Meleket wrote: ↑01 Jul 2025, 12:03
ለምንድን ነው ትግራይ ውስጥ 3 ብሄሮች ነው ያሉት የምትሉት? ከ3 በላይ ኣይሆኑም እንዴ? የሆነ የተዘባረቀ ነገርማ ኣለ!
የተዘባረቀ ነገር ቢኖር ነዉ እኮ ቤት ብሎ ቤተሰብ ከተባለ ሃገር ብሎ ብሔር እና እግዛብሔር ይባላል ማለት የማትችለዉ።
ቤት ብሎ ቤተሰብ ከተባለ ሃገር ብሎ ብሔር ይባላል ማለት ያልቻለ እንዴት ነዉ የመሃል እና የመስመር ዳኛ መሆን የቻለዉ?
ቤተሰብ ከመሃል እስከ ሃገር መስመር ነዉ እኮ።
እኛ በምናዉቀዉ ባህል ቤተሰብ ዉስጥ የተወለደ ልጅ ለአቅመ አዳም ከደረሰ ቀን ጀምሮ ቤተሰቡን ለማሻሻል፣ ለማበልጸግ፣ የቤተሰቡን ስም ከፍ ለማድረግ፣ ወዘተ ተግቶ መስራት የሚጠበቅበት መሆኑን ነዉ።
የተወልድክበት ቤተሰብ ዉስጥ የቤተሰቡ ልጅ መሆንህን እደራደራለሁ ብትል ሰዉን ታስቃለህ።
እዉነተኛ ጽምዶ፡ እዉነትን በመሸፋፈን እዉን ኣይሆንም። ገለጥለጥ አድርጋችሁ እስቲ ንገሩን! ያልገባንን እንዲገባንም ኣስረዱን! ለጨዋታ ያህል ነው!
ያልገባን እንዲገባን ነዉ እያልክ እንዴት ነዉ ለጫወታ ያህል ነዉ የምትለዉ?
ይህ በጀበና ዙርያ ቡና እየጠጡ የሚዝናኑበት ጫወታ ኣይዴለም።
ያልገባህን ሃምሳ ዓመታት ገደማ ወደ ኋላ ተመልሶ ለማስረዳት ተለፍቷል።
መቶ ሃያ ዓመታት ገደማ ወደ ኋላ ተመልሶ ለማስረዳት ተለፍቷል።
አምስት መቶ ዓመታት ገደማ ወደ ኋላ ተመልሶ ለማስረዳት ተለፍቷል።
ሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ ወደ ኋላ ተመልሶ ለማስረዳት ተለፍቷል።
ኣሁንማ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ገደማ ወደ ኋላ ተመልሶ ለማስረዳት እየተለፋ ነዉ።
ይህ ሁሉ ማስረዳት ግልጽ የምያደርገዉ ኣንድ ነገር ኣለ። የቤተሰብ በርጩማ ይነቃነቅ ሲባል የቤተሰቡ አባሎች ሁሉ ብቻ ሳይሆን ከቤተሰብ ዉጪ የሚኖሩ ብዙዎች የበርጩማዉ ረሃብተኞች የሚሆኑ መሆኑን ነዉ።
ለዚህ ነዉ ብልህ ቤተሰብ የቤተሰቡ በርጩማ ይነቃነቅ ከማለት በፊት ቢነቃነቅ ቀጣይነቱ እንዲህ ነዉ ብሎ ቀድሞ የሚዘጋጀዉ።
የሶስት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ገደማ ወደ ኋላ ተመልሶ ማስረዳት ሲገባደድ የኢትዮጵያ ፖለትካ የብሔር ፖለትካ ሳይሆን የጎሳዎች ቋንቋዎች ፖለትካ መሆኑ በጣም ግልጽ ሊሆን ይችላል።
ያ ለሁሉም ግልጽ ሲሆን በጀበና ዙርያ በበጩማዎች ላይ ተቀምጠዉ፣ እንደ ተከበሩት ንጉሶቹ፣ ፌደራሊዝም ለማለት ያልተኮላተፉት፣ በጎሳዎች ቋንቋዎች ቋንቋ ምን ማለት ነዉ? ቆንቆ ምን ማለት ነዉ? ሰበ ምን ማለት ነዉ? ሰብ ምን ማለት ነዉ? እያሉ ቆጥሬ መጨረስ የማልችለዉን መቁጠር ይችላሉ።
አሊ ብራ ራሱ ቢነሳ ቆጥሮ መጨረስ የሚችል ኣይመስለኝም። ምናልባት ብራን በሪኤ፣ ብርሃን ተኤ፣ ብራይት ጄዸሜ ብሎ የምያዝናናን በሰብኛ ያቀነቅን ይሆናል።
ያ ሲሆን አክሱም እና አምቦ ከተማዎች ዉስጥ ኖሮ የሁለቱንም ከተማዎች የጀበና ዙርያ ጫወታዎችን ተመሳሳይነት የወደደዉ እና ያደነቀዉ ሰዉ ዐይነት የኣንድ ቤተሰብ ዐይነት ጫወታ፣ የኣንድ ብሔር ጫወታ ሊሆን ይችል ይሆናል።