“ለካ ኣንተ ነህ”
“ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ”
ከነ ካድሬ ዺሲ ዶክተሬን ሁበቴራ?
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን በስም ማወቅ እንጂ በአካል ሳንተዋወቅ ነዉ ህይወቱ ያለፈዉ።
የጎሳ ዝምድና ስላለን ስለ እሱ ዝና መናገር ኣያምርብኝም።
ይህን ቪድዮ ለመጀመርያ ግዜ ያየሁኝ እና እነዚህን ስድስ ቃላቱን የሰማሁኝ የተወሰኑ ዓመታት በፊት ነዉ።
በእነዚህ ቃላት ምን ማለት እንደፈለገ ኣዉቃለሁ ማለት ኣልችልም። ቢሆንም ከሰማሁኝ ቀን ጀምሮ ግምት ኣለኝ።
ስለ ሎሬቱ ጥናት ሳላዉቅ በፊት ለረጅም ግዜ ኣስተዉዬ፣ ኣንብቤ፣ እና ኣሰላስዬ ከደረስኩበት የታሪክ ድምዳሜ ጋር ተመሳሳይ ሆኖብኛል።
በወጣትነቴ በርካታ ቤተክርስትያኖችን የተሳለምኩ ብሆንም እ ኣ አ ከ1992 ወዲህ ቤተክርስትያን ኣልሄድኩም።
አሜሪካ ዉስጥ ስኖር ኣንድ ግዜ የቦረና ባህል ኣዋቂ ነዉ የተባለ ሰዉ መጣ ተብሎ ፈልጌ ተገናኘን። ስታንፎርድ ዩኒቨርዚቲ ዉስጥ ይሰራ የነበረ ሰዉ ስምም ሰምቼ ስለነበረ እና ቦታዉ ከምኖርበት ብዙ የማይርቅ ስለሆነ በዩኒቨርዚቲዉ ዉስጥ ሁለቱ ሰዎች በተገኙበት ሀመቺሳ ቢደረግልኝ ብዬ ሀሳብ ኣንስቼ ችላ ተባልኩኝ።
ሀመቺሳ ክርስትና ከማንሳት ጋር ተመሳሳይ ነዉ።
የቦረና ሰዉ ጋር የተገናኘሁኝ ግዜ ሎሬት ጸጋዬ ቦረና ሄዶ ስለጻፈዉ ኣላዉቅም ነበረ።
የሬይነሳንስ ሰዎች ከሀይማኖት ማሳ ወጣ ብለዉ የባህል ማሳን የሚቃኙ ናቸዉ። ለረጅም ግዜ የተዘነጋ ማሳ ስለሆነ እዛ ማሳ ዉስጥ የሚገቡት በጣም ብዙ ነገሮችን ያያሉ፣ ያስተዉላሉ።
ለዚህም ኣንድ ሰዉ የሬይነሳንስ ሰዉ ነዉ ከተባለ ብዙ ነገሮችን ለመጀመርያ ግዜ ያስተዋለ፣ ያገኘ ተብሎ ይታወቃል።
የሬይነሳንስ ሰዉ ስሙ ከሳይንትስ በላይ ነዉ። ከፕሮፌሰር በላይ ነዉ። ከፈላስፋ በላይ ነዉ። ለረጅም ግዜ የተዘነጋ ማሳ ዉስጥ ገብቶ ብዙ ኣዲስ ነገሮችን ማግኘት ብቻ ሳይሆን ከእሱ በኋላ የሚመጡትም ማሳዉ ዉስጥ ገብተዉ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ማስተዋል፣ ማግኘት ይችላሉ።
ሬይነሳንስ ማለት ዳግም መወለድ ማለት ሲሆን በአማርኛ ኣንዳንድ ሰዎች ህዳሴን ይጠቀማሉ።
ለእኔ ከህዳሴ በላይ እዴሳ የተሻለ ቃል ይመስለኛል። እዴሳ ተዘንግቶ የነበረዉ ማሳ ላይ ብርሃንን ቦግ ማድረግ ማለት ነዉ።
ይህ ብርሃን ቦግ ሲል ሀዲ ወይም አዲ፣ እዴሳ፣ ኣዲስ፣ ህዳሴ እየተባለ የቃላቱን መመሳሰል ማጥናት ይቻላል። እየተጠናም ሕዝባችን በብዛት መሠረታቸዉ ኣንድ ነዉ ብሎ ሎሬቱ የደረሰበት ድምዳሜ ላይ ይደረሳል።
As far as I know, only few people in Ethiopia have reached at this conclusion.
In my view, the fact that he wrote the above six words some fifty years ago and reached a conclusion that many Ethiopians are struggling to reach at today makes him an Ethiopian Renaissance man.
He is the only person that I read about to have got various forms of the extremely competitive Fulbright scholarship four times. There are more scholars who received this scholarship and went on to win the Nobel Prize than those who received any other scholarship.
The late Ethiopian Laureate is also credited to have written the African Union’s anthem.
To belittle a genius like him, an Ethiopian Renaissance man whose observation is the farthest compared to any Renaissance man who came before him would be lacking of evolution.