Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12536
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

ደደቡ የኢትዮጵያ ወጣት!

Post by DefendTheTruth » 17 Jul 2025, 15:54

ደደቡ የኢትዮጵያ ወጣት፣ እኔም ብሆን ከዚህ የተለየሁ አልነበርኩም፣ የአባቴን ክቡር ስራ አሻሽዬ እንደማስቀጠል እሱን ንቄ የመንግስት ስራ በምል አጉል ዝና በደሞዝ ተቀጥሬ ከወር ወር የማያደርስ ደሞዝ እየተቀበልኩ፣ ድሃ ሆኜ ቀረሁ። የአገሬ ገበሬ ዛሬ ላይ በወር 200 ሺ ብር እያገኘ ሀብታም ለመሆን በቅቶዋል። አብዘኛ የኢትዮጵያ ወጣት አሁንም አልነቃም። ስራ የሌለበት ከተማ ገብቶ ግማሹ ይራባል፣ ግማሹ እድሜዉን በማይረባ ስራ ላይ ይጨርሳል፣ የገበሬ ልጅ ሆኖ ሳላ ና ስራዉን የምችል መሆኑን እያወቀ፣ ሀብታምነትን ንቆ ድህነትን አሜን ብሎ ተቀብሎ ከተማ ተሸሽጎ የጉስቁልና ኑሮዉን ይገፋል። የፈረደበት!

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12536
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ደደቡ የኢትዮጵያ ወጣት!

Post by DefendTheTruth » 19 Jul 2025, 14:45

250.000 USD per harvest, only from Avocado harvest.

ሌላዉ ተኝቶ ይተኩስ፣ እንደ እኔ ማለት ነዉ።

Abere
Senior Member
Posts: 13972
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ደደቡ የኢትዮጵያ ወጣት!

Post by Abere » 19 Jul 2025, 15:01

DDT,
200,000 ብር እኮ በዶላር $1,370 ነው። አንተ ለአብይ አህመድ ውታፍ ነቀላ ተቀጥረህ እኮ በሳምን $2,000 ዶላር በነጻ ያለምንም ታክስ ከጉርሻ ጋር ታገኛለህ። በእውነት በዚህ ገበሬ ቀንተህ ነው? ፕሮፓጋንዳ ናት - ነቅተናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው እንኳን ሆዱ ሊሞእ የጥሩ ወጥ ሽታ እንደራቀው እናውቃለን።
በኮሪዴሩ ማስታወቂያ መለጠፍ እንኳን ተጨማሪ ኮሚሽን ታገኝ የለም ወይ? አትዋሽ :mrgreen:

DefendTheTruth wrote:
17 Jul 2025, 15:54
ደደቡ የኢትዮጵያ ወጣት፣ እኔም ብሆን ከዚህ የተለየሁ አልነበርኩም፣ የአባቴን ክቡር ስራ አሻሽዬ እንደማስቀጠል እሱን ንቄ የመንግስት ስራ በምል አጉል ዝና በደሞዝ ተቀጥሬ ከወር ወር የማያደርስ ደሞዝ እየተቀበልኩ፣ ድሃ ሆኜ ቀረሁ። የአገሬ ገበሬ ዛሬ ላይ በወር 200 ሺ ብር እያገኘ ሀብታም ለመሆን በቅቶዋል። አብዘኛ የኢትዮጵያ ወጣት አሁንም አልነቃም። ስራ የሌለበት ከተማ ገብቶ ግማሹ ይራባል፣ ግማሹ እድሜዉን በማይረባ ስራ ላይ ይጨርሳል፣ የገበሬ ልጅ ሆኖ ሳላ ና ስራዉን የምችል መሆኑን እያወቀ፣ ሀብታምነትን ንቆ ድህነትን አሜን ብሎ ተቀብሎ ከተማ ተሸሽጎ የጉስቁልና ኑሮዉን ይገፋል። የፈረደበት!

Naga Tuma
Member+
Posts: 6259
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ደደቡ የኢትዮጵያ ወጣት!

Post by Naga Tuma » 28 Jul 2025, 21:48

DefendTheTruth wrote:
17 Jul 2025, 15:54
ደደቡ የኢትዮጵያ ወጣት፣ እኔም ብሆን ከዚህ የተለየሁ አልነበርኩም፣ የአባቴን ክቡር ስራ አሻሽዬ እንደማስቀጠል እሱን ንቄ የመንግስት ስራ በምል አጉል ዝና በደሞዝ ተቀጥሬ ከወር ወር የማያደርስ ደሞዝ እየተቀበልኩ፣ ድሃ ሆኜ ቀረሁ። የአገሬ ገበሬ ዛሬ ላይ በወር 200 ሺ ብር እያገኘ ሀብታም ለመሆን በቅቶዋል። አብዘኛ የኢትዮጵያ ወጣት አሁንም አልነቃም። ስራ የሌለበት ከተማ ገብቶ ግማሹ ይራባል፣ ግማሹ እድሜዉን በማይረባ ስራ ላይ ይጨርሳል፣ የገበሬ ልጅ ሆኖ ሳላ ና ስራዉን የምችል መሆኑን እያወቀ፣ ሀብታምነትን ንቆ ድህነትን አሜን ብሎ ተቀብሎ ከተማ ተሸሽጎ የጉስቁልና ኑሮዉን ይገፋል። የፈረደበት!
ደደብ ወጣት ደደብነቱ እዉን ከተስተዋለ ደደብ ብሎ መንገር እና መቀስቀስ ተገቢ ነዉ።

ታታሪነታቸዉ በጣም የሚገርም ኣርሶ እና ኣርብቶ ኣደሮች ሃገር ወጣቱም ከእነሱ ተምሮ ታታሪ እንዲሆን ማስተማር ኣስቸጋሪ ኣይመስለኝም።

ስንቱን ስማ በለዉዎችን ሲሰማ የኖረ ቢሆንም።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ ሃገርን ኣደራጅቶ አደዋ የዋለዉ የኣፍርካ ጀግና ኣፄ ምንልክ ነዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ ተባብሮ ሃገር ያደራጀዉ ራስ ጎበና ዳጬ ነዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ ቃልቻ ቃሉን ቅኝ መግዛቱ ስለሆነ ቃሉ ከቃልቻ ነፃ መዉጣት ኣለበት።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ነዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ በኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የተማረዉ ደብተራ ነዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ የፕሮቴስታን ክርስትያን ኣለመሆንህ ስለሆነ ፓስተሩን ሉበ ብለን እናስተምረሃለን።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ መጽሓፉ የማይፈቅደዉ ባህላዊ ዘፈን ስለ ሆነ ተወዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ አባቶችህ እና እናቶችህ ምግብ ከተመገቡ በኋላ ማወራረጃ ብለዉ ፉት የሚሉዋቸዉ ባህላዊ መጠጦች ጠላ፣ ጠጅ፣ እና አረቄ ስለ ሆነ ተወዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ ጥንት ግዜ በኢትዮጵያዊያን የተፈጠረ ፊደል ነዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ ክረምት ኣለፈ ብሎ እሬቻን የማክበር ባህል ስለ ሆነ ተወዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ ይህ ሃገር በቀል አማርኛ ቋንቋ ነዉ፤ የእንግሊዞችን ቋንቋ ማንበብ እና መጻፍ ችሎታ ምሁርነት ነዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ የኣፍርካ ኣንድነትን ለመመስረት የለፉት ኣፄ ሀይለ ሥላሴ ናቸዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግርህ ወገን ባዩ የሃገርህ ሕዝብ ወገነ ኣይዴለም፤ ባዕድ ነዉ።

ስማ በለዉ፥ ችግሩን ለመፍታት ሸዋ ኢዝ ዲፕሊ እንፍልትሬትድ ባይ ወለጋ።

እነዚህ ሁሉ ስማ በለዉዎች ሲስተጋቡ ሁሉንም ቋንቋዎችን የሚሰማዉ እና ማፍራት ያልሰለቸዉ የኢትዮጵያ አፈር እዛዉ ነበር። ሁሉንም ቆንቆዎችን የምያርሰዉ የኢትዮጵያ ዉሃም ኢትዮጵያ ዉስጥ መፍሰስ ኣላቆመም።

የሰነበተችዉ የአዋሽ መልካሳ የምርምር ጣብያ ላዚህ ምስክር ናት፣ ታታሪ ሆነ የሰነበተች ከሆነ።

ይህን ሁሉ ስማ በለዉዎችን ሰምቶ ይህ ሁሉ ቅዠት ምንድነዉ ብሎ ኣለመጠየቅ ትልቅ ደደብነት ነዉ።

Post Reply