Horus wrote: ↑14 May 2025, 10:07
ከዚህ በኋላ የሚቀረው የዚህ ወንጀለኛ ቡድን ንብረቶችና ከነሱ ጋ የተያያዙ ሰዎችን ሃብት አንድ ባንድ በመቀማት ወደ ኢትዮጵያ ካዝና ማስገባትና እነዚህን ወንጀለኞች በተገኙበት በመልቀም ቃሊቲ ማጎር ነው!
The transition from TPLF to OPDO!
ሲንቄ ባንክንጨምሮ አሥር ድርጅቶችን በአንድ ጥላ ሥር የሚያስተዳድር ‹‹ሲንቄ ግሩፕ››
ሊመሠረት ነው
ሲንቄ ባንክን ጨምሮ ሌሎች በፋይናንስ አገልግሎት ዙሪያ የሚሠሩ አዳዲስ ኩባንያዎችን አካቶ በአንድ ጥላ ሥር የሚያስተዳድር ‹‹ሲንቄ ግሩፕ›› የተሰኘ ትልቅ ተቋም
ሊመሠረት መሆኑ ተገለጸ፡፡
ሪፖርተር ከሲንቄ ባንክ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከፋይናንስ ሥራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው አዳዲስ ተቋማትን በማደራጀትና ብራቹንም አንድ ላይ አካቶ
የሚያስተዳደርና የሚመራ ‹‹ሲንቄ ግሩፕ›› የተባለ ተቋም ለመመሥረት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቁሞ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።
‹ሲንቄ ግሩፕ› የሚለው ስያሜን በማስመዝገብ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱን የሚያመለክተው ይኸው የባንኩ መረጃ፣ በዚህ ግሩፕ ሥር እስከ አሥር የሚደርሱ
ኩባንያዎች የታቀደ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችልም ተጠቅሷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አምስቱ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙ ዘርፎች ሲሆኑ በዕቅዱ
መሠረት ራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ ይደረጋል፡፡
ራሳቸውን ችለው በኩባንያ ደረጃ እንዲቋቋሙ ከተደረገ በኋላ የሲንቄ ግሩፕ አባል ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት መካከል አንዱ ራሱ ሲንቄ ባንክ ሲሆን፣ ከባንኩ
በተጨማሪ ሲንቄ ኢንቨስትመንት ባንክ፣ ሲንቄ ሊዝ ፋይናንሲንግ፣ ሲንቄ ማክሮ ፋይናንስ የሚባሉ ተቋሞች ተደራጀተው የግሩፑ አባል እንዲሆኑ ይደረጋል።
ከእነዚህ የፋይናንስ ዘርፎች በአሁኑ ወቅት በሲንቄ ባንክ ሥር በምክትል ፕሬዚዳንቶች ደረጃ እየተመሩ የሚቀርቡ አገልግሎቶች ሲሆኑ፣ ከዚህ በኋላ ግን ራሳቸውን የቻሉ
ድርጅቶች ሆነው እንዲመሠረቱና የሲንቄ ግሩፕ አባል ሆነው በአንድ ጥላ ሥር እንዲመሩ ለማድረግ ውጥን ተይዟል።
ለመመሥረት የታቀደውን ሲንቄ ግሩፕን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሲንቄ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ንዋይ መገርሳ፣ በግሩፑ ሥር በፋይናንስ ዘርፉ ላይ ብቻ
የሚሠሩ የተለያዩ ኩባንያዎች እንደሚታቀፉ ገልጸዋል። እስካሁን የታሰቡት ወደ አሥር የሚደርሱ ኩባንያዎች መሆናቸውን የሚጠቁመው የፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ አሁን
በሥራ ላይ ከሚገኙት የፋይናንስ ዘርፎች በተጨማሪ አዳዲስ ኩባንያዎችም በግሩፑ ሥር እንደሚካተቱ ጠቅሰዋል፡፡ በኩባንያ ደረጃ ተቋቁመው የግሩፑ አባል ይሆናሉ
ተብለው ከሚጠበቁት አዳዲስ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የኢንሹራንስ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ባንኩ ከአገር ውስጥ አገልግሎቱ ባሻገር
ከኢትዮጵያ ውጭ ተወዳዳሪ ባንክ ለመሆን ውጥን ያለው በመሆኑ ይህንኑ ውጥኑን ዳር ለማድረስ የሚያስችል ራሱን የቻለ ኩባንያ ተቋቁሞ የግሩፑ አባል እንደሚሆን
https://www.ethiopianreporter.com/141308/