Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4380
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

BBC:እገታ የሚፈፀምባቸው ገርበ ጉራቻ፣ ቱሉ ሚልኪ እና አሊ ዶሮ አካባቢዎች ከአዲስ አበባ 200 KM በማይሞላ ርቀት ላይ ናቸው! መንግሥት ያደራጃቸው አካላት ድርጊቱን ይፈጽማሉ!!

Post by Za-Ilmaknun » 12 May 2025, 12:25

በየጊዜው በተለይም ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በሚወስደው መንገድ የሚፈፀመው እገታ በርካቶችን ስጋት ላይ ጥሏል። ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰነው የኦሮሚያ ክልል፣ በተለምዶ 'አሊ ዶሮ' በሚባለው አካባቢ ሰላማዊ መንገደኞች እና አሽከርካሪዎች ላይ በተደጋጋሚ እገታ እና ግድያ ተፈፅሟል::

ሐምሌ ወር ላይ ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ ከ100 በላይ ተማሪዎች ገርበ ጉራቻ ላይ ታግተው ከፍተኛ የማስለቀቂያ ገንዘብ ሲጠየቅባቸው የነበረ ሲሆን፣ የተወሰኑት የተጠየቀው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ሊለቀቁ እንደቻሉ ቢቢሲ በወቅቱ ዘግቦ ነበር።

በዚያው መስመር ላይ በዚህ ዓመት መጋቢት ወር መጨረሻ ላይም በሁለት የሕዝብ ማመላላሻ አውቶብሶች ላይ እገታ ተፈፅሟል።የእገታ እና የታጣቂዎች ጥቃት በብዛት የሚፈፀምባቸው ገርበ ጉራቻ፣ ቱሉ ሚልኪ እና አሊ ዶሮ አካባቢዎች ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 200 ኪሎሜትር በማይሞላ ርቀት ላይ የሚገኙ ናቸው።

በቅርቡ ወደ ዘርፉ የገባ 'ፈለገ ግዮን' የተባለ አውቶብስ 50 መንገደኞችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ እየተጓዘ ሳለ 'አሊ ዶሮ' በተባለ አካባቢ ሹፌሩ በጥይት ተመትቶ ተሳፋሪዎች ታግተው መወሰዳቸውን የጠቆሙት አንድ የትራንስፖርት ኅብረት ባለሥልጣን በበኩላቸው የየብስ ትራንስፖርቱ ዘርፍ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል ይላሉ።

ታጋቾቹን ለመልቀቅም ከመቶ ሺዎች እስከ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚጠይቁ ሲሆን፣ በአንዳንድ ሁኔታዎችም የመንገደኞችን ብሔር በመለየት ዒላማ እንደሚያደርጉ ከእገታ በሕይወት የተረፉ መንገደኞች ተናግረዋል።ሆኖም በአካባቢው መንግሥት ኦነግ ሸኔ ሲል በሽብርተኝነት የፈረጀው እና ]ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። ታጣቂ ቡድኑ ከዚህ ቀደም የቀረበበትን ውንጀላ ያስተባበለ ሲሆን፣ መንግሥት ያደራጃቸው አካላት ድርጊቱን ይፈጽማሉ ሲል ከስሷል።[/color]

https://www.bbc.com/amharic/articles/cy8n4y8vg2vo