ለነገሩ ኢኮኖሚ እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል መለስ ዜናዊ አሳይቶህ አልነበር እንዴ?
ጤነኛ መሪ በአንተ ቦታ ቢሆን ኖሮ፣ አንተ ለጦርነት ያባከንከውን 60 ቢሊዮን ዶላር (30 ትግራይ፣ 10 አማራ እና 20 ኦሮሚያ) እንዲሁም እንደ ህፃን በብልጭልጭ ላይ ያባከንከውን 2.5 ትሪሊዮን ብር ለሚሊዮኖች የስራ እድል የሚፈጥሩ፣ የውጪ ምንዛሬ ወጪን በመቀነስ እና ገቢን መጨመር የሚያስችሉ፣ ወሳኝ መሰረተ ልማቶች፣ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ፕሮጄክቶች ለመስራት ያስችሉ ነበር። ለምሳሌ በመለስ ታቅደውና ተጀመረው የነበሮ ፕሮጄክቶችን፣ አንተ እንዲቆረጡ በማድረግ ገንዘቡን ለጦርነትና ብልጭልጭ መጫወቻእዎች ያዋልከውን እንይ።
ማዳበሪያ ፋብሪካዎች
* ያዩ ፣የሚፈጀው ገንዘብ 540 ሚሊዬን ዶላር ፣ 120 ሚሊዬን ዶላር ከወጣበት በኋላ ነው የተቋረጠው
* ዲረ ዳሞ፡ 2.4 ቢሊዮን
* አጠቃላይ የሚይስፈልገው ገንዘብ 3 ቢሊየን ገደማ ነው።
የስኳር ፋብሪካ
* ኦሞ-ኩራዝ ( አምስቱን ፋብሪካዎች)፦ ሊገኝ ይችል የነበረው ምርት 1.4 ሚሊዬን ቶን፣ የሚፈጀው ወጪ 3.8 ቢሊዬን ዶላር ነበር። ሶስቱ ፋብሪካዎች ተቋረጡ፤ሁለቱ በመለዋወጫ እጦች 35% ያክል ብቻ እየሰሩ ነው።
* ከሰም፦ ሊገኝ የሚችል ምርት 120,000 ቶን፣ ግንባታው የሚፈጀው ገንዘብ 460 ሚሊዬን ዶላር፣ ከመለዋወጫ እጦት የተነሳ በ 40% ብቻ እያመረተ ነው።
* ተንዳሆ፦ ሊገኝ የሚችለው ምርት 618,000 ቶን፣ የሚፈጀው ገንዘብ 720 ሚሊየን ( 700 ሚሊየን ከወጣበት በኋል የተቋረጠ)
* በአጠቃላይ እነዚህን የስኳር ፋብሪካዎች አጠናቆ በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስፈልገው ገንዘብ 5 ቢሊዬን ገደማ ነው።
የባቡር መንገድ
* አዲስ አባባ -ጂማ-ደምቢ-ዶሎ- ጋምቤላ ( 4.2 ቢሊዬን)
* አዲስ አበባ-ሃዋሳ-ሞያሌ ( 3.1 ቢሊዬን)
* አዋሽ -ሃራገበያ- መቀሌ ( 1.6 ቢሊየን_
* ከፊንፊኔ -ባህርዳር- መተማ ( 3.6 ቢሊዬን)
* እንዚህን ባቡር መንገዶች አጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት የሚስፈልገው ገንዘብ 12.5 ቢሊየን ነው።
እነዚህ አብይ ያስቆማቸውን ወሳኝ መሰረት ልመቶች እና ፋብሪካዎች ለመገነባት በአጠቃላይ የሚያስፈልገው ገንዘብ 20 ቢሊየን ዶላር ገደማ ነው። እንዚህ ፕሮጄክቶች ቢጠናቀቁ ኖሮ በብዙ ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራሉ፣ ብዙ ቢሊየን ዶላር የውጪ ምንዛሬ ያስገኙ ነበር።
አቢይ በሀገር ገነዘብ እቃእቃ ሲጨወት ከርሞ ማፈር ሲገባው አይኑን በጨው ታጥቦ ሊኩራራ ይሞክራል!
የአንድ ሀገር መሪ ሀላፊነት ሰፈር እየመረጡ ብልጭልጭ ማብራት ዛፍ ላይ እየጠመጠሙ አብሮ ፎቶ መነሳት አይደለም። የሀገር መሪ ሀላፊነት በእውቀት ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እና እቅድ ማውጣት፣ ብቃት ያላቸውን ሃላፊዎችን መልምሎ እንዲያስፈፅሙ ማሰማራት፣ ተፈጻሚነቱን በየጊዜው በመከታተለ እና በመገምገም ግድፈቶች ካሉ ማስተካከያ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው።