Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4776
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: Integrated Ethiopia Learning the Two Afàn Oromôs (Amarigna = Afàn Môtī and Oromiffà = Afàn Gadà)!

Post by Meleket » 29 Aug 2025, 10:19

እስቲ በሀገር በቀሉ፡ በግእዝ ፊደሎች አንዳንድ ታሪካዊ ትንታኔዎችን ካነበብነው እናቋድሳችሁ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር!https://debretsioneotc.org/YeEthiopia%20Andinet.pdf
የኦሮሞዎች መስፋፋት ክስተት

ኢትዮጵያ ልታሸንፈው ያልቻለችው ሌላ ጠላት ነበራት፡ ይኸውም የኦሮሞ የመስፋፋት ክስተት ነው። የኦሮሞ ከደቡብ ወደ መሐል ሀገር መስፋፋት ምክንያት ኢትዮጵያ ከባድ ውድቀት ደርሶባታል። የደቡብ ምዕራብና የምሥራቅ ክፍላተ ሀገሮቿን እንድታጣ ተገደደች። በነዚህ ክፍላተ ሀገሮች ይኖሩ የነበሩ ማንነታቸው በውል የማይታወቁ በአጠቃላይ ሲዳማ ወይንም አማራ ብለን የምንጠራቸው ሕዝቦች ከምድረ ገፅ ጠፍተዋል፣ ባይጠፋም ቋንቋቸው፣ ባሕላቸው፣ ታሪካቸውና ስማቸው ጠፍቶ በኦሮሞ ተተክቷል። አሁን ኦሮሞ ሕዝብ ተብለው ሰፍረውባቸው የሚገኙ መሬቶች ኦሮሞ ከመምጣታቸው በፊት ባዶ መሬት አልነበሩም፣ አማራ ፣ ጉራጌ፣ ሌሎችም አሁን የደቡብ ሕዝቦች ብለን የምንጠራቸው ወይንም ሌሎች የጠፉት ሰፍረውባቸው ነበር። ኦሮሞ ከመጡ በኋላ ግን በሙሉ ተገደሉ ለማለትም ኣይቻልም፤ ከኦሮሞ ጋራ ተቀላቅለው ዘራቸው ጠፋ ማለት ይቀላል። ኦሮሞዎች እንደ ይፋት ወይንም እንደ አዳል መንግሥት አልነበራቸውም፣ ወረራ ፈጽመዋል ለማለትም አይቻልም። ኦሮሞዎች ያካሄዱት የመሬት ማስፋፋት ነው፣ሰፈራ ነው። ኦሮሞዎች መንግሥት ስላልነበራቸው አንድ መሪ አልነበራቸውም። በይፋት፣ በአዳልና በቱርኮች ያልተሸነፈ የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሞች ግን ተሸንፏል። ኦሮሞች እንደሌሎች ሕዝቦች ለምሳሌ ሶማሌ በጐሳ ተከፋፍለው እርስ በእርሳቸው የሚጣሉ አይደሉም። የኢትዮጵያ መንግሥት በሥልጣን ሹክቻ ወይንም በሐይማኖት ምክንያት ከግራኝ ከሐረር እስላማዊ መንግሥት ጋር ያደረጋቸው እርስ በእርስ ጦርነቶቹ በመዳከሙ፡ ኦሮሞዎች ተጠቅመውበት ወደ ባሰ ውድቀት እንዲደርስ አድርገውታል። ኦሮሞች አዲስ መሬት ለመያዝ እንደ ማዕበል ወደ ፊት ከመገስገስ በቀር የታወቀ ዓላማ አልነበራቸውም። መንግሥት ለማቋቋምም ዓላማ አልነበራቸውም፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋራ ስልጣን ለማጋራት ወይንም የነበረውን መንግሥት ገልብጠው ስልጣን ለመያዝ ዓላማ አልነበራቸውም። በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጥላቻ እንዳልነበራቸው የሚያስረዳ አንዳንድ ነገሥታት ለውትድርና እየመለመሉ ይጠቀሙባቸው እንደነበሩ ብዙ ጊዜ ያጋጥም እንደነበረ ተዘግቧል።

ኤውሮጳውያን ታሪክ ጸሐፊዎች የኢትዮጵያ ሕዝብን በጎሳና በቋንቋ ሲከፋፍሉት ኦሮሞዎችን ከደቡባውያን የኩሽ ዘሮች ጋር ይመድቧቸዋል። የሀገራችን ታሪክ ጸሐፊዮችም የዚሁ ዓይነት አከፋፈል ነው የሚከተሉት። ይህ አሰራር ቋንቋና ጎሳን ለይቶ ለማወቅ ባለመቻሉ የአንድ ሰው ወይም ሕዝብ ማንነት ቋንቋው ብቸኛ መለክያ በመውሰድ የሚደረገው የዘር አመዳደብ ዘዴ ነው። በቋንቋው ብቻ የአንድ ሕዝብ ማንነት መመደብ ግን ትክክለኛው ሊሆን አይችልም። በሰሜን ኢትዮጵያ ሴማዊ የተባለው የግእዝ ቋንቋ ከመስፋፋቱ በፊት ከዚያም በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃላይ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እየፈለሰ ስለሚሄድ ቋንቋዉን ትቶ አዲስ የሰፈረበት ቦታ ቋንቋና ባሕል እንደሚይዝ የታወቀ ነው። ኦሮሞችም ከዚህ ሕግ አይወጡም። ቅድመ ታሪክ ኦሮሞዎች የሰፈሩበት ቦታ በሰሜን በደቡብ ወይንም በመሐል በምሥራቅ ኢትዮጵያ ይሁን አይታወቅም። አቶ ተክለ ፃዲቅ መኵሪያ በኢትዮጵያ ታሪክ አንደኛ መጸሐፍ ገጽ 30 የሌሎች ጸሐፊዎችን ታሪክ በመጥቀስ፡ ከኑቢያ እስከ ኤርትራ ባሕር ተበታትኖ የነበረ ሕዝባችን የስም ዝርዝር ሲሰጥ፡ በቁጥር 18፡ ጋሊ የተባለውን ጋላ ብለው ተርጉሞታል። መሠረት የሌለው አተረጓጐም ነው ለማለት አይቻልም። የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ሆኖ ያገለግል የነበረው ግብፃዊው የክርስትና ሐይማኖት ተከታይ ስሙ ብትሮስ ጋሊ ሲሆን ይኸውም ስማቸውን ወደ ዓረብኛ ያልቀየሩ የጥንት ግብፃውያን ስም ሊሆን ይችላል። ኢጣሊያዊው የኢትዮጵያ ታሪክ ፀሐፊ ኮንቲ ሮሲኒ ስለጥንታውያን ግብፅ ጥልቅ ምርምር ያደረጉ የኤውሮጳ ታሪክ ፀሐፊዎች የሰጡትን አስተያየት በመጸሐፉ እንደተገጸው ኢልሚ ኦርማ (የአርማ ልጆች) ወይም የኦሮሞ ልጆች ማለት መሆኑን የሚል ትርጉም ተሰጥቷል፡ ይሄም ትርጉም የተሰጠው ቱት ሞሲስና ሌሎችም የግብፅ ፈርኦኖች በሐውልቶቻቸው ስለአስገበሯቸው የኩሽ ዘሮች ስም ዝርዝር ተቀርፆ በተገኙ ማስረጃዎች መሠረት በማድረግ ነው።

ኮንቲ ሮሲኒ አስተማማኝ ታሪክነቱን በግሉ ቢክደውም ባለሞያዎች የሰጡት አስተያየት በደፈናው ሐሰት ነው ለማለት አይቻልም። ኦሮሞዎች ከ1520 ዓ.ም. በፊት ወደ መሐል ኢትዮጵያ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ደቡብ ኢትዮጵያ ቦረና አካባቢና ከኒያ ብቻ ሰፍረው እንደነበሩ የተረጋገጠ ነው። ኦሮሞች ሰፍረውበት የነበረ ዋናው ማእከል ዋላቡ ከአብያተ ሀይቅ በስተምሥራቅ የሚገኘው ተራራ ነው ተብሏል። በዚህ አንድ አውራጃ በማያህል መሬት ሰፍረው ተወስነው ለብዙ ዓመታት ይኖሩ የነበሩ ኦሮሞዎች በጥቂት ዓመታት ውስጥ መላው ኢትዮጵያን ማጥለቅለቃቸው በየትም የዓለም ክፍሎች ያልታየ ታአምራዊ ክስተት ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ብዙ ፈተናዎችን አልፎ ቋንቋውን ባሕሉን እና ስልጣኔውን ከሰሜንና ቀይ ባሕር እስከ ሕንድ ውቅያኖስ ሞንባሳ በሚያስፋፋበት ጊዜ፤ አንድ መቶ መንግሥታት ወይንም 35 መንግሥታት ወዘተ . . . በስሩ አሉት ይባል የነበረው፡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት፡ የአንድ አውራጃ ሕዝብ ብዛት እንኳን ያልነበራቸው ኦሮሞዎች ከስር መሠረቱ ሊያንኮታትኩቱት የቻሉት በጦር መሣሪያ ተጠቅመው አይደለም። ጋዳ ወይም ጉዲፈቻ በተባለው የአስተዳደር ስልታቸው ተጠቅመው ነው። ኦሮሞዎች ለብዙ ዘመናት ከባንቱ ጎሳዎች በጉርብትና በኖሩበት ጊዜ ጋዳ የተባለው የዕድሜ ክልል መሠረት የሚያደርግ የአስተዳደር ዘዴ ከእነሱ በመውሰድ አስፋፍተውታል። በዚህ ፀባያቸው ከሌሎች የካም ዘሮች ይለያሉ። ሌሎች የካም ዘሮች ሁሉ እርስ በእርሳቸው የሚለያዩ በስጋ ዝምድና ሲሆን ኦሮሞዎች ግን እንደ ኮከብ ቆጠራ የአንድ ዕድሜ ክልል የሆኑ ሰዎች በአንድ ወገን ይመደባሉ። ጋዳ ብዙ ደረጃ አለው 1. ዳባሌ 2. ፎሌ 3. ቆንዳዳ 4. ዶሪ 5. ሉባ እየተባሉ ይጠራሉ። የጋዳ ደጋፊዎች ዲሞክራሲ አስተዳደር ነው ይሉታል። ነገር ግን እጅግ ኋላ ቀር የሆነ አስተዳደር ዘዴ ነው። ኦሮሞዎች ወደ መሐል ሀገር ከመሰራጨታቸው በፊት የሐይማኖት መሪዎቻቸውና ጠንቋዮቻቸው አባ ሙዳ ይባሉ ነበር። ሁለት አባ ሙዳዎች ነበሩ። አንዱ ባዳሎ ጫካ በገናሌ ወንዝ አጠገብ ሁለተኛው በዋላቡ ተራራ። በኋላ ግዜ ኦሮሞዎች ወደ መሐል ሀገር ዘልቀው ገብተው የባሌን መንግሥት በተቆጣጠሩበት ጊዜ የአባ ሙዳ መኖሪያ የአቡል ቃሲን ተራራ ጫፍ ታዋቂው ሺክ ይኖርበትና ያረፈበት ሆነ። የሁለቱ እምነቶች ተዋሕደው የኦሮሞዎች ሁሉ ቅዱስ ቦታ ማእከል ለመሆን በቅተዋል። ኦሮሞዎች ለዘመናት በሰላም በደስታ ይኖሩባት ከነበሩ ሰፈራቸው ለቀው ወደ መሐል ኢትዮጵያ እንዲሰራጩ ምክንያት የሆኗቸው ሶማሌዎች ናቸው ተብሏል። በግራኝ ጦርነት ጊዜ ኦሮሞች አይታወቁም ስለነበረ ግራኝ ለውትድርና ሊመለምላቸው አላሰበም። ግራኝ ለተዋጊነት የተጠቀመባቸው ሶማሌዎች ብቻ ነበሩ። መጠነ ሰፊ የሆነ የቀንድ ከብቶች፡ ወርቅ የጦር መሣሪያና ባሮች ከክርስቲያን ኢትዮጵያ ሶማሌዎች በግራኝ ጦርነት ጊዜ ዘርፈው ያመጧቸው በማየታቸው ኦሮሞዎች በሶማሌዎች ከመሬታቸው ስለተፈናቀሉ ወደ መሐል ኢትዮጵያ እንደ ባሕር ማእከል ተሰራጩ። ኦሮሞዎች ከመምጣታቸው በፊት ምዕራብ ወለጋ አንፊሎ ተብሎ ይጠራ ነበረ። ወሎም የቀድሞ ስሙ አንጎት ነበር ወዘተ . . . ጋፋት፣ ትልቁ ዳሞት ፣ ዳዋሮ፣ ፋጢጋር፣ ማራ፣ አዳል፣ ወዘተ ተብለው ይጠሩ የነበሩ ክፍላተ ሀገሮች ወይንም መንግሥታት ታሪካቸውና ስማቸው ቋንቋቸውና ባሕላቸው ጠፍቷል፣ በኦሮሞ ቋንቋና ባሕል ተተክቷል ወይንም ዘራቸው በሙሉ ጠፍቷል።

ይህ ታሪክ የተፈጸመው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሲሆን አውሬዎች እንኳን ዘራቸው እንዳይጠፋ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል። በዛሬ አንድ መቶ ዓመት ዳግማዊ አጼ ሚኒልክ የቀድሞ አባቶቻችን የገነቧት የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ባስከበረበት ጊዜ እንደገና ወደ ኢትዮጵያ የተቀላቀሉት ክፍለ ሀገሮች ቋንቋቸው እና ባሕላቸው እንኳን ባይቻል የቀድሞ ስማቸው እንዲያገኙ ማድረግ ይገባው ነበር። አጼ ምኒልክ ይኽንን ባለማድረጉ የኦሮሞ ቋንቋና ባሕል እንዳይነካ በማድረጉ የዛሬ አንዳንድ ኦሮሞዎች አጼ ምኒልክን በወረራ እንደያዛቸው ሲወቅሱ ይታያሉ፡ አጼ ምኒልክ ያዘመተው የአማራ የኦሮሞ የትግሬ ወዘተ . . . ያሉበት የኢትዮጵያ ሠራዊትም ነፍጠኛ እየተባለ ስም ማጥፋትና ታሪካዊ ቅዱስ ዓላማውና ተልኮው የተወጣበት አድናቆትና ምስጋና ሲገባው የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚያናፍሱት ወሬ በማስተጋባት ይገኛሉ። ዛሬ ኦሮሞዎች የሰፈሩባቸው ክፍላተ ሀገሮች ምሥራቅ ደቡብና ምዕራብ ሸዋ፣ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ወለጋ፣ ኢሉባብር እና ጅማ ባዶ መሬት አልነበሩም። ቅድመ ኦሮሞ የነበሩ ሕዝቦች በግዴታ የኦሮሞ ቋንቋ በጉዲፈቻ በመውሰድ ኦሮሞ ተባሉ እንጂ በዘር ኦሮሞ አይደሉም። ስለዚህ ኦሮሞ ቋንቋ ነው እንጂ ዘር አይደለም። በዘር ከሆነ ኦሮሞ የአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎሳዎች በውስጡ ያቀፈ ነው። ስለዚህ ኦሮሞ ተናጋሪ የሆኑት የሁሉም የኢትዮጵያ ጎሳዎች ስለሆኑ በኢትዮጵያ ጎሳዎች ላይ ጥላቻና ቅራኔ ሊኖራቸው አይገባም። ኦሮሞ ሳይታሰብ ቋንቋውን በመላ ኢትዮጵያ አማርኛ ያልቻለውን በተአምር ሊያስፋፋ ችሏል። ይህ በመሆኑ ኦሮሞዎች ሊደሰቱ ይገባቸዋል እንጂ በግንባር ቀደም በቋንቋችን እንዳንጠቀም ያለፉት መንግሥታት ጨቆኑን ለማለት አይችሉም። በኦሮሞ ፈንታ አማርኛ ከዳር እስከዳር ባለመስፋፋቱ ቁጭቱ ሊኖራቸው የሚገባ አማርኛ ተናጋሪ ብቻ ሳይሆኑ ሀገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊያድርበት ይገባል። በኦሮሞ መሬታቸውን ተነጥቀው ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ያጡ ሕዝቦችም በዕድላቸው ሊያዝኑ ይችላሉ። የኦሮሞ ሕዝብ ግን ከማንኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብ በላይ መብቱ የተጠበቀለት ስለሆነ አሁን ሲነገር እንደምንሰማው መብቴ አልተከበረም ብሎ ቅሬታ ማሰማት ባለፈው ታሪካችን አንፃር ተቀባይነት የለውም። በማንኛውም ጦርነት እንደሚያጋጥም የምኒልክ ሠራዊትም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጭፍጨፋ ተፈጽሞ ይሆናል፣ ኦሮሞዎች ከፈጸሙት ጭፍጨፋ ግን የሚነጻጸር አይደለም። ብዙ የሰው እልቂት የተፈጸመበት ወቅት ቢኖርም በምኒልክ ዘመቻ ግዜ ከሁሉ የባሰ በኦሮሞዎች አካባቢ የተደረጉ ጦርነቶች አልነበረም። ከሁሉ የባሰ ጭፍጨፋ የተፈጸመው ኦሮሞዎች እንደ ጅማ አባጅፋር የተካፈሉበት በከፋ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ዘመቻ ጊዜ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ብዙ ቃላቶች ያለአግባብ እንጠቀማለን።

ለኦሮሞዎችና በሌሎች ሕዝቦች ያለውና የነበረው ግንኙነቶች ወራሪና ተወራሪ ገዢና ተገዥ ብለን ለመጠቀም ብንፈልግ ግን የኦሮሞ ሕዝብ ወራሪ ነው እንጂ በሀገሩ ላይ አልተወረረም። ለም መሬት ነጥቆ ከሌሎች በመያዙ ገዢ ነው እንጂ ተገዢ አይደለም። የአማርኛ ቋንቋ እንኳን የመንግሥት ቋንቋ ሆኖ ያላደረገውን ኦሮሞዎች ሌሎች ሕዝቦች ቋንቋቸው ባሕላቸውን ስማቸው እንዲቀየሩ አድርገዋል። አማራ ማለት እንደ ኦሮሞ ቋንቋ ነው እንጂ የጎሳ ስም አይደለም። አማርኛ እንደ ኦሮምኛ ብዙ ጎሳዎች የሚጠቀሙበት ቋንቋ ነው። አብዛኛው ዛሬ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ዘራቸው አገው ነው፣ አገው ባይሆኑም ከትግራይ የመጡ ናችው።

ኦሮምኛ ቋንቋ እየተናገሩ ኦሮሞ እንዳልሆኑ ከሚያምኑ ሕዝቦች የወርጂ በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። ወርጂ ከትግራይ እንደሚወለዱ ያምናሉ። በንጉሥ ዐምደፅዮን ዘመን ከአፋር ኗሪዮች እስላሞች ከሌሎች እስላሞችም ጋራ ሆነው ፀረ ክርስቲያን የኢትዮጵያ መንግሥት ግንባር የፈጠሩ ተብለው ተጠቅሰዋል። ዘራቸው ከአፋር ወይንም ከሶማሌ አይደሉም፤ ጉራጌዎች ከትግራይ መጣን እንደሚሉ፣ እንደዚሁም በሲዳማ የነበሩ የነገሥታት ዘራቸው ከትግራይ መሆኑን እንደሚያምኑ፣ በተመሣሣይ ወርጂ ከትግራይ መምጣታቸው ይናገራሉ፡ በአዋሽ ከኦሮሞ ሜታ በቾ ይዋሰናሉ።

ኦሮሞች በታሪካቸው በሶማሌዎች ከሰሜን ወደ ደቡብ እንዲፈልሱ ተደርገዋል፡ በባንቱ ከደቡብ ወደ ሰሜን እንዲፈልሱ ተገዷል፡ ቀጥሎም ከ100 ዓመት ባነሰ ጊዜ ከሲዳማ (ደቡብ ሕዝቦች) እና ከአማራ ባደረጉዋቸው ጦርነቶች አሁን የሚኖሩባቸው ሰፋፊ መሬቶች ለማግኘት በቅቷል። በመጨረሻም ጠብመንጃ ታጥቀው ሊዋጉዋቸው ከመጡ አዲሶች የአማራ ወራሪዮች ጋራ ጩቤ ይዘው እንኳን ለመከላከል ሳይሞክሩ ነፃነታቸውን ተነጥቀዋል በማለት ቸሩሊ ስለ ኦሮሞች መስፋፋት ክስተት ባጭር ገልጾታል። ኦሮሞ ድል የተመቱት የማሩ ኰሪቻ (Sella Maru) በተባለው ቦታ በራስ ጐበና በሚመራው የኢትዮጵያ ሠራዊት ነው። ራስ ጐበና ጨቦ በኦሮሞች ላይ ጦርነት ገጥሞ ድል ተጐናጽፎ ወደ ጊቤና ምዕራብ ኢትዮጵያ ለመገስገስ መንገድ የከፈተበት ወሳኝ ድል የተጐናጸፈበት ቦታ ነው። “የኢትዮጵያ አንድነትና ኢጣልያ - በዶ/ር ተወልደ ትኩእ - አዲስ አበባ በ1990 ዓ.ም. - ከ ገጽ 85-88 የተወሰደ)

የቀይባህሩ ፈርጥ ዶ/ር ተወልደ ትኩእ፡ ኢትዮጵያ እምብርት አዲስ አበባ ማለትም ፊንፊኔ ወይም ሸገር መሃል፡ ሃዉልት ሊሰራላቸው የሚገባ ምርጥ የአፍሪካ ቀንድ የታሪክ ተመራማሪ መሆናቸውን ለመግለጽ ያህል ነው። ይመቻችሁ!
:mrgreen:

Post Reply