Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12889
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

ሆረስ ሁሉን ነገር ትተህ፣ አሁን እዉነቱን ተናገር ና፣ አሁን አዲስ አበባ ብትሄድ መዉጫ መግቢያዉን ትለያለህ?

Post by DefendTheTruth » 15 Aug 2025, 12:08

የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ፣ እዚያ ያደግኩኝ ነኝ ስላልክ ነዉ። እኔ በበኩሌ የአዲስ አበባ ልጅ አይደለሁም፣ እዚያ ኖሬያለሁኝ እንጂ። አሁን ብሄድ ግን ምንም ከምን መለየት የምችል አይመስለኝም።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ወዶ አይመስለኝም ከኩርፊያዉ ወጥቶ ወደ ምርጫ እመለሰለሁኝ ያለዉ።

ሌላ ምን አማራጭ አለዉ?

እዉነትን የካደ ከሰዉ ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪም ጋር ተጣልቶዋል ማለት ነዉ።



Horus
Senior Member+
Posts: 39939
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሆረስ ሁሉን ነገር ትተህ፣ አሁን እዉነቱን ተናገር ና፣ አሁን አዲስ አበባ ብትሄድ መዉጫ መግቢያዉን ትለያለህ?

Post by Horus » 15 Aug 2025, 12:29

ዲዲቲ፣
እኔ የኖርኩባት አዲስ አበባ በምራብ አስኮ ፋብሪካ ታበቃ ነበር። በሰሜን ጉለሊና ሽሮ ሜዳ ነበር ፣ በምስራቅ ላም በረትና ካሳንቺስ ነበር ፣ በደቡብ ነፋስ ስልክና አሮጌው አይሮፕላን ማረፊያ ነበር ። በዚህ ክልል ያለቸውን አዲስ አበባ ሺ ግዜ መንገድና ፎቅ ቢሰራባት ጥርት አድርጌ ነው የማውቃት! እኔ እያለሁ የነበሩት የሳር ፣የቆርቆሮ ቤቶችና ሚዳዎች በፍጹም አንዳቸውም ዬሉም ። እንኳንስ አዲስ አበባ አገር ቤት ያደኩበት ሰፈር ሁሉ ከተማ ሆኖዋል! እኔ እጅግ በጣም ለውጥ የምወድ ፣ ለለውጥ እድሜዬን ሁሉ የታገልኩ ሰው ነኝ ! እኔን የማይመቹኝ ዱላ ተሸካሚ እረኞችና ግዜ ያለፈባቸው ፊውዳሎች ካመት አመት የምታደርጉት ቀቢጸ ተስፋ መላላጥ ነው ። ለውጥ በኢቮሉሽንም በሬቮሉሽንም የታሪክ ሕግ ነው! ሆረስ ነኝ!

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12889
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ሆረስ ሁሉን ነገር ትተህ፣ አሁን እዉነቱን ተናገር ና፣ አሁን አዲስ አበባ ብትሄድ መዉጫ መግቢያዉን ትለያለህ?

Post by DefendTheTruth » 15 Aug 2025, 12:59

ጀምሮ መጨረስ ማለት ምን ማለት ነዉ፣ እንዴት ይለያል?

ፕሮጀክቶች በወያኔም ዘመን ይጀመሩ ነበር፣ በጣም በብዛት። የወያኔ መለያ የነበረዉ ጉዳይ ግን ጀመሮ መጨረስ የምባል ነገር አልነበረም። ብዙ ፕሮጀክቶች እንደተጀመሩ ይቀሩ ነበር፣ ለአመታት በእንጥልጥል ይቀሩ ነበር፤ ገንዘብ ይሰረቃል። ጉቦ ይበዛል። የአገር ሃብት ይወድማል። የሕዝብ ብሶት ይንራል። በመጨረሻም ይህ የሕዝብ ብሶት ወያኔን ራሷን አጠልቅልቆ ወሰዳት።

ብልፅግና ይህን ጉዳይ በደምብ ተረድቶታል። ጠንቅቆ ያዉቃዋል፤ ምን እንደምያስከትል። ለዚህ ነዉ ነገሮችን በጥንቃቄ ና በብልሃት የምይዘዉ። አሁን ላይ ለዚህ ነዉ ትልቅ ትርጉም የተሰጣቸዉ ቃላቶች ስፒድ ና ስኬል (speed & scale) የምባሉት።

አሁንም ሌባ የለም ለማለት አይደልም፣ የምሰርቁ አሁንም አሉ፣ በፓርቲ ዉስጥም ተስግስጎ ወይም ደግሞ ከዉጪ ሆኖ የአገኙትን እድል ሁሉ ተጠቅሞ ለስርቆት የምጠቀሙት። እነዚህኞቹ ወደ ፖለቲካም የምሄዱት ለስርቆት ና ለራስ ጥቅም ነዉ። ትልቁ ለዉጥ አሁን ላይ ለጊዜዉ ነዉ እንጂ የላቸዉ ጊዜ ዉስን ነዉ። ይጋለጣሉ፣ ይወገደሉ። መስረቅ ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ስፒድ ና ስኬልን የልተገነዘቡ ሀላፊዎች ተስፋ የላቸዉም። ሰዉዬዉ እየሳቀ ዉስጡ እሳት ነዉ፣ የማትሰራ ከሆንክ ትዕግስት የለዉም። ለዚህ ነዉ ሁሉም በላባቸዉ ግፊት ቀን ተሌልት የምሮጡት። ጊዜዉ የለዉጥ ነዉ። የለዉጡ ሞተሮች ደግሞ ስፒድ ና ስኬል ናቸዉ። አክሎም ጥራት፣ ለትዉልድ የምተላለፍ መሆን አለበት። መደመር ትዝ ይበልህ!

Speed, Scale and Quality are the engines of today's changes in Ethiopia.

Post Reply