Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 37036
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ዕውቀትና ዕውነት

Post by Horus » 14 Jun 2025, 00:19

ሰላሳ ሚሊዮን ተማሪዎችና በመቶ ሺዎች አስተማሪዎች በአሉበት ኢትዮጵያ እከሌ ተብሎ የሚጠራና የሚጠቀስ አንድም የስነ ግንዛቤና የዕውቀት ፈላስፋ የሌለባት ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ መቶ ሰላሳ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ መኖሩ እጅግ የሚያሳዝና የሚያናድድ ነው። አቢይ አህመድ ይህ መሰረታዊ ርዕስ ከፖለቲካዊ ፕሮፓጋንዳና የፖለቲካ ተቃውሞ ጋር አያይዞ ቢያነሳውም በርግጥ ርዕሱ ከፖለቲካ ሙግት ብቻ ሳሆን ከትምህርትና ስልጠና ጋር መነሳት የነበረበት መሰረታዊ ርዕስ ነው ።

አቢይ አህመድ የተለያዩ ነገሮች አድርጎ አቀረባቸው እንጂ ዕውቀትና ዕውነት አንድ ነገር ናቸው። ዕውቀት ሳይንስ ማለት ነው ። በጣም ቀላልና ሌጣ ትርጉሙ ማወቅ አንድን ነገር ከሌላ ነገር መለየት ፣ ለይቶ መገንዘብ ማለት ሲሆን የቃሉ ግንድ አቅ ወይም ሃቅ ማለት ነው። ይህ በላቲን አንድ የአለ ነገር፣ የሆነ ነገር፣ የተደረገ ነገር ወይም ፋክት ማለት ነው። ይህን አቅ ወይም ፋክት ነው በትክክልም ያ ሲሆን ዕውን ፣ ዕውነት የምንለው ። ስለዚህ ዕውቀትና ዕውነት አንድ ነገር ናቸው ።

በትክክልም ዘመናዊ ሳይንሳዊ ትምህርት፣ ማንኛውም የትምህርት አይነት ከሂሳብ እስከ ሕብረ ትምህርት በይዘቱ ዕውነት መሆን አለበት ። ያኔ ብቻ ነው ተማሪው ዕውቀት ተማረ፣ አወቀ ማለት የሚቻለው። አወቀ ማለት ዕውነተኛ ሆነ ማለት ነውና። ዛሬ ላይ ይህ ባብዛኛው የማይታወቅና በዘፈቀደ የሚሻር ነገር ሆኖዋል። አስተማሪውም አብዛኛው የሚያስተምረው ሃሳብ ዕውነት ስለመሆኑ እራሱ አያውቀውም። ተማሪውም በሚማረው ሃስብ ዕውነተኛ ሰው መሆን እንዳለበት አያውቀውም።

ይህም ስለሆነ ነው ዛሬ ላይ አንድ ሰው በሃቅ የሌለ ነገር ፣ በኩነት ያልሆነን ነገር፣ በተግባር ያልተደረገን ነገር ከልብ ወልዶ በድምጽና ፊደል ከትቦ በመረጃ መልክ በሚዲያ የሚሰራጨውና ሰው ሁሉ ዕውነትና ውሸት ፣ እውቀትና ስህተት ሳይለይ እጅግ ግዙፍ የሃሳብና ተግባር ቀውስ ውስጥ የሚባክነው። በመሆኑም ዕውነትና ስህተት የማይለይ ማሕበረሰብ ደሞ ችግሩን በሃቅ መገንዘብ አይችልም ፣ ስለሆነም ለችግሩ መፍትሄ ሊያገኝ አይችልም።

አቢይ አህመድ ይህን ግዙፍ የዕውነትና ዕውቀት ችግር አሳንሶ ከፖለቲካ ጋር ብቻ አነሳው እንጂ የዘመናችን የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ብሄራዊ ጥያቄ ነው! ዕውነተኛነቱ ያልተረጋገጠ መረጃና ሃሳብ እንደ ዕውቀት የሚሰበክበት ማሀበረሰብ በጭለማ ወስጥ እንዳለ ይቆጠራል።