል አለመኖር፡ ባንኩ የሰጠው ብድር ለታለመለት አላማ መዋሉን የሚከታተልበት ስርዓት አልነበረውም።

ይህንን ተከትሎም ጃዋር፣ "ሲንቄ ባንክ በምን ምክንያት ይሆን ይህንን ሁሉ የባንክ ህግ ጥሶ፣ በዕዳ ለተዘፈቀ ኩባንያ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ያበደረው?" የሚል ጥያቄ በማንሳት፣ ድርጊቱ ከጀርባው የፖለቲካ ግፊት እንዳለበት ጠቁሟል።
በጉዳዩ ላይ ከመንግስት፣ ከኦቪድ ኮንስትራክሽንም ሆነ ከሲንቄ ባንክ በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

https://www.facebook.com/share/p/1CG1FToek1/