ETHIOPIA & EGYPT: THE THUCYDIDES TRAP!
Egypt's issue with Ethiopia is not about water; it is about Ethiopia's emergence as East African regional power. Can Egypt stop Ethiopia? The answer is a definite no. Have a nice day.
Re: ETHIOPIA & EGYPT: THE THUCYDIDES TRAP!
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትክክል ነው። ኢትዮጵያን የከበቧት ትናንሽ ጠጠሮች ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን ሱማሌ ፣ ሱማሌላንድ ሁሉም በኢትዮጵያ ባህር ውስጥ ጠብ ቢሉ ባህር የሚያናጉ ማዕበሎች አይደሉም። እንዲያውም ሁሉም በመልከ ምድር፣ በሕዝብና ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ጋር ለዘላለም የታበቱ ፍጥረቶች ናቸው ። ስለዚህ ኢትዮጵያ ከነዚህ ትናንሽ ጠጠሮች ጋር በመነታረክ ታላቁን ጉዞዋ ፣ ታላቁን ትግሏ ማስትውጓጎል በፍጹም እስትራተጂዋ አይደለም ፣ ሊሆን አይገባም ። ያም እንዲሆን ነው ቁጥር 1 የኢትዮጵያ ጠላትና ምቀኛ ግብጽ እነዚህን ጠጠሮች እዚም እዛም እንዲወረወሩ የፕሮክሲ ወንጭፏን የምትወነጭፈው ። ኢትዮጵያ በተለቀችና በዘመነች ቁጥር የጠጠሮቹ ፕሮክሲ ዋጋ እየወደቀ እየረከሰ ይመጣል ። ኢትዮጵያ ለደቂቃም አይኗን ከዝመናዋና እድገቷ ማንሳት የለባትም ።
Re: ETHIOPIA & EGYPT: THE THUCYDIDES TRAP!





Last edited by Fiyameta on 03 Jul 2025, 12:49, edited 1 time in total.
Re: ETHIOPIA & EGYPT: THE THUCYDIDES TRAP!
Is Abiy really smart, surrounded by well-meaning, well-informed Ethiopians, or ወዳጃችን from the north ጨርሶ ያለበትን ክፉለዘመን ባለማወቁ አቢይ does seem smart in comparison.
Open for debate, discuss.
Open for debate, discuss.
Re: ETHIOPIA & EGYPT: THE THUCYDIDES TRAP!
አፈብል፣
ስለ መሪነት ምንነት ስናስብ ከዘመናት ተሞክሮና ዛሬ ደሞ ከሳይኮሎጂ ሳይንስ ግኝት የሚታወቁ መርህና ሞዴሎች አሉ ። ለምሳሌ ከነዚህ ማክሲሞች አንዱ አንድ ሕዝብ እራሱን የሚመስል መሪነትን ይወልዳል የሚለው ነው። አንድ ሕዝብ ከወስጡ የሚያወጣው የመሪነት አይነትና ብቃት ያ ሕዝብ በደረሰበት አጠቃላይ የሶሻል ሳይኮሎጂና ካልቸር ልክ ነው ። ይህ አንዱ ነው። አቢይ አህመድ በግላዊ ስብዕናው ምንም ይሁን ምን እንደ ድምር ውጤት ያገር መሪ የሚሆነው በተመሪው ሕዝብ ልክ ነው ። ይህን ስንል አቢይም ሆነ ኢሳያስ በግለሰብ ደረጃ ከዙሪያቸውና ሕይወት የመማር ፣ የመለወጥ ያላቸው መክሊት እንዳለ የኤርትራ ሆኖ ማለት ነው። ስለዚህ የኤርትራ ሕዝብና የኢትዮጵያ በፍጹም አንድ አይነት መሪነት አይፈጥሩም ፤ ሁለቱ ሕዝቦች በተሞክሮም ሆነ በውስብስብነት እጅግ በጣም የተለያዩ ስለሆኑ።
ሌላው በመሪነት ሳይንስ ወይም ሞዴል ውስጥ ያለው ሃቅ መሪነት ፣ የአመራር አይነትና የመሬንት ችሎታ ለአንድ ግለሰብ ገና ሲፈጠር ላንዴም ለሁሌም እንደ ሃብቱ የሚሰጠው ክህሎት አይደለም። መሪነት እንደ ማንኛውም ክህሎት ፣ እስኪል በሂደት የሚገኝ ፣ የሚዳብር ፣ የሚሞረድ ችሎታ ነው። ለዚህ ደሞ እንደ ኢትዮያ ያለ አስቸጋሪ ፣ ውስብስብና ተለዋዋጭ ትምህርት ቤት የለም። ስለዚህ ኢንተለጀንስ የሚባለው ነገር አንጻራዊ ነው ። አንድ የኔ ብጤ መሪነት ላይ ቢወጣ ቀድሞ ከነረው ችሎታ ይልቅ ካለው ሁኔታ በፍጥነት የሚማርና ስልትና አመራሩን የሚለውጥ ይበልጥ ስኬታማ መሪ ይሆናል።
ሌላው እውነታ አንድ መሪ በማንኛው የክህሎት ደረጃ ቢሆን ሕብረተሰቡን ወደፊት በመግፋት አዲስ ሃሳብ ፣ አዲስ እሴት ፣ አዲስ ተሞክሮ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ለግዜው ጥራዝ ነጠቅና ተስፈንጣሪ ቢባልም አዲስ ፋና ወጊና ፍኖተ እድገት የሚያመላክት ድፍረት ያለው መሆን አለበት ። ሕዝብ ባህሉ ሳይሸራረፍ በልማዱ ውስጥ ተደላድሎ መኖርን ቀላል ሆኖ ቢወደውም በሌላ በኩል የሰው ልጅ ለአዲስ ነገር ሁልግዜ ይበልጥ ዋጋ ስለሚሰጥ አንድ ስኬታማ መሪ በድፍረት አዳዲስ ነገሮች ማሳየት አለበት ። ለምሳሌ ይህን በተመለክተ አቢይ ኢሳያስን ይበልጠዋል።
ኢሳያስ በእድሜ መብሰሉ ብቻ ሳይሆን የኤርትራ ሕዝብ ጥቂትና ብሄራዊ አንድነት ስላለው ኢሳይሳ ምንም አይነት የሚፈትነው ሁኔታ አጋጥሞት አያውቅም ። ኢሳያስ የኢትዮጵያ መሪ ቢሆን ምን አይነት ችሎታ ይኖረው ነበር? ጥያቄው ይህ ነው። በሌላ በኩል ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ በ90 ጎሳዎች ተበጣጥሳ በትግሬ ኦሮምና አማራ የጎሳ ፖለቲካ እስከ መበጠስ ባትወጠርና አንጻራዊ ብሄራዊ አንድነት ቢኖራ ኖሮ አቢይ አህመድ ምን አይነት መሪ ይሆን ነበር? ሌላው ጥያቄ ይህ ነው።
ሌላው ቀርቶ እንደ ኢትዮጵያ መላ ቅጡ የጠፋውና ዝብርቅና ውስብስብ ሕዝብን ለአንድ ቀን እንኳ መምራት እራሱ ችሎታ አይደለምን?