Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በእንቁጣጣሽ ዋዜማ አዲስ አበባ ግዙፍ ጭንቀት ላይ ነች!

Post by Horus » 31 Aug 2025, 13:57

ይህ ግዙፍ ጭንቀት ...

የሰሞኑ ከባድ ዝናብና ጎርፍ አይደለም

እዚም እዛም የሚመረቀው ኮሪደርና ሪቨን ቆረጣ አይደለም

ከእንቁጣጣሽ በመላ ከተማው የሚተራመሰው የባዛርና የገበያ ትፍፍግ አይደለም

በአለም አቀፍ ደረጃ በጉጉት የሚጠበቀው የጳጉሜ 4ቱ ታሪካዊው የህዳሴ ገርድ ምርቃት አይደለም !!!

ጭንቀቱ ...

ሰሞኑን ባዲስ አበባ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር የሚደረገው የተባበሩት መንግስታት ክላይሜት ኮንፈረንስ ነው!!!!!!!!!!!!!!

በዚህ ግዙፍ ስብሰባ ላይ ለመካፈር 45, 000 እንግዶች አዲስ አበባ ይገባሉ!

ይህ ሁሉ ሕዝብ የት ነው የሚያርፈው?

ባለፈው የአፍሪካ አንድነት ሰብሰባ ወቅት እንደ ተነገረው አዲስ አበባ 42 አለም አቀድ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎች ብቻ ነው ያላት ?????

እነዚህ ከ39፟ እስከ 42 የሚደርሱት ከ 5 ኮከብ እስከ 1 ኮከብ ደረጃ ያላቸው ማለት ነው

ለምሳሌ ባለ 5 ኮከቦቹ 5 ሆቴሎች እስካይላይን፣ ሼራተን፣ ሂልተን፣ ሃያትና ራዲሰን ያላቸው 2100 አልጋዎች ብቻ ነው

የቀሩት 35 ሆቴሎች 43,000 እንግዶችን ማስተናገድ ይኖርባቸዋል ማለት ነው።

አዲስ አበባ ከአለም 3ኛ ወይን 4ኛው የአለም ዲፖልማሲ ከተማ በመሆኗ ገና ብዙ ብዙ የሆቴልና ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ እድገት እንደ ምትፈልግ ይህ ክላይሜት ሰሚት ፍንትው አድርጎ ነጋዴውን እያነቃው ነው!!!!

THIS IS WHAT WE CALL GOOD PROBLEM!!!

ኢትዮጵያ ትደግ ትመንደግ !!!!