Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 39939
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ናሴ 15 ምጅር ያቆሙ ማይ! የደመራ ማቆሚያ ቀን!

Post by Horus » 15 Aug 2025, 22:04

የቀሩት ኦርቶዶክስ ጉራጌዎች ትክክለኛ ቀን ባላውቅም (በተለይ ምሁር አክሊን ከኛ ጋር አንድ ባህል ነው ያላቸው) በክስታኔ ደመራ ሃ ተብሎ አጠናዎቹ የሚተከሉት በነሃሴ 15 ቡሄ ለት ነው። ምጅር ደመራ ማለት ነው ። በመላ ምድረ ክስታኔ በነሃሴ 15 አንድም ሰው ዛፌን አትቁረጡ ብሎ መከልከል አይችልም። ያገር ሴራ ነው። ቀጫጭን የምጅር ዛፍ በለበት ሁሉ ስንቆርጥ ልክ በገና ጨዋታ መፈናከት እንደ ማያስቆጣ ሁሉ ነሃሴ 15ም እንደዚያው ነው። ቀጫጭኖቹ ረጃጅም ወጣት ዛፎች ልጣጫቸውን ልጠን የደመራ ተክለ አጽም (አስኬለተን) የምናቆመ በፍልሰታ ቡሄ ቀን ነው። የምጅር ትክል ማይ (የደመራ ማቆሚያ ቀን) እንለዋለን ። ከዚያም ከእንቁጣጣሽ ማግስት ጀምሮ ደመራውን በቅጠልና ገድራ በተባለ ነዳጅ ቁጥቋጦ እንጠቀጥቀዋለን። እንዲሁም ከእንቁጣጣሽ (አክራሚ ይባላል በክስታኔኛ) ማግስት ጀምሮ ማታ ማታ እስከ መስቀል ድረስ ልጃ ገረዶች (ቀንዣዠ) ደመራው ስር እየተሰበሰቡ ይዘፍናሉ! አበቤ አበቤ ይባላል። ይህ ቀን የዛሬ ሳምንት ይመስለኛ፣

Last edited by Horus on 15 Aug 2025, 22:37, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 39939
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ናሴ 15 ምጅር ያቆሙ ማይ!

Post by Horus » 15 Aug 2025, 22:16

ከዛሬ ሳምንት ጀምሮ እስከ ገና ድረስ በጉራጌ ምድር እጅግ ከፍተኛ የደስታ ወራት ነው ። በመስክረም ጥቅምት ህዳር ውስጥ ያሉት የበአላትና ጨዋታ አይነቶች በጣም ብዙ ናቸው! በብዙ መንገድ ከመደበኛው ኦርቶዶክስ በአላት የተለዩ ናቸው ። ለምሳሌ እንቁጣጣ አክራሚ ሲባል ክርማን የክረምት መጨረሻና የብርሃን መወለድ ጋር የተያያዘ ነው። መስቀል The Festival of Light ነው ምጅር ደመራ ፌስቲቫል የ15 ቀናት በዓል ነው። በክስታኔ ቡሄ ሆያ ሆዬ ወጣቶች ከሕዳር መጀመሪያ አስንቶ እስከ ገና እለት ሜዳ ገና (አንቃት) እነተጫወትን ማታ ማታ ሆያ ሆዬ (እንዞሪቴ) በየቤቱ እየዞርን ወይፈን መግዣ ገንዘብና እህል የምንሰበስብበት ወራት ነው ። ስለዚህ ገና (የብርሃን ልደት) ፌስቲቫል በመሰረቱ ከአክራሚ እንቁጣጣሽ እስከ ገና የሚከበር ወራት ነው ። መስቀል ግማደ መስቀል አሌኒ ያገኘችበት የሚለው እና የጉራጌ መስቀል አንድ አይደሉም ።

Horus
Senior Member+
Posts: 39939
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ናሴ 15 ምጅር ያቆሙ ማይ! የደመራ ማቆሚያ ቀን!

Post by Horus » 15 Aug 2025, 22:46

የመስቀል ሰሞን የጎረምሶች ጨዋታ !


Post Reply