ብልፄ በሀሳብ ሞግቱኝ ፣ በምክንያታዊነት ተከራከሩኝ ብላ ትፎክራለች ... ሀሳብ ሲቀርብ ፣ በማስረጃ ስትጋለጥ ፣ በምክንያት ስትተች ... በቅፅበት ድንኳኗን ጥላ ብሶት አራጋቢዎች ፣ ችግር አነፍናፊዎች ፣ ስህተት ፈላጊዎች ብላ ታለቅሳለች ...
ብልጭልጭ ፕሮጀክቶቿን እንኳን ለምን እንደተገነቡ ፣ ምን ጥቅም እንደሚሰጡ ፣ ምን ያህል ገቢ እንደሚያስገኙ ፣ የስራ እድል ምን ያህል እንደሚፈጥሩ ፣ ለሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት ምን አስተዋጽኦ እንዳላቸው ፊት ለፊት መሞገት ሳትችል ...
በአርባ አቅጣጫ በ700 ካሜራ የተቀረፀ የመብራት ጋጋታ ፎቶዎችን እየለቀቀች ስለ ሃሳብ ልዕልና ትሰክሳለች። ብልፄ ዛሬ ላይ ስህተቷ ገዝፎ ፣ የፖለቲካ ካርዶቿ ተቃጥለው ፣ ትኩረት የሚሰጠው አጀንዳ መቅረፅ ተስኗት ... ኮንፊደንሷ ወርዶ አሁን ላይ በአባይና በቀይ ባህር አጀንዳ ለመደበቅ ትውተረተራለች።
በነገራችን ላይ ጃ ከስድስት ወራት በፊት ..."ከተማውን ሺሻ ቤት አስመስለው .. ይህቺ ናት ኢትዮጵያ ብለው እያለ ይፎክራሉ" .. ብሎ ትችት ከሰነዘረ በኃላ ብልፄ የምትመካበት ፕሮጀክቶችን ወደ ህዝቡ ማስረፅ አልቻለችም።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ፈርሴቡላ ስለ ዲምላይት ተአምራት ለስድስት ወራት በየእለቱ ህዝቡን በፕሮፖጋንዳ ለመጥመቅ ቢዘመትም ዋጋ ቢስ ሆኗል። የብልፄ አባላት እርስ በርስ ከመማራቸው ውጪ የፈየደውም ነገር የለም።
ዛሬ በአባይና በቀይ ባህር አጀንዳ የህዝቡን ቀልብ ለመግዛት ፣ የሞተውን የፖለቲካ ካርድ ለመመንጨቅ ፣ ተቀባይነት ለማግኘት ሲውተረተሩ ሲታይ እጅጉን ያዝናናሉ።
ሰራዊት ሳያደራጅ ፣ ጦር ሳያዘምት ፣ የመንግስትን መዋቅር ሳይቆጣጠር ፣ በሃሳብ መሳሪያ ብቻ በየእለቱ የብልፄን የፖለቲካ ኮንፈርት ዞን ከላይ እስከ ታች የናጠው የጀዌ ትውልድ መሆን በእራሱ ኩራት ነው
.
.https://www.facebook.com/share/p/16ir2G9B3N/
.
"ዛሬ በአባይና በቀይ ባህር አጀንዳ የህዝቡን ቀልብ ለመግዛት ፣ የሞተውን የፖለቲካ ካርድ ለመመንጨቅ ፣ ተቀባይነት ለማግኘት ሲውተረተሩ ሲታይ እጅጉን ያዝናናሉ።"
Fìfinne Press is an Ethiopian facebook blogger who is exposing PP's bankruptcy. He is a hard-hitting analyst who despises the likes of horus who are intent on cheating Ethiopians by useless flashy corridor projects.