Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6348
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

በስመ ኣብ፣ ኣብ ዳር፣ አባ ጋዝ

Post by Naga Tuma » 09 Jul 2025, 21:59

እዚሁ ፎረም ላይ ስለ አባ፣ ኣብ፣ አባት ቃላት በቅርቡ ተወያይተን ነበር።

ዉይይቱ ዉስጥ ከእነዚህ ቃላት ብቻ በመነሳት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጎሳዎች ብዙ ማወቅ ይቻላል ተብሎም ነበር።

ኣንድ የሆረስን ጽሑፍ ሳነብ አባ ጋዝን ኣስተዋልኩኝ።

ኣንድ የሴሰሜን ጽሑፍ ሳነብ ስለ ኣብ ዳር ኣስታወሰኝ። ኣድባር ወይም አብዳሪ ሲባል ኣብ ዳር ማለት እንደሆነ ኣላስተዋልኩም ነበር።

ኣሁን በስመ ኣብ፣ አባ ጋዝ፣ እና ኣብ ዳር ማለትን እያስታወስኩ ብዙ ኣሰላሰልኩ።

ስለ እነዚህ ቃላት ብቻ ምርምር ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊነት ብዙ ያስተምራል።

ስለ ምርምሩ ማሰላሰሉ የሚከተለዉን ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲዘፍን ወይም ሲዘምር ዛሬ በጠራራዉ ጸሓይ ኣሳለመኝ።

ታወቀ ኣሉ የእግዜር ቤት ተወዳሽ
የማያምን ሰዉ ኣይገኝም በጭራሽ
ደያብሎስ ከሆነ ኣይጠጋም በጭራሽ