“እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
የኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ ዘመን ተሻጋሪ ነጻ እይታና የማይናወጥ ጽኑ ኣቋም የነጠረበት፡ ከጦብያዉ ጠቅላይ ኣብዪ ኣሕመድ “እርካብና መንበር” የተሰኘ መጠሐፍ ይዘት ዙርያ ያጠነጠነ የነጣ እይታና ግምገማ ውጤት ነው! 2018 ላይ ያልተገኛችሁ፡ ኣርፍዳችሁ የመጣችሁ ወንድሞቻችንና እህቶታችን ትኮምኩሙ ዘንድ ተጋብዛችኋል፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና እንዲሁም ልበሙሉነት ጭምር!
viewtopic.php?f=17&t=168044&
viewtopic.php?f=17&t=168044&
Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑19 Oct 2018, 04:56“እርካብና መንበር” በሚል ርእስ፣ ጠቅላዩ የጣፉት ነው ተብሎ ከሚነገርለት መጠሃፍ እየቀነጨብን፣ ከጡሁፉዎም እየተማርን ገጡንም እየገለጥን ነጣ እይታችንንም አክለንበታል። በርግጥም “ዲራአዝ” ጠሃፊው ‘ዲቦራ+ራኬብ+አብይ+ዝናሽ’ ሁለቱ ልጆቻቸውና ባልናሚስት ተደምረው መሆኑ ልብ ተብሏል።
መታሰቢያነቱ - “በዚህ ደረጃ በልጅነት ወቅት ትዝታዬ በሕልም ፈቺነት ያላበሰችኝን ሠፊ ራዕይ፣ የቀረፀችውን ፅናት በዕውቀት ዘመኔ ደግሞ በዝናዬ አለሁ ባይነት ተደግፎና ተበረታቶ ለፍፃሜ የድል ማግስት መብቃቱን በልበ-ሙሉነት እመሰክራለሁ። ከመመስከር በላይ እነዚህ ሁለት ጀግኖች፣ ምትክ አልባ ህልም ፈቺዎችና ዓላማ አስጨራሽ መሆናቸውን በማመኔ የዚህች መጽሐፍ መታሰቢያነት ለሁለቱ የሕይወትና የፍቅር ፀበል መፍለቂያ ምንጭ ለሆኑት ለትዝታና ዝናዬ ይሁንልኝ።” ገጽ Vii ዝናዬ ባተቤተዎ ነች እማማ ትዝታ ደግሞ እናትዎ ይሆናሉ ብለን ገምተናል።
ከመግቢያው ክፍል ስንቀነጭብ
“ታሪክን ማወቅ ትናንትን በከፋ መልኩ ላለመድገም ትምህርት የሚገበይበት ምቹ የልምድ መሸመቻ ገበያ ነው።” ገጽ xvii
ለዚያም ነው ኤርትራዉያን ድንበራችንን አሁኑኑ በውሉ መሰረት በፍቅር አስምሩ የምንለው። ያገሬ ኤርትራና የኢትዮጵያ ድንበር የዛሬ 27 አመትም በወጉ ተሰምሮ ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ እልቂት ባልመጣ ነበር የሚሉም እኮ አሉ። ድንጋይ አንዴ ካደናቀፈህ - - - ነበር የተባለው።
“አበው በተረታቸው “መሪዎች ሲከፉ ዘመንም ይከፋል!” ገጽ xii - አበው’ማ ጥበብ የሞላቸው እማደሉ!
“በዘመናችን የርካብና መንበር መመላለሻ መንገድ የተጓዙት ጨካኝ መሪዎቻችን በጌጡ እየደመቁ የህዝቡን ሸክም ግን አብዝተው እና አጠንክረው ጫንቃው ላይ ቆልለው በማለፋቸው፤ ስልጣንም በኃይል እና በጉልበት እንጂ በፍቅርና በእውቀት የሚመላለሱበት ስላልነበር እርሱም ሳያንስ ይህ ቅንነት የታጣበት መንገድ በድንቁርና ታጅሎና በስውር ደባ ተጠላልፎ ዘመናትን እንዲሻገር በመፍቀዳቸው፤ በግሪክ አፈ ታሪክ ውስጥ ቋጥኝ ድንጋይ ከተራራ እግር ሥር ወደ ተራራ አናት እድሜ ልኩን እንዲገፋ በአማልክት እንደተፈረደበት ምስኪን ዜጋ እኛ ኢትዮጵያውያንም የተጫነንን የታሪክ ቋጥኝ ሥንገፋ ዘመናት ተቆጥረዋል። ከተራራው እግር ሥር ያነሳነውን ቋጥኝ ከተራራው ጫፍ በታላቅ ስቃይ አውጥተን አደረስን ብለን ለአፍታ እንኳ እረፍት አግኝተን ልባችን ሳይሞላ ድንጋዩ ወደነበረበት የተራራ እግር ስር ተንከባሎ የኋሊት እየተመለሰ ይሄው ዘላለም ዓለማችንን ከተራራው ጫፍ ተደላድሎ የማይረጋ እና እፎይታ! የማይሰጥ የመከራ ቋጥኝ ስንገፋ አለነው። መኖር ከተባለ።” ገጽ xviii
ይህን አገላለጽዎ በተመለከተ ሰፊው ያዲሳባ ህዝብ እንዲሁም ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ አስተያየቱን ሊሰጥበት ይችላል። በተለይም መጨረሻ ግድም ያስቀመጡት ሃቅ ጦቢያ ያለችበትን ሁኔታም ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ይመስላል። ኣቱ ነብይ ነዎት መሰል? ቢሆኑ ምን ግዴ! ሰራዊትዎን ካገሬ ምድር ያውጡ ብቻ። ሰራዊትዎ በምድሬ የሚቀመጥበት ምንም ዓይነት ምክንያታዊነት የለም፤ በምንም መልኩ ምክንያታዊ ሊሆን አይችልም። የሰው ገንዘብ አይመኙ። ስጋታችን “ከተራራው እግር ሥር ያነሳነውን ቋጥኝ ከተራራው ጫፍ በታላቅ ስቃይ አውጥተን አደረስን ብለን ለአፍታ እንኳን እረፍት አግኝተን ልባችን ሳይሞላ ድንጋዩ ወደነበረበት የተራራ እግር ስር ተንከባሎ የኃሊት እየተመለሰ እንዳይሆን ነው።” ድንበር የሚባል ነገር የለም ነበሩ ያሉት?” በርግጥ ደፋር ነዎት ቀልደኛ ቢጤም ነዎት፣ እኛ “ለድንበር ሲል ነው ጀግና የተሰዋው እኮ ነው የምንል!”።
ክፍል አንድ
“ ‘ችግሩን በፈጠረው አስተሳሰብ፣ ችግርን መፍታት አይቻልም’ አልበርት አንስታይን” ገጽ 1
የጦቢያን የአዲስ ዘመን ችግር የትግራዩ ጎጠኛ አስተሳሰብ ነው የፈጠረው፣ ዛድያ ይህን ጎጠኛ አስተሳሰብ በአዲስ ጎጠኛ አስተሳሰብ መፍታት አይቻልም ሲሉ ሰምቻለው አዲስአቤዎች፣ በርግጥ እውነታቸውን ነው! አንስታይንም እውነቱን ነው።
ምዕራፍ አንድ “የዘመኑን ሥጋትና ጥሪ መጋፈጥ”
“የህግ የበላይነት እለት በዕለት ዕየተሸረሸረ ቀጥኖ ሊበጠስ ሲቃረብ የግለሰቦች ህግ አብቦ ይፋፋ ጀምሯል።” ገጽ 4 - የደንበሩ ብይን ከተበየን ስንት ዓመት አድርጎ የለ፣ ዛድያ የህግ የበላይነት ሳይተገበር በእርስዎ እንቢ “ደንበር የሚባል ነገር አላውቅም” ባይነት ይሀው እስተዛሬ የግለሰቦች ህግ አይደል እንዴ እየተንፈላሰሰ ያለው። አረ ጡር አለው! ዲንበሩን መሬት ላይ ወርዴየው ያስምሩ! ዴሞ ችግሩን በሌላ ሰው ላይ እንዳያላክኩ!
“ከአንዳንድ አካላት ዘንድ የሚንጸባረቅ አጥፊ አስተሳሰብ እንዲሁም በህብረተሰቡ የጋራ ጉዳይ ላይ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን ውሳኔ ሰጪ የሆኑ አካላት በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የግጭት ሥጋት ጥላውን እንዲያጠላ ተጠቃሽ ምክንያት ሆነው እናገኛቸዋለን።” ገጽ 5
“ምንም እንኳን አንዳንድ ሀገራት ህዝቦቻቸው የበለጸጉ ቢሆኑም በተቀረው ዓለም የሚገኙ የሰው ልጆች ግን ድህነት በሚባል ሠንሰለት ተጠፍረው፤ አሰቃቂ በሆነው የርሃብ፣ የዝቅተኝነት፣ በይሉኝታ የመሸበብ እና በጠባቂነት አለንጋ እየተገረፉ፣ የማይሽር ቁስላቸውን እያስታመሙ፤ የማይፋቅ ጠባሳቸውን እያስታወሱ፤ የማይታበስ ዕንባቸውን እያፈሰሱ እና ነገን በተስፋ እያለሙ፤ ሊነጋ ሲል በሚጨልም ፅልመት ውስጥ አንገታቸውን ደፍተው እናገኛቸዋለን።” ገጽ 6 - ኣረ ቢያንስ ቢያንስ ያፍሪካን ቀንድ እያሰቡ ደግመው ያንብቡት!
“ለሰው ልጆች ችግር መፍቻው ቁልፍ በሰው እጅ የመሆኑን ያህል ችግሮቹን ከናካቴው ለማስወገድ እንዳይቻል ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ ራሱ ሰው ነው። ገሚሱ ለችግሮች መፍትሔ ሲያፈላልግ ገሚሱ ደግሞ የመፍትሔው ማርከሻ ችግር ማፈላለግ ላይ ተጠምዶ ይውላል።” ገጽ 7 - እርስዎስ? የዲንበሩን ውሳኔ ትግባሬ መፍትሔ ማርከሻ ችግር ማፈላለግ ላይ ተጠምደውና ተጥደው እየዋሉም አዴል?
“የሞት ፅዋን ከመጎንጨት ያመለጡ ተስፈኞችም ቢሆኑ ከመኖር ወድያ እና ከመሞት ወዲህ ተጥለው የልዕለ ተፈጥሮን ረድኤት ይጠብቃሉ፣ ብዙዎች ቤት ንብረታቸው ወድሞ ባልተጠበቀ ሁኔታ ኑሯቸው ተመሰቃቅሎ አሁን ብቻ ለሚኖሩበት ጊዜያዊ መጠለያ ካምፕ፣ ገሚሱ ለባይተዋርነትና ስደት፣ የተቀረው ደግሞ ሰብዓዊነት ለራቃቸው ነፍስ በላዎች የገቢ ማስገኛ አዲስ የስራ ዘርፍ መፍጠሪያ በመሆን የመከራ እና የሰቆቃ ህይወት መግፋት ዕጣ ፈንታቸው ለመሆን በቅቷል።” ገጽ 8 - በርግጥ ለህግ የበላይነት አለመገዛት የሚያመጣው ችግር ነው። በዝጌሩ ዲንበሩን አስምሩ።
“በተለይም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ሕይወታችን ውስጥ የጋራ ተጠቃሚነታችንን የማረጋገጥ የኃላፊነት ቀንበር የተጫነባቸውና ለርሱም ተፅእኖ መፍጠሪያ ኃይልና ሥልጣን በጃቸው የጨበጡ ቀዳሚዎች፣ አስተዳዳሪና መሪዎች ለአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል። በሙሉ ዓይን ከችግራችን ጋር መተያየት አቁመዋል።” ገጽ 11 - ዲንቅ ብሌዋል፣ የዲንበሩን ውሳኔ ትግባሬ በሙሉ ዓይን ማየት አልቻሉም፣ አረ ጀሮ ዳባ ልበስ እያሉት ነው “ድንበር ብሎ ነገር የለም እማደል ያሉት!
“ትክክለኛ መፍትሄ ያልተሰጣቸው ችግሮቻችን ዘመን ሲያስቆጥሩ ትክክል ያልሆነን መፍትሄ የችግር መፍቻ አድርገው ቢወስዱ አያስገርምም። በዚህ ሂደት መወቀስ ያለበት ለችግሩ መፍትሄ ያጣው በሽተኛ ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ መፍትሄን የነፈጉት ሐኪሞችም ጭምር መሆናቸው አሌ አይባልም። ውጤቱም የዜሮ ድምር ነው።” ገጽ 11 - አረ ጉድ የቤተስኪያን መባ የሰረቀ ራሱ ይለፈልፋል አሉ፣ የድንበሩን ብይን ትግባሬ በተመለከተ እኳ ራስዎ ‘ትክክለኛ መፍትሄን የነፈጉ ሓኪም ነዎት፣ ምክንያቱም ትክክል ያልሆነን መፍትሄ የችግር መፍቻ አድርገው ሲወስዱ እያየን ስለሆንን።
“መፃኢ ዕድልን በጥሩ መሠረት ላይ ለመገንባት የኅብረተሰብን ተሳትፎ ማረጋገጥ መቻል ወሳኝ ነገር ነው። የሀገር ጉዳይ የኔ ጉዳይ ነው፣ ብሎ የሚያምን ኅብረተሰብን መፍጠር የቻሉ ሀገራት ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በቀላሉ መቋቋም ተችሏቸዋል። ምክንያቱም እኚህ ዜጎች ለሀገር ደህንነት ዘብ ናቸውና። ነገር ግን ህዝብን ወደኋላ ገሸሽ የሚያደርጉ መንግሥታት ሳቢ ተገቢ ምላሽ መስጠት ይሳናቸዋል። በአንፃሩ በአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ወይም በጥቂቱ አዋቂ በሚባሉ አካላት ከሚደረግ የተናጠል ጥረት ይልቅ በጋራ የሚደረጉ ጥረቶች እጅግ ውጤታማ መሆናቸው እሙን ነው።” ገጽ 15 -ጠቅላዩ ኅሊናዎ ምን እያለ ነው! ቃልዎ ረታዎ አይደል! ቃልዎ ጠቀለልዎ አይደል። እንደዚያ ነው።
ተቻልኩ ምዕራፍ ሁለት “ጀግንነት፣ ጀብዳዊ ጭካኔና ጀብዳዊ ቅንነት” የሚለው ክፍልን በቀጣይ እቃኛለው!
እውነተኛ ፍትህ ላዲሳበቤዎች!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
Meleket wrote: ↑20 Feb 2025, 04:50[ሰሞንኛዉ ኤርትራዊ ኣጭር ግጥም] - አንት ብልጽግና አንተ ወያኔ . . . .
ድሮ ድሮ እንዲህ ይባል ነበር
አንተም መላጣ እኔም መላጣ
ምን ያጣላናል በሰው ሰላጣ።
ዘንድሮ ደግሞ
አንት ብልጽግና አንተ ወያኔ፡
ምን ያጣላናል በሄግ ብያኔ!![]()
https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=308857&

Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑20 Oct 2018, 11:00
እንደዋዛ የጀመርነው የክቡር ‘ዲራአዝ’ ጥሁፍ ብዙ ቁምነገር እየሸመትንበት ነው። መጣሃፉን የጠቆማቹን ወንድሞችና እህቶች እናመሰግናለን። እንዳጀማመራችን እያዋዛን እንማርበት በሉ።
“ታላቁ እስክንድር የተወለደው በ356 ከክርስቶስ ልደት በፊት በፔላ መቄዶንያ ነበር። አባቱ ንጉስ ዳግማዊ ፊረና ሲሆን እናቱ ደግሞ አሎምፒስ ነበረች። እናቱም የመቄዶንያ ነገስታት የግሪክ አምላክ የሆነው የዜውስ ልጅ የሄርኩለስ ዝርያዎች መሆናቸውን ለእስክንድር ታስተምረው ነበር። እንደ እናቱ አባባል ከሆነ የእስክንድር ቅድመ አያት ኦሊያድ በሚባለው የሆሜር ግጥም ውስጥ የተገለፀው ጀግና አርኪላስ ነው። በመሆኑም ወላጆቹ ድል የማድረግና ንጉሳዊ ክብር የመቀዳጀት ምኞት ስለቀረፁበት ወጣቱ እስክንድር በጊዜው ወደ ጦር አምባ ፊቱን ለመመለስ በጦር ግንባርም ለመሰለፍ ሊገፋፋ ችሏል። ምንም እንኳን አርስቶትል እስክንድርን ፍልስፍና ሊያስተምረው ቢፈልግም እስክንድር ግን “የጀብደኛው አርኪለስ ዝርያ ነኝ” የሚለው የጀብደኛነት መንፈስ በውስጡ ስላደረበት ጦረኛ ለመሆን ተገደደ።” - - - - “ በዚህ ባለንበትና ከትላንት የማይሰምር ሌላ ዘመን በጠባበት እንግዳ የዕድሜ ካብ ላይ ሆነን እንኳን ከአርኪለስ እስከ እስክንድር በሚዘረጋ የ“በሆንኳቸው” ጀብደኛ ምኞት ጋዲ ታስረው ሳይተኙ የሚያልሙና የሚቃዡ እዚህም እዚያም ብቅ ሲሉ ማስተዋል እንግዳ ክስተት አይደለም።” ገጽ 20 – 21
ግሩም ጠቅላይን የሚገልጽ ገላጭ የጥቅስ ላይ ጥቅስ ነው!
“ስለ ጥቂት ንጉሳዊ ቤተሰቦች ንግግር ማመን የምንችለው ከንጉሶች በስተጀርባ ስላለው ምስኪን ህዝብ እርግጠኛ መሆን ስንችል ብቻ ነው።” ገጽ 23
ይችም ድንቅ የጠቅላይ ጥቅስ ነች።
“ ‘ልጅ የሚበላውን ይመስላል’ እንደሚባለው ሁሉ ጋንዲም በልጅነቱ ወቅት የእናቱ ፑትሊባ ሃይማኖታዊ የቀኖና ጻድቅነት ከፍተኛ የመንፈስና የሞራል ጥንካሬ እንዳሳደረበት ጸሃፊዎች ያስቀምጣሉ።” ገጽ 24
“በኢትዮጵያ ማህበረሰብ በገጠርም በከተማም፣ በተለያዩ ብሄሮችም ሆነ ሀይማኖቶች ለልጆች በጨቅላ ኣዕምሯቸው የሚነገሩ ተረቶች ታሪክ ምን ይመስላል? አብዛኛው ጊዜ በተረቶቹ ውስጥ ገጸ ባህሪ ሆነው የሚቀረጹት እንስሳት እነማን ናቸው? የሚወክሉት የህይወት ጠባይስ ምንድነው? የሚለውን ወስደን ጥናት ብናከናውን በጣም ከሌሎች ጎልቶ የምናገኘው መልስ በአህያ፣ ጦጣና አንበሳ ዙሪያ የሚሽከረከር ነው። አህያ በላቡ ጥሮና ግሮ የሚኖር እንስሳ እንደሆነ ቢታወቅም በተረቶቻችን ውስጥ ያለው ውክልና ግን እንደ ጅል፣ የማይረባ እና ሁልጊዜም ተሸናፊ ተደርጎ ይቀርባል። በተቃራኒው ጦጣ ብልጣብልጥ፣ አጭበርባሪና ተንኮለኛ ተደርጋ የምትቀርብ ሲሆን ብዙ ጊዜ ሁኔታዎችን በአሸናፊነትና በበላይነት እንደምታከናውን ይተርካል። አንበሳ ደግሞ ጉልበተኛ፣ ደፋርና አስፈሪ ተደርጎ ይሳላል። በመሆኑም የአገራችን ትርክት የአህያን ማንነት ሳይሆን የሚያበረታታው የጦጣንና የአንበሳን ማንነት ነው። ይህ ማለት ደግሞ በላቡ ለፍቶ ጥሮ ከመኖር ይልቅ አጭበርብሮና ቀልጣፋ ሆኖ በብልጠት መኖርን ወይም ደግሞ በጉልበት አስፈራርቶ፣ ቀምቶና ተደባድቦ መኖርን የሚደግፍ በመሆኑ በአብዛኛው የማህበረሰብ እርከን ማለትም በንግዱ ዘርፍ በተሰማሩ፣ በፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች አመራርነት ላይ በሚገኙ ወይም በጠቅላላው ማህበረሰብ ዘንድ ይህ ስብዕና ተገንብቶ ይታያል።” ገጽ 26
ድንቅ ነው አሁን እርስዎ የጦጣን የአንበሳን ወይስ የአህያን ባህሪ ነው የተላበሱ። “ድንበር የለም” የሚሉት ማጭበርበር ከየት የመጣ ፈሊጥ ነው? ኤርትራውያን እንደሆንን “ቃል እንደሚተክልና ቃል እንደሚነቅል” ስለምናውቅ ቃልኣባይ ሰው ሲያጋጥመን እንዲህ እያልን እንገጥማለን እየተንገዳገድንም ቢሆንም እንቀኛለን። ለምሳሌ እስዎን እንዲህ እያልን ምክራችንን እንለግስዎታለን።
ቃልዎን ያድሱ ቃልዎን ያክብሩ ፣
ድንበር የለም ብለው ሰው አያጭበርብሩ።
ምዕራፍ ሶስት “ኃይልና ሥልጣን”
“ሥልጣን ያባልጋል! እውነት ነው፥ ፍጹማዊ ሥልጣን ደግሞ የባለጌ ባለጌ እንደሚያደርግ የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጎርጎሪያ ሶስተኛ የተናገሩት ሀሳብ ግሩም ምስክር ይሆናል። ነገር ግን ይህም ታውቆ እንኳን ዛሬም እንደ ትላንቱ ‘ስልጣን’ የአያሌዎችን ልብ እያጓጓች፤ ልክፍት በሚመስል አስፈሪ ፍቅሯ እንደማግኔት ትስባቸዋለች። ድሮም ሆነ ዘንድሮ የመንበር ጥማት ያው የመንበር ጥማት ነው፤ ከብዙዎች ልብ ተፍቆ አልወጣም። ስልጣን፣ ቢሰሩባትም ባይሰሩባትም እርካቧን የረገጠ፣ ኮርቻውን የተቆናጠጠ፣ መንበሯ ላይ የተደላደለ ሁሉ (ቢያንስ አብዛኛው) በሞቱ እንጂ በፈቃዱ ሊለያት የማይሻ በ‘ጦሰኛ ፍቅሯ’ ተቀፍድዶ ኖሯል። አፍቃሪዋም ዘመኑን ሁሉ ሲጨነቅና ሲጠበብ ዕድሜውን የሚገብርላት፣ የክበሩ ዘውድ፣ ወይም የመራራ ውርደቱ ፅዋ ትሆናለች፤ ሥልጣን።” ገጽ 29-30
የሊቀጳጳሱ ምስክርነት በርግጥ ግሩም ነው፣ ፍጹማዊ ሥልጣን ማባለግ ብቻ ሳይሆን የባለጌ ባለጌ ያደርጋል። ፍጹም ሥልጣን ከተቆናጠጥክ እኔ ብቻ የሚል ሃሳብ ይቆጣጠርሃል፣ በሥልጣንህ “ድንበር ማለት ትርጉም የለውም” ብለህ ካሰብክ የህዝብንና የዓለምን ስሜት እንደሌለም ቆጥረህ፤ ባለም አደባባይ የተቀበልከውን በቃልህ ያወጅከውን ብይንም ለማጣጣል ትሞክራለህ። ዓለምና ህዝብም በውስጣቸው እየሳቁ ይታዘቡሃል፣ እያሳሳቁም መራራዋን የውርደት ፅዋ አስጎንጭተው ይሸኙሃል፣ በሥልጣን ከባለግክ እንዲያ ነው የሚያደርጉህ።
“አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ዮሃንስና አፄ ምኒሊክ የስልጣን ጥም እንደነበራቸው። ዮሃንስ ሟቹን ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ሊወጋ የመጣውን የእንግሊዝ ሠራዊት በመርዳት ከሸኚ እና ስንቅ ጋር በግዛታቸው እንዲያልፍ በማድረጋቸው ወሮታውን ከድሉ በኋላ በዘመናዊ መሣሪያ፤ መድፍ እና ጥይት አበልጽጓቸው ሲሄድ በጊዜው ከነበሩት መሪዎች ሁሉ የላቀ ኃይል ለማግኘትና የንጉሠ ነገሥትነት ዘውድ እጃቸው ለማስገባት አመቻቸላቸው። አፄ ምኒሊክም ኢትዮጵያን ጠቅልሎ የማስተዳደር ፍላጎታቸውን ለማሟላት ንጉስ ከመሆናቸው በፊት በተለያየ መንገድ ግዛታቸውን በደቡብና በምዕራብ አቅጣጫ እያስፋፉ ኃይላቸውን ከምዕራባዊያን ከሚያደርጉት እርዳታ በዘመናዊ መሣርያዎች እየታጠቁ ቀናቸውን ሲጠብቁ ኑረው በስተመጨረሻም ፍላጎታቸውን አሟልተዋል።” ገጽ 31
እርስዎስም ሆኑ ወንድሞችዎና እህቶችዎ “ኢትዮጵያውያን” በኛ በኤርትራውያን ላብና ደም እንዲሁም የህይወት መስዋእትነት አማካኝነት ምን ምን ዓይነት “እርዳታ” እንደተደረገላችሁ መቸም አይስቱትም፣ ለእውነት የቆሙ ከሆኑ “ዲንበሩን ካሰመሩ በኃላ” በሚቀጥለው መጥሃፍዎ “የኤርትራዉያንን አስተዋጽዖ” በዚ ብርቅ ብዕርዎ አማካኝነት ይጥፉት ይሆናል ብለን እንገምታለን።
“አጼ ኃይለ ሥላሴ ኢትዮጵያና ህዝቧን፣ መሬትና አየሯን ሳይቀር ርስታቸው አድርገው በሥልጣን ርካብና መንበር ከልጅነት እስከ ዕውቀት የተጓዙ የቅርብ ዘመን ንጉሥ ነበሩ። ንጉሡ ከ44 ዓመታት በላይ በመግዛት ቢዘልቁም በቃኝ፣ አረጀሁ፣ ደከምኩ፣ . . . ብለው በህዝብ ለተመረጠ መሪ ማስረከብ ቀርቶ ከአብራካቸው ለወጣውና አልጋ ወራሽ ላደረጉት ልጃቸው እንኳን ማስተላለፍ ሳይችሉ ከዚያው፣ “ሞቴም ሕይወቴም” ካሉለት መንበር በደርግ መጀመሪያ ወደ ወህኒ ቀጥሎም ወደ መቃብር ተሸኝተዋል። ገጽ 31
ግሩም አገላለጽ፣ ሥልጣን የባለጌ ባለጌ እንደሚያደርግ የሚያሳይ ግሩም አገላለጽ ነው። የሚገርመው ግን በዓለም አሁንም ከኒህ አጼ ሆነ ተመሳሳይ ታሪክ ካላቸው ሥልጣንን “ሞቴም ሕይወቴም” ይሉ ከነበሩ ሰዎች ዓለማችን አለመማሯ ነው! አይደል? እርስዎ ተምረዋል “አሸጋግራለው” ነው ያሉት አይደል? ዲንበራችንንም በቅጡ አስምረው ካለመሰመር ወደ መሰመር “ያሸጋግሩት” እንጂ!
“ሥልጣንን ለዝናና ክብር ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል ሲሉ ብቻ የሚፈልጓት ጥቂቶችም ቢሆኑ መኖራቸው ግን ሃቅ ነው፣ ለጭቦና በደል፣ ለመከራና ግፍ ሳይሆን በተፅዕኗቸው ሀገርና ሕዝብን ለመለወጥ ሌት ተቀን የሚለፉ መሪዎችም ነበሩ፤ አሁንም አሉ። ማህተመ ጋንዲን አንድ ብለን ብንነሳ፣ ቼጉቪራን፣ ጎርባቾቭን፣ ቫክላቭ ሃቬልንና ማንዴላን በአርዓያነት መጥቀስ እንችላለን።” ገጽ 32
ምነውሳ ምሳሌ ሲያቀርቡ የነበሩትን አበርክተው ያሉትን አሳነሱሳ፣ ለነገሩ “ጥቂቶች” ናቸውም ብለዋል።
“በተጨማሪም ‘መንበሩን ከምለቅ ወገቤ ይላቀቅ!’ ከማለት ይልቅ” ልክ እንደዚያ እንደተራው ወንበር በማየት ሳይሞቱለት ወይም ሳይገድሉ በቃኸኝ! ብለው የሚሰናበቱ መሪዎችንም ዓለማችን አስተናግዳለች። የታንዛኒያው ጁሊየስ ኔሬሬ መንበሩን በገዛ ፈቃዳቸው ደህና ሰንብት ብለው ወደ ትውልድ መንደራቸው ተመልሰው ገበሬ በመሆን ለአፍሪካ የመጀመሪያው መሪ ናቸው። የእንግሊዙ ልዑልና አልጋ ወራሽ እንዲሁ ፍቅሬ ይበልጥብኛል፤ በማለት ዘውዱን ከአናቱ አውርዶ ከፍቅረኛው ጋር አሜሪካ ገብቷል። የቫቲካኑ ሊቀጻጻስ ጆን ቤኔዲክትም ቢሆኑ ከስልጣን መንበር የገዳም ፀሎት በስንት ጣሙ! በማለት በገዛ ፈቃዳቸው ለተተኪ አስረክበው ገዳም ገብተዋል።” ገጽ 33 -
ኤርትራችንም ከነዚህ ጋር የሚመደቡ አሏት፣ ታጋይ ሮመዳን መሃመድ ኑርም ይባላል፣ ታሪኩን ቀስ ብለው ፈልገው ያንቡት። ኢትዮጵያዊው ኃይለማርያም ደሳለኝ ግን በዚህ ኣይካተትም ምክንያቱም እሱ ቀድሞውኑም ልክ ሳይክል ላይ እንደሚፈናጠጥ ህጻን “ተፈናጦ” የነበረ ነውና፣ ዴሞም ወዶ ሳይሆን ‘አላሰሩኝ አሉ’ ብሎ ነው የወረደው። ኃይለማርያም ከነዚህ ጋር ከተቆጠረ፣ መንጌም የማይቆጠርበት ምክንያት የለም ቢባል ቀልድ ይመስል ይሆንን?
“ - - ስለዚህ ከፍቅር ይልቅ በትር ለመከበር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው። ይህ ማለት ግና ‘በምድር ላሉት እዘኑ በሰማይም ያለው ያዝንላችሁ ዘንድ’ የሚለውን አስተምህሮ ወደ ጎን በማለት ወሰን ማለፍ እንደሚገባ ለማሳየት አለመሆኑን መረዳት ያሻል።” ገጽ 35
እኛም የጠላነው ይህን ነው ወሰን ወይ ደንበር ማለፍ አይገባም፣ “አባቶችህ ያቆሙትን የድሮውን ወሰን አትጣስ!” የሚል ተጥፎ የለ።
“በትርን ብቻ ተመራጭ አካሄድ አድርጎ መውሰድ የራሱ ድክመት እንዳለው ኒኮሎ ማኪያቬሊ ይናገራል። ምክንያቱም መስፍኑ ህዝቡን በማስፈራራት ከሱ ጋር ማድረግ ቢችልም የችግር ቀን ግን መጀመሪያ አሳልፎ የሚሰጠው ያኔ በመንቀጥቀጥ ሲሰግድለት የነበረው ህዝብ ስለሚሆን ነው። ለዚህ ደግሞ የደርግ መንግሥትን የመሰለ ማሳያ አይገኝም።” ገጽ 35
አረ ያያ አህመድ ልጅ ምነው’ሳ የሊቢያው ጋዳፊና የኢራቁ ሳዳምን ረሷቸው’ሳ?
“አንዳንዴ ደግሞ መስፍኑ የተለበጠ ማንነት ሊኖረው ይገባል። - - - በፍቅር ወቅት መልዓክ በአመጽ ግዜ ግን ሰይጣን ሊሆን እንደሚችል ማሳወቅ አለበት።” ገጽ 36
ምን? “የተለበጠ ማንነት” ብሎ ዝም ነው እንጂ! “በፍቅር ወቅት መልዓክ በአመጽ ግዜ ግን ሰይጣን” እንዴት እንዴት ነው “በፍቅር ግዜ መልዓክ በአመጽ ግዜም መልዓክ” መሆን አይቻልም ማለት ነው? ይቻላል “ቤተመንግሥት ድርስ ታጥቀው የመጡትን ወታደሮች ‘አማጽያን’ በፍቅር መቀበል፣ በአመጽ ግዜ መልዓክ ሆኖ ‘ፖሽ አፕ’ ማሰራት ረቂቅነት ነው። ረቂቅነቱ ይቆይልዎና፣ ታገሬ ከኤርትራ መሬት ያሉ ሰራዊትዎን ግን በፍቅር ያውጡ፣ ድንበሩንም በፍቅር ያስምሩ።ጎሽ የኛ ረቂቅ!
“መቼም ሥልጣን ዝም ብሎ አይገኝም። መሃሉ ላይ መውጣትና መውረድ፤ መውደቅና መነሳት ይኖረዋል። የተሳካለት ባለሟል ግን ሥልጣን የመያዝ ፍላጎት እንዳለው ሳያሳብቅ ጥሩ ተዋናይ በመሆን በትረ ሥልጣንን መጨበጥ የቻለ ነው።” ገጽ 36 -
እርስዎ በተዋጣለት መልኩ ተውነውታል ሊባል ይቻላል፣ ምክንያቱም “ቤተመንግስት የገቡትን ያመጠኞቹን ወታደሮች” ጥያቄ በመልካም አመላለስ የተዋጣለት ትወና እንደተወኑ ራስዎም ነግረውናል። አገሬን ኤርትራን በተመለከተ ግን ‘ትወና’ አይሰራም! ወለም ዘለም ሳይሉ ‘ሰራዊትዎን” ማውጣት ብቻ ነው፣ ምክንያቱም “ቃል ይተክላል፣ ቃል ይነቅላል” ብለዋልና፣ ያስታውሱታል። አያዘግዩት ታድያ።
ቃልዎን ያድሱ ቃልዎን ያክብሩ፣
ድንበር የለም ብለው ሰው አያጭበርብሩ።
እውነተኛ ፍትህ ላዲሳበቤዎች!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
-
- Member
- Posts: 2368
- Joined: 24 Feb 2022, 14:08
Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Qomal agame man, there is no such thing as conditional recognition. The Pakistani dude is just trying to feed his family from youtube.
BTW, you are an idiot. There will never be peace in Tigray if Abby succeeds even taking Assab temporarily. The Galla hordes are a bit away from Eritrea. 




Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑22 Oct 2018, 12:01በተከበሩት ‘ዲራአዝ’ ጥሁፍ ይበልጥ ጣዕም ስላገኘንበት ብዙ ትምህርትም እየሸመትንበት ስለሆነ፣ እንግዲህ እናንተም ተመልእክቱ ሳትሰለቹ ተቋደሱ እንጂ፣ ያሻቹን ያህል ዝገኑና ቆርጥሙ፣ በደንቡ ግን አኝኩት፣ ከመዋጣችሁ በፊት!
“ተግባር የሌለበት ወሬ እንዲያውም በሰዎች ዘንድ ተዓማኒ እንዳይሆን መሰናክል ከመሆኑ በቀር የሚፈይደው ነገር አይኖርም። በመሆኑም ጠቃሚና አዳዲስ የሆኑ ተግባራትን ማሳየት እኔ ለቦታው እመጥናለሁ ብሎ ከመለፍለፍ ይልቅ ተቀባይነትን ያላብሳል።” ገጽ 37 - ማለፊያ አባባል ነው፣ እኛም የምንለው እንዲያ ነው። ኤርትራን በተመለከተ ተቀብየዋለው ያሉትን ውል በወሬ ብቻ እንጂ በተግባር መሬት ላይ ወርደው ደንበራችንን አልከለሉም። መቼ እንደሚወጡም በይፋ ለህዝብ አልገለጡም።
“ተቀናቃኞችን በሃሳብ መርታትና ወደራስ ጎራ እንዲመጡ ማድረግ በራሱ አንድ ጥበብ ነው። ምክንያቱም ለሥልጣን ምቹ መደላድል ከመሆኑም ባለፈ አካሄድን በሌላ እይታ ለመቃኘት፤ የሰዎችን የልብ ትርታ ለማዳመጥና በሰዎች ጫማ ላይ ሆኖ ስለ ሰዎች ህመም ጭምር ማወቅ ስለሚያስችል ነው። ሆኖም ግን ተቀናቃኝ ሁሉ በሃሳብ በመርታት ወይም በመረታት የሚያምን አይደለም። እንደዚህ ካለው ጠላት ጋር ሀሳብን እንደ መሥሪያ ተጠቅሞ ማሸነፍ ከባድ ነው። ስለዚህም አማራጭ ስትራቴጂዎችን መንደፍ ግድ ይሆናል።” ገጽ 37 - አዲስ አበቤዎቹ ጠበቃው ሄኖክ አክሊሉና ሚኪ እንዴት ናቸው? በጽህፈት ቤትዎ ጠርተው ለምን አያናግሯቸውም? እርግጥ ነው ሃሳቡን በነእንቶኔ ተግብረውታል፣ እነ ሄኖክ ላይ ግን ምነው ጨከኑ’ሳ፣ የግድ በኤርትራ በኩል መምጣት አለባቸው ማለት ነው? በገዛ አዲሳበባቸው ፍትህ የሚነፈጉት ሌምንድን ነው?
“እንደ ውሻ፣ ጠላት ላይ በመጮህ ማምለጫን ማመቻቸት ዘላቂ መፍትሄ ባይሆንም ለጊዜው ይጠቅማል። ምክንያቱም እንዳይመለስ ሆኖ ያልተሸኘ ጠላት ጊዜ ጠብቆ ዳግም ለማጥቃት እንደሚመጣ ጥርጥር የለውምና። ታዲያ ጊዜው ሲደርስ ልክ እንደ ነብር ኮቴን ሳያሰሙ ከጀርባ ቀብ ማድረግና ህልሙን ባንድ ጀንበር ማምከን መረሳት የለበትም፤ ወይም ስውር የሆነ ወጥመድ ማዘጋጀት ይበጃል። ሰዎች ራስ ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው። የሚፈልጉትን ነገር እያሳየህ ወደ ምትፈልገው ስፍራ ውሰዳቸውና ጣላቸው። ከዚያም “በሬ ሆይ! ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ” የሚለውን ተረት ተርትባቸው። ይህን መሰሉ ለዘብተኛ የኃይል አጠቃቀም ዘዴ ሠላም ሳይበጠበጥ ህዝብም ሳያጉረመርም የተደላደለ ስልጣን ባለቤት ለመሆን ያግዛል።” ገጽ 38 - እኛ ኤርትራዉያን የደንበሩ ብይን፣ “እንዳይመለስ ሆኖ እንዲሸኝ እንፈልጋለን”። ለምን ቢባል ጊዜ ጠብቆ ዳግም ለማጥቃት እንዳይመጣብን፣ ድንበራችን በፍቅር አሁኑኑ እንዲሰመር በጨዋ ደንብ ህሊና አለኝ የሚለውን የጠቅላዩን መንግስት እንጠይቃለን። “በሬ ሆይ! ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ” ተብሎ እንዲተረትብን አንፈቅድም። በምንምም አንደለልም። ደንበራችንን አሁኑኑ መሬት ወርደው ያስምሩ፣ ሰራዊትዎንም ከኤርትራ ምድር ልክ እንደነ ኦነግና ደምህት ከኤርትራችን ምድር ያውጡ።
“የተሰበጣጠረ የኃይል አጠቃቀም ሌላኛውና ዘመናዊው የኃይል አጠቃቀም ዘዴ ነው። ይህ ዘዴ የከፍተኛ ኃይል አጠቃቀምና የለዘብተኛ ኃይል አጠቃቀም በአንድ ላይ ስናጣምራቸው የምናገኘው ኃይል ነው። - - - ይህ ዘዴ በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሀሳብን ማስፈጸም፣ አቅምን በመገንባት ለሚመጡ ችግሮች ዝግጁ ሆኖ መጠበቅን፣ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ በሆነመንገድ ተጽዕኖ መፍጠርን እንዲሁም ጉልበትን ከማሳየት ይልቅ በህጋዊ መንገድ ፍላጎትን ማስፈጸምን አካቶ ይይዛል።” ገጽ 38 - ህጉ ለኤርትራ ያለውን ምድራችንን እርስዎ የሚያዙት ሰራዊት ግን በማን አለብኝነት የሰፈረበትን ይልቀቁ።
“ጥበብ ያልታከለበት ኃይል ጊዜው ይርዘም እንጂ ለውድቀት መንስኤ መሆኑ አይቀሬ ነው። ለዚህ ነው ባለንበት ዘመን አገራት ይህንን ስብጥር የኃይል አጠቃቀም ዘዴ የሚመርጡት። ‘የእኔን ፍላጎት ካልተገበርክ የምጽዓት ቀን ይሆናል!’ ብሎ ከማስፈራራት ይልቅ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር ሃሳብን በሃሳብ መርታት የዘመኑ ፖለቲካዊ ብልህነት ነው። ይህ አካሄድ የተሳካ እንዲሆን የሌሎችን የልብ ትርታ አድምጦ፣ የራስንም ፍላጎት በጥበብ አስረድቶ፣ ለመስጠትና ለመቀበል ራስን ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው። እብሪተኛ ከመሆን ይልቅ ለሌሎች በጎ በመሆን የደነደነ ልብ ያላቸውን ተጠራጣሪዎች ለራስ ፈቃድ ማስገዛት ይቻላል። የበጎነት እና ታማኝነት ስብዕና የተላበሱ ሰዎችን ለማዘናጋት፣ በቀላሉ ለመሸንገልና ለመደለል ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።” ገጽ 38 - አረ ጉድ ጉድ ነው! የበጎነት እና ታማኝነት ስብዕና የተላበሱ ሰዎችን ለማዘናጋት፣ በቀላሉ ለመሸንገልና ለመደለል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል! ኤርትራዊ እንታይ ከምዝበሃል ዘሎ ተስተውዕሎ’ዶ አሎኻ? ኤርትራዉያን እንደሆንን በፍቅራዊ ቁንጥጫ ሆነ ቁልምጫ፣ በጭብጨባ ሆነ በሆሆታ ጋጋታ አንዘናጋም አንሸነገልም አንደለልምም፣ ጥያቂያችን አንዲት ነች “ሰራዊትዎን ከአገራችን ከኤርትራ ያውጡ”።
“አንዳንዴ ህይወት በችግር የተሞላች ልትሆን ትችላለች። ታዲያ በእነዚህ የችግር ጊዜያት ቀድሞ መገኘትና አስደሳች ሁኔታዎችን መፍጠር በበረሀ እንደበቀለች አበባ በፍቅር ለመታየት ያበቃል። በማንኛውም ጊዜ አብሮን የሚሆን አካል አለን፣ የሚለው ፅኑ እምነታቸውን ለማግኘትም ያበቃል። በተለይም ወዳጅና ጠላት የሚለየው በችግር ቀን ነው፣ ብሎ በሚያምነው ህዝባችን ልብ ውስጥ ከነዕድፍ ተደላድሎ ለመቀመጥ በችግር ጊዜ መድረስን የመሰለ ጥሩ አጋጣሚ አይገኝም። መንግስት በሚገዛቸው ህዝቦች ላይ የሞራል፣ የፖለቲካና የአይዲዮሎጂ የበላይነት እንዲኖረው ያስችለዋል። ገጽ 39 - ቆቁ፣ ይሁና ይቺን መላ በእስረኞችና መግቢያ ቀዳዳ ይሹ በነበሩ በዲያስፖራ “ተፎካካሪዎች” ላይ በደንብ አድርገው በተግባር ተጠቅመውባታል! አይደል? ኤርትራዉያንን ግን በመልካም ምላስና ሽንገላ ሊደልሉን ነው የሞከሩ፣ በተግባር ዲንበር ስለማስመር ትንፍሽ ስላላሉ። ምላስዎ “ፍቅር” እያለ ተግባርዎ ግን አላሳመነንም። አረ እንዲያውም ስለ ዓሰብ የሰጡት ምላሽና ስለ ድንበር የተናገሩት ቃል ኤርትራዉያንን አስከፍቶናል።
ሥልጣንና የሥልጣን አጠቃቀም ተሚለው ንኡስ ክፍል ደግሞ
“በ12ኛው ክፍለዘመን በዛጕዌ ሥርወ መንግሥት ኢትዮጵያን ይመራ ለነበረው ንጉስ ላሊበላ ‘ሥልጣን’ ማለት ሁለት ነገር ነው። አንድም ራስን ዝቅ አድርጎ ለፈጠረው አምላክ ሲያገለግሉ የሚኖሩበት ነው። ከዚህ አለፍ ሲል ደግሞ ዘመን የማይሽራቸው ብርቅዬና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ አስገራሚ ሥራዎችን ሠርቶ የሚታለፍበት ጥሩ አጋጣሚ ነው። ይህ ንጉስ የሰራቸው አስራ አንድ ውቅር አብያተ ክርስትያናት አሁንም ድረስ ስሙን ከመዘከራቸው ባሻገር ለአገሪቱ የቱሪዝም መስህብ በመሆን ጭምር እያገለገሉ ይገኛሉ።” ገጽ 41 - አልሰሙም ማለት ነው በእንክብካቤ ጉድለት ወይም ከቱሪዝም አንጻር ብቻ በመመልከት መንፈሳዊ እሴትነታቸው ችላ ተብሎ ተገቢው ትኩረት ስላልተሰጣቸው እየተሰነጣጠቁ ናቸው እኮ። አረ መላ ፈልጉ። እርስዎ አስራሁለተኛውን ውቅር ቤተስኪያን እንዳይሰሩ፣ አንድ መነኮስ ብቻቸውን ጀምረውታል ነው ሲባል የሰማን። አረ ያለውን ያቅቡ! በዘመንዎ ይህ ድንቅ ቤተስኪያን ፈረሰ ሊባል! አረገኝ!
“ከግለሰብ እስከ ቤተሰብ፣ ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ፣ ከማህብረሰብ እስከ አገር፣ ብሎም እስከ ዓለም በተዘረጋው ትስስራዊ ሂደት ሥልጣን የላቀውን የጋራ ተጠቃሚነት እያቻቻለ፣ እያረጋገጠ እንጂ ለጥቂቶች ወግኖ፣ በብዙሃን ጫንቃ ላይ የሚጫን ቀንበር አይደለም። ከሁሉም በላይ በከፍተኛው የአመራር እርከን ያስቀመጥናቸው ፖለቲከኞች ኃላፊነታቸውን መሳት አይኖርባቸውም። እንደጠንካሮች ሁሉ ለደካማዎቹ የኅብረተሰብ ክፍሎች አለኝታ መከታ መሆን ይጠበቅባቸዋል።” ገጽ 41 -አይ ጦቢያ ባህርዳር ላይ እኒያ ውሑዳን ባንድ ጀምበር የመቶ ምናምን ሰው ህይወት ቀዘፉ፣ ሰዉ ለውጥ መጣ ሲል ደግሞ ብዙሃኑ ውሁዳኑን ምን የሚሏት መንደር “አርባጉጉ ነው ቡራዩ” የሚባል ቀየ ውስጥ በገጀራ አረ ዝም ይሻላል። የጂግጂጋውን ልክ ያስገቡት ማን ላይ ግፍ ስለፈጸመ ነው? አረ ራዮቹንም በእኩል ዓይን ይዩ።
“- -- ለጋራ ጥቅም መስራት ስናቆም ችግር መፍታት ሲሳነን ሕዝብ ይሁንታውን ይነፍገናልና በመራራ የቅጣት በትር ካልሆነ ተፅዕኖ አይረጋም እንላለን። ወደ ተሻለው ዓለም ለማንቀሳቀስ ልንጠቀመው የሚገባን ኃይል ከተፅዕኗችን ባፈነገጡትና ለማፈንገጥ በሚያማትሩት ጀርባ ላይ ለማሳረፍ ስንቆፍር እናድራለን። ” ገጽ 42 -እውነት ብለዋል፣ ራዮች እንዴት ናቸው’ሳ። ያ ያገሬ ጀግኖች “ኤርትራ ውስጥ የባዕድ ሰራዊት ሰፍሮ እያለ ጎረቤቶቿ የሰላም ዕንቅልፍ አይተኙም!” የሚሉት ለካ እውነታቸውን ነው!
“ሀገራት አንድ አይነት የኃይል አጠቃቀም ስልትን አይከተሉም። አንዱ ፍጹም ዴሞክራሲያዊ ሲሆን አንዱ ደግሞ ረግጠህ ግዛ ዓይነት ይሆናል። አንዱ ያለውን ኃይል ዓላማውን ለማሳካት በግልጽ፣ በይፋ ሲጠቀምበት ሌላ ደግሞ የህጋዊነትን ጭንብል ለብሶ ውስጥ ውስጡን ግን ለማመን እንኳን አስቸጋሪ የሆኑ ድርጊቶችን ይፈጽማል። - - - የህብረተሰቡ ንቃተ ህሊና በሚፈለገው ደረጃ አለማደጉ ዓብይ ምክንያት ሆኖ እናገኘዋለን። የመብት ረገጣ ሲካሄድበት ለምን ብሎ ሲጠይቅ አይታይም። እባብ ያየ በልጥ በረየ እንደሚባለው ሁሉ ህዝቡም የዕውር ድመት ኑሮ ሆኖበት፣ ነጋ ሲል ዳግም እየጭለመበት፤ ገዢዎች የፈለጉትን ነገር የመፈጸም መብት እንዳላቸው አምኖ የተቀበለ ይመስል አይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶም እንዳልሰማ ይሆናል። - - -” ገጽ 42 - ይቺ አባባል ራያ ላይ እየሰራች አይደለም!
“የተለያዩ አገር መንግሥታት ሥልጣን ላይ ያላቸው አመለካከት የኃይል አጠቃቀማቸው ሁኔታን በእጅጉ ሲወስነው ይስተዋላል። ‘ስልጣን የህዝብ ነው’ ብለው የሚያምኑ መንግሥታት ኃይላቸውን ልጓም አልባ አያደርጉትም። ምክንያቱም ወደ ላይ ያነሳቸው ህዝብ የትዕግስቱ ጽዋ የሞላች ቀን ወደ ታች እንደሚያወርዳቸው ጠንቅቀው ያውቃሉና። - - - በዓለማችን ታሪክ እንከን አልባ መንግሥት ተፈጥሮ አያውቅም።” ገጽ 43 - ታድያ በዓለማችን እንከን አልባ መንግሥት ተፈጥሮ ስለማያውቅ ራዮች ቢገደሉ፣ አዲሳቤዎች ቢታሰሩ ወልቃይቴዎች ቢፈናቀሉ ምን ችግር አለው እንዲባል ነው የፈለጉት ማለት ነው! አይ እርስዎ ከኤርትራ ምድር ‘ኮ ሰራዊትዎን ቢያወጡ ይህ ሁሉ እክል ባልተፈጠረ ነበር።
“አንዳንድ መንግሥታት ሥልጣንን የዘላለም ርስታቸው አድርገው ከማሰባቸውም ባሻገር ህዝብንም ከመጤፍ የማይቆጠር አድርገው ይወስዱታል። ይህ አስተሳሰባቸው ስልጣናቸውን ያለ ምንም ገደብ እንዲጠቀሙበት ያደርጋቸዋል። አገር እንዴት ትለማለች? ህብረተሰቡስ እንዴት ይሰለጥናል? ትምህርትን እንዴት ልናስፋፋ እንችላለን? ህብረተሰቡንስ እንዴት ከአስከፊ ድህነት ልናወጣው እንችላለን? ብለው ከማሰብ ይልቅ የሚያሳስባቸው ነገር ኃይልና ስልጣናቸው እንዴት ተከብሮ መቆየት እንደሚችል ሲሆን የመንግስታቸው እጀ ሰፊነትም ለጉርሻ ሳይሆን ለጥፊ እና ለጡጫ ይበልጥ ይመቻል። በመሆኑም በስልጣናቸው ለሚመጣና የተለየ አስተሳሰብ ለሚያራምድ ማንኛውም አካል የቆመበት ምድርን የምጽዓት ቀን (አርማጌዶን) የደረሰበት ያስመስሉታል። ገጽ 43-44 - በተግባር ራያ ላይ እየታየ ነው።
“አገር ቀድማ የገነባችው የፖለቲካ ሥርዓት በመንግሥታት የጉልበት አጠቃቀም ላይ መልካምም ሆነ መጥፎ ተጽዕኖውን ሲያሳድር እንመለከታለን። ዲሞክራሲያዊ በሆኑ አገራት ላይ አዲስ የሚመጣው መንግሥት በእርግጠኝነት ዴሞክራሲያዊ ነው’ ብሎ ከሁሉ በፊት አውቆ መናገር ባይቻልም የመሆን አጋጣሚው ግን ከፍተኛ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም በተዘረጋለት መሥመር ብቻ እደሚፈስ የቧንቧ ውሃ ዲሞክራሲም በተዘረጋለት ሥርዓት ላይ መሠረቱን አድርጎ የሚቀጥል ስለሆነ ነው። ምናልባት ቀድሞ የተዘረጋው ሥርዓት ፈላጭ ቆራጭ ከነበረ ዋጋ አስከፍሎ እንጂ እንዲህ በቀላሉ በአንድ ጊዜ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሰርዓት ሊሸጋገር አይችልም።” ገጽ 44 - አገላለጥዎን ወደድኩት።
“አንዳንድ መንግሥታት በህግ መንግሥታቸው ላይ የሚያስቀምጡት ሀሳብ ለመንግሥት ከለላ ከመሆን በቀር ሌላ ምንም ነገር እንደማይፈይድ በተለይም ባላደጉት ሀገራት ዘንድ በግልጽ የሚታይ እውነታ ነው። - - - የእምነት ስፍራውም ሆነ የህግ አስከባሪ አካላት መንግሥቶቼ ለሚሏቸው ኃይሎች የተለጎሙ ፈረሶች ሆነው ያገለግላሉ።” ገጽ 46 - [ይህ አባባል በስዎ መንግስትስ እየሰራ እንዳይሆን ትንሽ አጢነውታል። ለምንድን ነው’ሳ የአገርዎ የእምነት ተቋማት ሆኑ ህግ አስከባሪ አካላት “ተኤርትራ መሬት ያለው ሰራዊታችን ይውጣ የማይሉት’ሳ”፣ በኤርትራ ላይ የሚያሳዩት ኢፍትሀዊነት ውጤቱ አገርዎ ውስጥ ረመጥ መነስነስ መሆኑን ዘነጉት አይደል። ኤርትራ ላይ የሚያሳዩት ፖሊሲ ነጸብራቅ ያው ወልቃይት ላይ፣ ራያ ላይ፣ አዲሳባ ላይ - - - ለመንግስትዎ ሰላምን አይሰጥዎትም፣ ስለዚህ በወጉ በጭዋ መልክ ተኤርትራ ምድር መውጣት ይበጅዎታል።
እውነተኛ ፍትህ ለወልቃይቴዎች፣ ለራዮችና ላዲሳበቤዎች!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑24 Oct 2018, 01:15የክቡር “ዲራአዝ” መጠሐፍን ቁምነገር ልክ እንደ ከመልካም ፍሬ እንደተጨመቀ ጭማቂ መጠጥ መጠጥ እያደረንው ነው። መጣሐፉን ያላገኛቹ ምዕራፍ አራት - ኃይልና ሥልጣን በኢትዮጵያ - እሚለው ክፍሉ ላይ ደርሰናል፣ እያነበባቹ ተማሩበት ተዝናኑበትም! መልካም ንባብ።
“ሥልጣን በሀይማኖት . . . ኃይል በወታደር” - - - “ እንደ እኛ አገር ተጨባጭ ሁኔታ የቀደመው ጊዜ ንጉሣዊ ቤተሰቦች ዕድሜያቸውን ለማራዘም ሲሉ ያዋጣናል፣ የሚሉትን ሌሎችም ዘዴዎችን ሲጠቀሙ ነበር። መርዘኛ ሃሳብ በሥልትና ዘዴ ቀምመው ተንኮልን ወደ ህዝብ መርጨት ከሚጠቀሙት አንዱና ዋነኛው የፖለቲካ መሳሪያ እንደሆነም ይታወቃል። ይህም ህዝቡ እርስ በእርስ እንዲቃቃርና አንድ ጥግ ይዞ እንዲቆም ማድረግ ነው፣ ዓላማው። አንዱን ‘ቆንጆ ነህ’ ብሎ ሌላኛውን ‘ታስጠላለህ’፣ አንዱን አዋቂ ሌላውን ሞኝ፤ አንዱን የቤት ልጅ ሌላውን የእንጀራ ልጅ፤ አንዱን አቃቢ ሌላውን ቀራፊ፣ አንዱን አወዳሽ ሌላውን ተወዳሽ፤ አንዱን ምርት ሌላውን ገለባ፤ አንዱን ተሳዳቢ ሌላኛውን ሰዳቢ በሚል ጎራ ለይተው ክፋታቸውን በማናፈስና በማራገብ ከላይ ሆነው የበላይ ጠባቂ የሚመስሉ ‘አፈ ቅቤ፣ ልበ ጩቤ’ የሆኑ መሪዎች ያለፉባት አገር መሆኗን መገንዘብ ያስፈልጋል።” ገጽ 47 ያለፉባት? አሁን ያሉትም ቢሆኑ እኮ አንዱን ባይሰድቡም እንኳን አንዱን ግን “ወርቅ ህዝብ ነው ሞተር ህዝብ ነው” ብለዋል። ስሞተኛ ሰራዊት ቤተመንግስት ሲገባም “መንግስታችን ተነካ ብለው ወደ ቤተመንግስት የገሰገሱት በማለትም የተወሰኑ ክፍሎችን ጠቅሰዋል” አይደል? እዛው አዲሳባ ያለውን ህዝብ ግን ችላ ብለታል? አይ ዶተረ! “ወርቅ ህዝብ፣ ሞተር ህዝብ” ከተባለው የፈለቁት በራያ ምን እንደፈጠሩ የትናንት እውነታ ምስክር ሁኗል።
‘ጀብዳዊ ጭካኔ’ የነገሠበት የኃይልና ሥልጣን ሥርዓት - “ - - ማር የተለወሰ እሬትን ሙሉ ማር ተደርጎ ትውልድ ይጋታል። ሚዛናዊ ሳይሆን፣ ጭካኔው በቅንነት ተተክቶ ይመሰከራል። ሚዛን ከግራውም ከቀኙም ያለውን ገምግሞ ይዳኛል እንጂ ከመጀመሪያው ለአንዱ ዝቅ ለሌላው ከፍ ያለ ግምት በመስጠት እንደማይዳኝ ይታወቃል። የእኛ ግን በተቃራኒው ሆነ - - “ ገጽ 50 ሰላም ሰፍኗል በሚል “ማር” ውስጥ “ዲንበር ትርጉም የለውም” የሚል “እሬት” ለውሰው ሊግቱን ሲሉ’ማ፣ እኛ ኤርትራዉያን “ሞኝዎትን ይፈልጉ፣ ነቄ ነን” ብለናል፣ ቦለቲካን ከኑሯችንና ህይወታችን በላይ ማንም እንዲያስተምረን አንጠብቅም። ይሰማል!
“ከሥር ከምንጩ የደፈረሰ ውኃን ተከትሎ ከወደ አናት የጠራ ውኃ መጠጣት አይቻልም። የእኛ መሪዎች እና የፖለቲካ ባህል ግን እንዲያ ሆኖ ነው የተገነባው። ከበቀል ምንጭ የፈለቀ ልንለውም እንችላለን። በሙሉ ዓይን ደፍረው እውነትን ማየት የሚችሉ መሪዎችና የፖለቲካ ሰዎች ባለቤት ከሆኑ ሀገራት መካከል እኛ የመጨረሻዎቹ መጨረሻ ነን ብንል ያንስ እንደሆነ እንጂ አይበዛብንም። በፖለቲካ ምህዳራችን ገዝፎ ያጠላው ሀቅ፣ የእውነት ሁሉ ምንጭ ራሱ እውነት ሳይሆን ኃይል ነው። ጠቢብነት ብሎም አርቆ አስተዋይነት ከመንበረ ስልጣኑ ተኮራርፏል። በጥላቻ ተጋርዷል። መደማመጥ የድክመት እንጂ የጥንካሬ መገለጫ ተደርጎ አይታወቅም። በሸፍጥ በሰበሰቡት፣ ከደሃ አፍ ነጥቀው ባከማቹት መሳሪያ በለው! ንዳው! ሂድበት! . . . እንጂ ይቅርታ አትታወቅም። መጠፋፋት ግን እንደ ክረምት አረም ሠርክ ዙሪያችንን ሸፍኖናል።” ገጽ 51 - ይቕርታንማ ጥሩ አድርገው ተግብረዋታል፣ በዚህስ አይታሙም። እነ እንቶኔ ደግሞ ከደሃ አፍ ነጥቀው ባከማቹት መሳሪያ በለው! ንዳው! ሂድበት ሲሉ ትናንት በራያና በወልቃይት በተግባር ታይተዋል። ማን ነው ይህን “አሌ” የሚል?
“በግራኝም ሆነ በልብነ ድንግል ዘመነ-መንግሥት ሂደቱ እንዲያ ነበር። ቴዎድሮሥ፣ ዮሃንስ፣ ሣህለ ሥላሴ፣ ሚኒሊክም፣ ተፈሪም፣ መንግሥቱም፣ . . . የጭካኔውን ቀንበር፣ የጥላቻውን ድንበር አግዝፈውና አስፍተው ለቀቁት እንጂ ‘ትውልድ ይዳን በኛ ይብቃ’ አላሉትም። የጥላቻው ልክ እስከምን በመሪዎቻችን ደምና አጥንት ውስጥ ዘልቆ እንደገባ ሕያው ምስክር የሚሆነን በመጨረሻውና የማንም መንፈስ በሚታጠፍበት ጊዜ እንኳ የሞት ፅዋው እስከሚሞላበት የመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ከክፋታቸው መነጠል አለመቻላቸው ነው። “ ገጽ 51 ጥበበኛ ነዎት፣ ከመንግሥቱ ቀጥል ያስቀመጧትን ነጠብጣቧን ግን ወደድኳት።
‘ቦ ጊዜ ለኩሉ . . . ‘ እንዳለ መፅሐፍ፣ አጼ ኃይለ ሥላሴም ከልጅ ኢያሱ (አጤው ልጅ ኢያሱን ከእስር አስወጥተወ እንዳስገደሉትና የተቀበረበት ቦታ እንደማይታወቅ መነገሩን በፊተኛው አንቀጽ ተገልጧል) የተሻለ ዕጣ ፈንታ አልነበረም የገጠማቸው። እርሳቸውም በተራቸው በደርግ የጭካኔ መዳፍ በእርጅና ዘመናቸው ሕይወታቸውን ተቀሙ። ይቅርታን በማያውቅ የፖለቲካ ባህላችን እርስ በርስ መጠላለፋችን በከፋ መልኩ ቀጠለ፤ የሚሊዮን ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ። የቀደሙት ማለትም ባልዘመነው ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የምናገኛቸው ልማዳውያኑ ንጉሦቻችን ለአፋሽ አጎንባሽ እንጂ የትችት ሀሳብ ለሚሰነዝርባቸው ወገን ቦታ አልነበራቸውም። በሃሳብ የተለያቸውን ያለምህረት ይገድሉ፣ ግዞትም ይልኩ ነበር።” ገጽ 53 እርግጠኛ ሆነን ለመናገር ይቅርታን በተመለከት በጦቢያ ታሪክ ውስጥ ድንቅ ምዕራፍ ይዘዋል እርስዎ። ቢሆንም “ጀሮ ለባለቤቱ ባዳ ሆኖ እንጂ”፡ “አፋሽ አጎንባሽን እንጂ የትችት ሃሳብ ለማቅረብ ዓቕም ያሏቸውን ሰዎች በሚንስትርነት አልሾሙም” ተብለው ይታማሉ’ኾ፣ ነገሩ ነው እንጂ እኛ ምን አገባን ብቻ ሰራዊትዎን ተኤርትራ ምድር ያውጡ፣ ስለ መጭው ትውልድ ህልውና የሚቆረቆሩ ከሆነ ደግሞ መሬት ላይ ወርደው በመተግባር ቃልዎን ያክብሩ።
“ወላጆች ጧሪያቸውን ተነጠቁ። አገር ተረካቢ ታዳጊዎች ያለ ወንድም፣ ጋሼና እታበባ ከባዱን ሕይወት በራሳቸው መጋፈጥ፣ የእናቶቻቸውና አባቶቻቸውን እንባ እንጂ ሳቅ ሳያዩ ማደግ ዕጣ ፈንታቸው ሆነ። በባህላዊ ንጉሦቻችንና በዘመናዊ አምባገነን መሪዎቻችን መካከል ያለው ልዩነት የዘመን እንጂ የግብር ሊባል እንደማይችል ታሪክ ምስክርነቱን የሰጠውም በዚህ ጊዜ ነበር። ከትላንትናዎቹ ጨካኝ ጀብደኞች ሥልጣን የተረከቡት አዲሶቹም ገዢዎች አባቶቻቸው ባዘገሙበት መንገድ ከማዝገም ውጪ ሌላ ፈለግ መተለም ሳይሆንላችው ቀረ። ዛሬ ያሏት ዛሬ ከመምሸት ወዲህ የተገኘች ሌላ ቀን ከመሆኗ ባሻገር በሁሉ ነገሯ ቁርጥ ትላንትን መሰለች፤ ትናንትናን ሆነች።” ገጽ 54 ያለ ወላጅ የሚያድጉትን ረሷቸው’ሳ፣ እናትና አባቶቻቸውን ሳያውቁ ያደጉም እኮ አሉ።
“ባህላዊ ንጉሦቻችንም ሆኑ ዘመን አመጣሾቹ ወራሾቻቸው የነገሡበትን ዘመን ብቻ አይደለም ገድለውና ቀብረው ያለፉት። ቀጣይ ዘመንና ትውልድንም እንጂ። ዛሬ አንገታችንን አቅንተን የምንቆምባት አገር ያሳጣን ዕድል ዕጣ ፈንታ ፈቅዳላቸው መንበር ላይ የወጡ ገዢዎቻችን በአደባባይ የረጩት የጥላቻ የታሪክ መርዝ እርማት ተጠምደን እየተጓተትን አለን። የቅርብም ሆኑ የሩቅ ገዢዎቻችን ከሌላ ፕላኔት እንደመጣ ፍጡር ኢትዮጵያዊነት ላይ የሚዘምቱት፣ አንድነትን የሚቃረኑት፣ የዴሞክራሲ ጠላት የሚሆኑት ኢትዮጵያዊነት የፍቅር የብልፅግና እንቅፋት በመሆኑ አይደለም። ይልቁንም ራሱ ፍቅር በመሆኑና የሚዘመትበትም ኃይል እንደሆነ ስላመኑ እንጂ። ከነሱ አፈ-ታሪክ በላይ ግርማና ደርዝ ያለው መሆኑም ከነሱ ደጃፍ ውጪ አንድም መጠጊያ ደጅ እንዳይኖር ስለሚሹ ነው።” ገጽ 54 እርስዎ አሁን ተራዎ ደርሷል በስራዎ ይመዘናሉና ቃልዎን ያክብሩ፣ ደንበር የለም ብለው ህዝብ አያደናግሩ፣ ይልቅስ ብይኑን ቶሎ ይተግብሩ።
“አውቀን ይሁን ወይም ደመነፍስ ተጣብቶን ባይታወቅም ‘ጀግና እንወዳለን’ ሳይሆን ‘እናመልካለን’ ብንል አይበዛብንም። ገጽ 55 አረ ጎበዝ እኛ አምላክን ብቻ ነው የምናመልከው፣ ጀግናን ግን እንወዳለን እናከብራለን።
“እውነት እውነት እላችኋለው በዓለም ላይ እንደ ኢትዮጵያውያን አንበሳ አምላኪ ህዝብ አለ ማለት ከባድ ነው።” ገጽ 56 አረ ጉድ ክርስትያኑ ሥላሴን ሙስሊሙ ደግሞ አላህን ነው የሚያመልክ እንጂ እንስሳ የሚያመልክ በዚህ ዘመን አንድም ሰብአዊ ፍጡር በጦቢያ ምድር አለ ብየ አላስብም።
“በምንም በማንም ሊሻር በማይችል ደረጃ አንበሳ ኃያል ነው፤ የአራዊት ንጉስ። ብዙዎች ስለዚህ አራዊት ገድል በብዙ ዘግበዋል። የቢቢሲ ዶክመንተሪ ስለዚህ እንስሳ የሚነግረን እውነታዎች አሉ። ከሰ ውልጅ አስቀድሞ ድንበር ማስመር፣ ግዛት መከለል የጀመረ አራዊት አንበሳ ነው በሽንቱ ምልክት በማድረግ ግዛቱን ያሳውቃል ያን ድንበር ጠብ ፍልሚያ የሚሻ ካልሆነ በቀር የማንም እንስሳ እግር ማለፍ አትችልም።” ገጽ 58 ስለዚህ የድንበር ጉዳይ ከተነሳ እግዚአብሄር አዳምን ከኤደን ገነት አስወጣው የሚል ጥሁፍ አለ፣ ስለዚህ ከአንድ የተወሰነ (ወሰን ወይ ድንበር) ካለው ቦታ ነው ያስወጣው ማለት ይቻላል፣ አንበሳው ይህን የድንበርን ጉዳይ ተግዝሔር ተምሯል ማለት ነው! አዪ የድንበር ጉዳይ፣ ሰራዊትዎን’ሳ ከድንበራችን መቸ ነው የሚያወጡት። እኔ የገረሙኝ ስለ አንበሳ ቢቢሲ እንዲህ ኣለ እንዲያ አለ ከማለት አንበሳን እንደ የቤት እንስሳ ስላለመዱት ያገርዎ ሰዎች አንዳችም መረጃ አልነበርዎም ማለት ነው?
“በመሆኑም ከራስ አብራክ የወጡ እና የአጎት የአክስት ልጅ የሆኑ ወንድ አንበሶች ለጉርምስና ሲደርሱ፣ ጎፈሬያችው ሲበቅል፣ ዝምድና ተሽሮ ይባረራሉ። የሥልጣን ተቀናቃኝ ናቸውና ይሰደዳሉ። አቅም ካላችው ተፋልመው ለመንበር አለዚያም እግራችው ወደመራችውና ከግዛታቸው ውጭ ወደሆነ ቀየ ለስደት ይዳረጋሉ። ተቀናቃኝ ግን ተሸንፎ ቢባረርም ተባሮ አይቀርም። ሲጠነክር ይመጣል። ይፋለማል- ለዙፋኑ። ከቀናው ወንድሙ ወይም የአጎቱ ልጅ የሆነውን ንጉሡን ይገድለዋል። ወይም በስተርጅና እድሜው ለስደት ይልከዋል።” ገጽ 58 ግሩም አገላለጽ ነው!
“ደርግ ልጅህን ገድሎ፣ ሬሳውን መንገድ ጥሎ ወላጅን ማልቀስ አይቻልም፣ ብሎ የከለከለው ከግብር አባቱ አጼ ቴዎድሮስ ትምህርት መውሰዱ ግራሞትን ይጭራል . . . ።” ገጽ 60 ክቡር ዲራአዝ ኢሕአዴግ ባጠቃላይ ወይም ወያኔው በተለይ የፈጸመው ግፍ’ስ ከማን ይሆን የተማረው? ምነው ቦርቀቅ ሰፋ አድርገው የነዚህንም የግብር አባት ያልጠቀሱት? ፈርተው ነው ወይስ ነገሩ ከንክኑዎት!
“ . . . ደጃች ውቤ የአፄ ቴዎድሮስ አማች ናቸው። የሚስታችው የጥሩወርቅ አባት። በዚያም ላይ በደግነት የሚታወቁ የዘመኑ መሥፍን ነበሩ። ይህ አምቻነት፣ ጋብቻም ሆነ ደግነት ደጃች ውቤን ከመቅደላ እስር አላዳናቸውም። እዚያው መቅደላ በእስር ላይ እያሉ ነበር፣ ሕይወታቸው ያለፈው።” ገጽ 60 - ይህቺ ጥሁፍዎ ኤርትራን ምንም እንደማያውቋት ታሳብቅብወታለች፣ ምክንያቱም ደጃች ውቤ በምድሪባህሪ ቆይታው ግፍ ይፈጽሙ ነበር ነው የሚባለው፣ በሰዎች ጀሮ ውስጥ የዐተር ቆሎ ያስገቡና ያደነቁሯቸውም ነበር ይባላል፣ በመሆኑም “ብዘመን ውቤ ዝጸመመ፣ ዝባን ውቤ ኪብል ይነብር” እየተባለም በምሳሌነት ይጠቀሳል። ኤርትራን አያውቋትም!
እውነተኛ ፍትህ ለወልቃይቴዎች፣ ለራዮችና ላዲሳበቤዎች!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑26 Oct 2018, 08:47የክቡር ዲራአዝን መጠሀፍ ገረፍ ገረፍ እያደረግን ተዚህ ደርሰናል። እሳቸው በመጠሃፋቸው ምን አስበው እንደሆኑ ባይታወቅም፣ አጤ ቴዎድሮስን በተመለከተ ከደጃች ውቤ፣ ከአቤቶ ሰይፉ፤ ከደጃች ተድላ ጓሉና ከወሎው ውጊያ አንጻር የተገጠሙትን ግፍን የሚያመለክቱ የተለያዩ ግጥሞችን ካቀረቡ በኋላ ጎንደሬውን አጤ በተመለከተ እንዲህ ብለዋል፦ እኛ እየተዝናናን እንማርበት
“እሱም አልበቃ ቢላችው ከነህይወት ገፍትረው ገደል ጨምረው ገድለዋል።” ገጽ 62 - አጤው የሰው ልጅ ንቃተ ህሊና ባልዳበረበት በዚያን ዘመን ያን ግፍ ፈጸሙ እንበል፣ እኛን የሚገርመን ከሳቸው ሳንማር በዚህ በዘመናችን እንዲህ አይነት ግፍን የሚፈጽሙ እንስሳዊ ባህሪ የተጠናወታችው ሰዎችን እያየን መፍትሄ አለመሻታችን ነው። በሐረር፣ በበደኖ፣ በባህርዳር፣ በጂግጂጋ፣ በራያ፣ በወልቃይት ወዘተ የተፈጸመው እኮ ከዚህ አይተናነስም። ዜጎቼ ምትላቸውን ሰዎች እንደ ጠላት ፈርጀህ የሚጠጣ ውሀ መከልከል ከነህይወት ገፍትሮ ወደ ገደል ከመጨመር በምን ይለያል? አጤው እንዲያ ቢያደርጉ 1, 2 10, 20 ተብሎ የሚቆጠር ሰው ላይ ይሆናል እንበል፣ የነኝህ ግን እግዚኦ አያስብልምን? ያገጠጠ ሽፍታነት ማለት ይሄ አይደለም እንዴ? አረገይ! ቀስ ብለው ኅሊናዎን ይመርምሩና ትልቁን የቤት ስራዎን ይስሩ ሰራዊትዎንም ታገሬ ተኤርትራ ምድር ማውጣትም አይርሱ። ታልሆነ’ኮ እርስዎም “ዓለም ያወቀውን ጠሃይ የሞቀውን ብይን ወይ ውል” በተግባር እስካልተገበሩት ድረስ፣ ውሉን እያሳሳቁ ከነህይወቱ ገፍትረው ገደል ለመጨመር ከተፍጨረጨሩት ከወያኔዎች በምንም አልተለዩም ልንል እንችላለን እኾ። እንዲያ ለማድረግ ያሰቡት ሁሉ ገደሉ ውስጥ ራሳቸው እንደገቡና እየገቡ እንዳሉ መቸም አይዘነጉትም።
“በርጋታና በጸጥታ ለዘመናት አንቀላፍታ በመፍሰስ ላይ ያለችውን ጥንታዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ አገር ድንገት አንቅተው ሥርዓት ልትከል፣ ለውጥ ላምጣ ያሉት ንጉሥ (አጤ ቴዎድሮስ) በግራና በቀኝ፣ በደቡብና በሠሜን አንድም ያልዘመቱበት ግዛት፣ አንድም ያልተዋጉት መሳፍንትና መኳንንት አልነበረም። ሸዋ፣ ወሎ፣ ትግሬ፣ ጎጃም፣ አገው ሁሉም የጭካኔ በትራችውን ቀምሷል። የዘመኑን መንፈስ (sprite of the time) መቃኘት እና በነርሱ ጫማ እግርን አኑሮ ማሰብ ያስፈልጋል የሚሉ ወገኖች እዚህም እዚያም ያሉ ቢሆንም የተፈጸመውን ያህል ግፍ እና በደል ፈጽሞ ዘመን ላይ ለማላከክ መሞከር ግን ሩቅ የሚያስጉዝ መንገድ አይደለም።” ገጽ 62-63 - ጎንደሬውን አጤ ወረዱባቸው እኮ! አሁን በእስርዎ ስር ‘የሚመሩትን ሰራዊትዎን’ እሰው አገር ዱለው ወይ ወዝፈውና ዘፍዝፈው፣ በዚህ ተግባርዎ ሰበብ የተፈጠረንና እየተፈጠረ ያለን በደል ምን ብለው ይጠቅሱት ይሆን? በማንስ ለማላከክ ይሞክሩ ይሆን? ዓቅም ስላጡ ነው ወይስ ግፉ አይታይዎትም? ወይስ የፈረንጅ ፍርፋሪ ገንዘብ እስኪገኝ ነው እየጠበቁ ያሉት? የራያ፣ የወልቃይት፣ የሃረር ወዘተ ወዘተ ንጹሐን በእብሪተኞች አማካኝነት በገሀድ እየተዘመተባቸው እንዳሉም ዘንግተው ነው ወይስ ዓቕም አጥተው መፍትሔ የማይፈልጉላቸው’ሳ።
“በአናብስታዊ የጀግንነት ባህላችን ውስጥ እኔና እኔ ብቻ እንጂ እኛ ወይም አገር የሚለው ትልቁ ስዕል ቦታ የለውም።” ገጽ 63 ቦታ ቢኖረው’ማ በሰው አገር ሰራዊትዎን አስቀምጠው፣ ምንም እንዳላደረገ ተዚያም አልፈው አስመራና ምጥዋ ላይ የዘፈን ድግስ ሊያደርጉ በተመኙ ነበረን? አገርዎን ይዘው እኛም አገራችንን ይዘን፣ ሰራዊትዎን ባገርዎ ሰራዊታችንን ባገራችን ድንበር ውስጥ አድርገን፣ ከዚያ በኋላ የሰላም ድግስ ቢደረግ ባልከፋ፣ የሰው እግር ደፍጥጠው ረግጠው፣ በሰዎች ስቃይና ሰቀቀን ላይ ድግስና ዳንስ አማረኝ ሲሉ፣ አይደለም ሰው መላእኽትና ፈጣሪም ይታዘቡዎታል። ራስዎንና መንግስትዎን ይመርምሩ! እርግጥ ነው ባገራችን ላይ የተደነገገውን ማዕቀብ ለማስነሳት የሚያደርጉትን ጥረት ሳናደንቅ አናልፍም።
“አፄ ኃይለስላሴም በዚያው በጥንቱ ባህል ነው የቀጠሉት። በድንቁርና ለታወረ ሕዝባቸው አይኑን እንዲገልጥ ት/ቤት ከመገንባት ይልቅ በየደብሩ ለክብራቸው መገለጫ ቤተመንግሥት ሲያስገነቡ መኖራቸው ነው የሚነገረው።” ገጽ 63 - አቤት በወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛል አሉ! ምናለ ሂሳችን በጭብጥ የታጀበ ቢሆን፣ ይህ ጉዳይ ‘የሚነገረው’ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም። እስቲ አሁን ኃይለስላሴ ት/ቤት አላሰሩም? ደርጉ ያዲሳባ ዩኒቨርስቲ ያለውን፣ አሁን አሁን እንደሚነሳው ደሞ ‘ፊንፊኔ ዮኒቨርስቲ’ ብለው ሊያጠምቁት የሚሹ ሰዎች አለን አለን ሳይሉ፣ ቤተመንግስታቸውን ለዩኒቨርስቲ የሰጡ ሰው አይደሉም እንዴ? ተሳሳትኩ? አረ ጎበዝ የት ነው እንዴ እርስዎ የተማሩት? እርግጥ ኃይለሥላሴ ግፍ ፈጽመው ይሆናል፣ ትምህርት ቤት ግን ሰርተዋል። ‘በየደብሩ’ ማለት ግን ምን ማለት ነው? አጤው እኮ ለቦለቲካዊ ጥቅማቸው መስጊድም ያሰሩ ነበሩ። ዩኒቨርስቲዎች ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያዎቹን 33 የዘመናዊ ትምህርት ተማሪዎችን በተለይም ድሆችን ወደ ውጭ አገር አስልከው አስተምረው እስከ ምኒስትርነት ደረጃ ያበቁ ናቸው፣ እነ ያያ ሃብተወልድንና፣ ያያ ደሬሳ ልጆችን ወዘተ ማለቴ ነው። ለሚዛናዊነት የዘውዴ ረታን ጥሁፍ እንዲያቡ እንመክራለን። “ፍረድ ለማተብህ” ነው ነገሩ። “ንወድሰብ እንተሃብካዮ ናቱ - - -” ይላሉ ዘመዶቻችንም!
“ልጆቿን መግቦ የማሳደግ ጣጣ ያለባት ሴት አንበሳ ናት። ወንዱማ ጎፈሬውን አቁሞ መተኛት ነው። አድነው ያመጡትን እየቀማ መብላት። ከዚያ ዝንብ እሽሽሽሽ እያሉ በቀን 18 ሠዓት መተኛት። እንዲህም ነግሠው እንዲህም አለፉ አፄ ኃይለሥላሴ። ኮሎኔል መንግሥቱም በንጉሳዊ ካባ ምትክ ወታደራዊ ዩኒፎርም ከመደረባችው ውጭ በጭካኔያቸው ከአጼዎቹ የተለዩ አልነበሩም። ሠቅለዋል። ገርፈዋ። ረሽነዋል። አቃጥለዋል።” ገጽ 64 - ለዚህ ነው ሴት ሚኒስትሮችን ያበዟቸው እንዲሁም ሴት ብረዚደንትም ያስተዋወቁና! ግሩም ምርጫ ነው። ወንዶቹ እንቅልፍ አበዙ አይደል? በዚህ ፍጥነትማ ጠቅላይዋንም በዕድሜያችን እናያታለን ማለት ነው። እርግጥ ነው ኮለኔል መንግሥቱ ግፍ ፈጽመዋል፣ አሁን እስቲ እውነት ይናገሩ ወያኔዎች የፈጸሙት ግፍ ከንጉሡና ከመንጌ ግፍ ያንሳልን? ፍርዱን ላንባቢና ለኅሊናዎ። የወያኔዎች ግፍ ካልተሰማዎና ካልታየዎ ግን ምን ይባላል? ይህ ግፍ ምንም እንኳን እርስዎ እንዲፈጸም ባይሹም፣ በርስዎ ዘመን እየተፈጸመ አይደለምን? ወያኔዎች አልታዘዝም ካላሉዎ በስተቀር፣ በኤርትራ መሬት ሰራዊትዎ እስካለ ድረስ ይህን ዓይነት ግፍ ውስጥ እጅዎ ተነክሮ እንዳለ ይወቁት።
“እንደ አፄ ምኒልክ ሁሉ አጼ ኃይለሥላሴም ገና አልጋወራሽ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሻገር መድኃኒቱ ትምህርት ብቻ መሆኑን በመረዳት ስላደረጉት ተጋድሎ በገንዘባቸው የሰሩትን ተፈሪ መኮንን ተብሎ የተሰየመውን ትምህርት ቤት መርቀው ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር ውስጥ እንዲህ በማለት ገልፀዋል . . .” ገጽ 68 እራስሽ ታመጪው እራስሽ ትፈጪው ማለት ይህ ነው። አስቀድመው ግን ቤተመንግስት ‘በየደብሩ’ ሰሩ እንጂ ትምህርት ቤትስ አልሰሩም ብለው ወቅሰዋቸው ነበር፣ አሁን ደግሞ ትምህርት መድኃኒት መሆኑን ተረድተው እንደነበሩ እየገለጹልን ነው። እውነትን እንደሆን በምንም መልኩ መቅበር አይቻልም።
“በእምነት ፊት አገሪቱ ያላት ጠንካራ መሠረት በአዎንታም በአሉታም ሊገለፅ የሚችል ነው። ይህቺ ጥንታዊ አገር ታላላቆቹን ሃይማኖቶች ከሌሎች ሀገራት በተለየ መልኩ ሠላማዊ በሆነ ሂደት ማስተናገድ መቻሏና በህዝቧም ውስጥ መቻቻል የተሞላበት የኑሮ ባህል መፈጠሩ አስደናቂነት ያለው ሲሆን አሁንም ድረስ ኃይልና ሥልጣንን መጋረድ የሚያስችለው ጥንካሬ ያለው ብርቱ ኃይል በመሆኑ እና የዜጎች ሞራላዊ መሠረት ከርሱ የሚቀዳ መሆኑ በቀጣይ ያገሪቱ ዕጣ ፈንታ ላይ የራሱ ተጽእኖ የሚያሳድር ገፅታ ያለው መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው።” ገጽ 69 - የሱማሌው ክልል ብረዚደንት ነበርና የትግራይ ክልል በተለይም የአክሱም አስተዳዳሪዎች ይህ እውነታ አልገባቸውም ብየ፣ ትንሽ አክሱሜዎችን ላነጫንጫቸው አልኩና በኋላ ግን ‘የሐረሮች የውሃ ጥም ቢከነክነኝ” ትርጉም የለውም ብየ ተውኩት። ሐረሮችን ውሃ የሚከለክሉት ሰዎች ለመሆኑ ሃይማኖት አላቸውን? ያን ያክል ጭካኔ በህጻናትና በእናቶች ላይ ማድረግ በምን መልኩ ነው ምክንያታዊ የሚሆን። አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ያለው ጎንጤ እውነቱን ነው። ታሸም ተበጠበጠም እላይ ያሰፈሩትን ሓቅ ክቡራን ወላጆችዎ በደንብ ገብቷቸዋል ግን ማለት ይቻላል።
“ ጆሮ ያለው ይስማ። ‘ ዋናው ቁምነገር ታሪክ መሥራት እንጂ ታሪክ መፃፍ አይደለም።’ ሲል የዛሬዋን ጀርመን አሁን በምናውቃት መልክና ቅርፅ ፈጠራት የሚባለው ጦረኛውና ጨፍጫፊው አቶቫን ቢስማርክ ተናግሯል። በዋጋ ደረጃ ሊሆን ይችላል። እንደ ኢትዮጵያ ላሉት ታሪክን በወጉ ላልፃፉና ላልመዘገቡ ሀገራት ግን ታሪክን ከመስራት ባልተናነሰ መልኩ ታሪክን በተገቢው መልኩ መፃፍ ዋጋ አለው። አለበለዚያማ በመሪዎች ደረጃ የሃይማኖትን አጥር አልፎ መደጋገፍ፣ መከባበርና መሳተፍ በሀበሻ ምድር እንግዳ ዜና ባልሆነ እንደ ብርቅም ባልተቆጠረ ነበር። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ኖረነው ግን በሰፊው ያልተፃፈው ታሪክ እንኳንስ ለሀገሪቱ ዜጋ ኩራት ለመላ ጥቁር ሕዝብም ጭምር ይተርፍ ነበር።” ገጽ 72 - ጠቅላዩ ምን ሆኑ፣ የቀጠናችን ብቸኛ ፊደል ፈጣሪዎች እንደሆንን፣ ታሪካችንን ወረቀት ከመፈጠሩ በፊት በቆዳ ከዚያም በፊት ከድንጋይ ላይ ወቅረን ያስቀመጥን ህዝቦች መሆናችንን ረስተውታል መሰል። የተጣፈው ታሪክ አልጣመኝም ሊሉ ይችሉ ይሆናል እንጂ፣ እስቲ አሁን ማ ይሙት እንደ ሀበሻ አድርጎ ታሪኩን የጣፈ ህዝብ አለ? ኅሊና ላለውና ለሚያነብ ሰው እኮ ላሊበላም፣ ጣናም ሐረርም በደንቡ የተጣፉ ብርቅና ህያው ታሪኮች ናቸው። አይደለም ለጥቁሩ ለነጩም ሕዝብ ኩራት ናቸው እኮ! ዳሩ ምን ያደርጋል ጠቅላዩም ይህን የተገነዘቡ አይመስሉም። ከጥፋት የማይታደጓቸው፣ ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንደመሻት ውሳኔ ላይም በጣም ዳተኛ በመሆን ሹመት ማከፋፈል ላይ ብቻ የተጠመዱት ለዛ ነው ብንል አልተሳሳትንም። ለማንኛውም ታገሬ ምድር ሰራዊትዎን ማውጣት እንዳይዘነጉ ላስታውስዎ እሻለሁ።
እውነተኛ ፍትህ ለወልቃይቴዎች፣ ለራዮችና ላዲሳበቤዎች! ለሐረሮችም ጭምር!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑28 Oct 2018, 05:19ከክቡር ዲራአዝ ጥሁፍ ለዛሬ እነዚህን ትምህርታዊ ጥቅሶች ቀንጭቢያለው። መልካም ንባብ
“መሪ መሆን የሚችሉ ሰዎች ግን የመምራት ሥራቸውን የሚጀምሩት ዛሬውኑ ነው። የእውነት ለመምራት - - - የስኬት ተምሳሌት- እንዲሆን መምራትህ ውል እንዲይዝ ሥሩ፣ መምራት እና መግዛት አይጥፋህ ድንበሩ። ለምትመራው ጀማ ራሥህን ካልሰጠህ ስስቱን በመተው፣ ‘እኔ’ ያለ ቀን ነው፣ መሪ የሚሞተው። የመምራት ኃይልህን - - - በቅንነት ያዘው በጥበብ አጽድለው ምክንያቱም - - - ተመሪ ውስጥ ነው የመሪ ዕድሜ ያለው።” ገጽ 77 - ድንቅ አባባል ምነአለ ይህችን ግጥምዎን ለሁሉም የአፍሪካ መሪዎች ቢያጋሯቸው። መሪ እንደመሆንዎ መጠን ተመሪዎች ሁሌ እንዲያጨበጭብሉዎት እንዲያቆላምጥዎትና እንዲያሞካሽዎት አይጠብቁ፣ መደረግ ያለበትን የህዝብ ፍትሀዊ ስሜትም ለመስማት ጀሮ ይኑርዎ። ትክክለኛ መልስም በግዜው ሳይዘገዩ ይስጡ። የጣናን ገዳማት እንጂ የጣናን እምቦጭ መጎብኘት አይገባዎትም ነበር፣ አሁንም ጥቂት ነው የዘገዩት፣ ዛሬ ህዝብ ባይጮህ ኖሮ ጣናን ከነጠፈ በኋላ በጎበኙት ነበር! ራያንም ወልቃይትንም የኤርትራን የድንበር ብይንንም “ፊት ለፊት ለመጋፈጥና በፍትሀዊ መንገድ ለመፍታት” መድኋኔዓለም ብርታቱን ይስጥዎ። የምን እነ እንቶኔን መለማመጥ ነው! ታገሬ መሬትም ሰራዊትዎን ማውጣትም አይዘንጉ፣ ማንም አሌ ሊለው የማይችል የኤርትራ ህዝብ ፍትሃዊ ጥያቄ ነውና የዝሆን ጀሮ አይስጡት። አለበለዚያ ግን “ተመሪ ውስጥ ነው የመሪ ዕድሜ ያለው” ያሉት ነገር ተመሪውን የሚያስመርር ከሆነ ‘ጫን ያለው’ ይሆናል።
ምዕራፍ 5 - ሥልጣንና ኃይልን ለመጠቀም ከልብ መሪ መሆን ያስፈልጋል
“ በአንድ አገር ላይ የማስተዳደ ኃላፊነትን የተቀበለ መንግሥት 3 ነገሮችን የግሉ ሊያደርግ ይገባዋል -
1) ጠቃሚ የሆኑ ሀሳቦችን ማፍለቅ መቻል ሲሆን ይህም አገርን ባረጀ-ባፈጀ ወይንም ጊዜው ባለፈበት የአመራር ሥርዓት ወደኅላ እንዳያስቀር ያግዘዋል። - -
2) በሥልጣን አካሄድ ውስጥ አገር ማለት ከተራራና ሸንተረሩ ባለፈ ህብረተሰቡ እንደሆነ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ታዲያ የእነኚህን ዜጎች ፍላጎት ያላማከለ አመራር ለአገር ቆሟል፣ ከማለት ይልቅ አገርን እያጠፋ ነው ማለቱ ሚዛን ይደፋል። - -
3) ውሳኔ ሰጪነት ነው። አንድ መሪ አገሪቱን በሚመለከቱ ማንኛውም ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል። ታዲያ ይህ ውሳኔ የአገርን ሁኔታ የሚወስን በመሆኑ የተጠና ውሳኔ ሰጪነት እጅግ አስፈላጊ ነው።” ገጽ 78 - ግሩም አገላለጽ ነው።
“መሪ ህዝብን ሲመራ ወይም አስተማሪ ተማሪዎቹን ሲያስተምር ሁልጊዜም ቢሆን ለሚከተሉት ጀርባውን መስጠት የለበትም፤ ተከታዮችም ቢሆኑ ከመሪው ጀርባ ያለውን ሁሉ በንቃት መከታተል አለባቸው።” ገጽ 79 - ተመሪዎች ከመሪው ጀርባ ያለውን በንቃት መከታተል አለባቸው ድንቅ አገላለጽ ነው! ለዚያ ነው ቅርሶችን ጠብቁ፣ ህዝብ ሲበደል ዝም አይበሉ፣ የድንበሩን ብይን በአፋጣኝ ፍቱ እያልን ስለፍትህ በሰለጠነ መንገድ ድምጣችንን የምናስተጋባው።
“እምነትን የሚጻረር ሥራ እየሰራን ግን ‘መሪ እሆናለው’ ብለን የምናስብ ከሆነ ቅቤን በህልሙ ብቻ እንደሚበላ ድሀ ከመቆጠር ውጪ የህልማችንን ደፍ የሚሻገር ራዕይ ለመንደፍ እጅጉን እንቸገራለን።” ገጽ 81 እምነትን የሚጻረር የሚሰራማ ከዲያብሎስ እማደል፣ ጣናን አንጥፎ ገዳማትን ማስወረር፣ ላሊበላን እስኪሰነጣጠቅ ሰምቶ ያልሰማ መምሰል - - - እያለ እያለ ቤተስኪያን ማቃጠል! የፈረመበትን ውል ትግባሬ በረባ ባረባ ምክንያት ማዘግየት እምነትን የሚጻረር የቃልአባዮች ስራ ነው እያል ነው። ይሰማል እርስዎ ባይሰሙ የላይኛው ይሰማናል።
“ስለዚህ መሪ መሆን የሚፈልግ ጎበዝ ሁሉ እኔ ከማንም ምንም ዓይነት እርዳታ የማልፈልግ ለራሴ የበቃሁ ሰው ነኝ! ብሎ ማሰብ የለበትም፤ በፍጹም። አብሮን የሚሆን፣ ስህተታችንን የሚነግረን፣ አስፈላጊም ሲሆን የሚረዳን ሰው ያስፈልገናል. የሚያማክረን ፕሮፌሽናል የሆነ ሠው ቢኖረን ደግሞ እጅግ መልካም ነው።” ገጽ 81 - ድንቅ አገላለጽ።
“አንዳንድ ሰዎች ብዙ መልካም ነገሮችን እያደረጉ ያደረጓቸው መልካም ነገሮች ግን ገሃድ እንዳይወጡ ይፈልጋሉ። ይህ ለመሪዎች የማይሰራ ፍልስፍና ነው። ምክንያቱም ከሠራናቸው ሥራዎች መካከል የሚታወቁት እጅግ ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው። ያለህን ዕውቀት በገሀድ ሌሎችን ለመርዳት ተጠቀምበት። ለየት ያለ ሃሳብ ሲኖርህ እነዚህን ሃሳቦች ዕውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ ሚዲያዎችን ተጠቀምባቸው። ሥራዎችህ ላይ ያስመዘገብካቸውን ድሎችም ጭምር ሚዲያዎች እንዲያራግቡ አድርግ። ነገር ግን በሥራህ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሰዎችን በገሃድ ማመስገንህን አትርሳ”። ገጽ 83 - አሁን ጣናን ከነእንቦጩ እንደጎበኙት እንዲስተጋባ ነው የሚሹት፣ ይህ ሁሉ ሆ እያለ ድምጡን የሚያሰማው ህዝብ’ኾ ስለእርስዎ መመረጥም ሆ ሲል የነበረ ነው። አሁን ስልጣኑንና እርካቡን ከያዙ በኋላ እሱንና ስሞታውን አለመስማት ጡር አለው። ህዝብዎና ህዝቤ መሰማትን ብቻ ሳይሆን አፋጣኝ ፍትህን ነው የሚሻ። ታገሬ ምድርም ሰራዊትዎን ማውጣት አይዘንጉ፣ ሁሌም ሲተኙ ሲነሱ ይህ ድምጥ በኅሊናዊ እንዲያስተጋባ ነው በሰለጠነ መንገድ የኤርትራን ህዝብ ድምጥ የምናሰማው።
“ፍቅር ከሌለን ግን መሪ ብንሆን እንኳን የራስን ጥቅም ከማሳደድ በቀር በህዝቡ ህይወት ላይ ጠብ የሚል ነገርን ልናደርግ አንችልም።” ገጽ 83 - ግሩም እውነትን የተላበሰ አገላለጽ።
እውነተኛ ፍትህ፣ ፍትህን እጅግ ለተጠሙ የዋሃን ኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን!
እውነተኛ ፍትህ ለወልቃይቴዎች፣ ለራዮችና ላዲሳበቤዎች! ለሐረሮችም ጭምር!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
ቢያነቡት ይጠቀማሉ viewtopic.php?f=2&t=308857
Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑01 Nov 2018, 11:00ከክቡር ‘ዲራአዝ’ ጥሁፍ ዛሬም እኒህ ነጥቦችን ጨልፊያለው። እየተዝናናን እንማማርበት።
“ለእምነት ትልቁ ቦታ በሚሰጥበት አገር፣ እምነት አልባ ርዕዮትበምን መልኩ ወደ ዕድገትና ፍትህ ሊመራ እንደሚችል በምሁራኑ አልተፈተሸም ወይም አልተተነተነም። ከአገር ነባራዊ ሁኔታ ጋርም ለማስተሳሰር አልተሞከረም።” ገጽ 87 – ድንቅ አባባል ነው፤ እርስዎ በዚህ አይታሙም፣ ቢያንስ ቢያንስ የእግዚአብሔርን ስም በአደባባይ ከጠሩ መሪዎች ጋር ተደምረዋልና። ትልቁ የመደመር ምልክት ላሊበላ እንኳን በጦቢያ ምድር እምነት ምን ያህል ቦታ እንደነበረው ምስክር ነው። እድሜ ባለፈው ሳምንት ሰላማዊ ሰልፍ ለወጡት የዋሃን፣ ይሀው እንኳን ላሊበላን ለመታደግ ፈረንሳዮች ከጎናቹ ነን ማለት ጀምረዋል እየተባለ ነው! ምን ያህል እውነትነት እንዳለው ባናውቅም ድሮም እኮ ፈረንሳይ ላሊበላ ሲታነጽም እጇ ነበረበት የሚሉ ሰዎች አሉ! ማስረጃ ሲባሉ ዓለቱ ላይ የተፈለፈሉት ቤተስኪያኖች ውስጥ የመስቀላውያኑ ምልክት አሻራዎች አሉ ይላሉ። እኛ ደግሞ “እንዲያ ነው እንዴ?” እንላለን። ላሊበላ ላይ የናዚዎቹ አርማ አለ የሚባለውስ እውነት ይሆንን? ጀርመንስ ጣናን ለመታደግ ምን አስባ ይሆን? ብለንም ጠይቀናል። ያም ሆነ ይህ ግን ካገራችን ምድር ሰራዊትዎን ማውጣትዎን አይዘንጉ።
“ ፍላጎቱ ስላለን ብቻ የአገር መሪ ለመሆን መጣር ትርፉ ድካም ነው። ችሎታም ብቻ ለመሪነት የሚያበቃ ነገር አይደለም። መሪ የምንሆነው የግል ፍላጎቶቻችንን ለማግኘት አይደለም። መሪ ስንሆን ትልቅ ኃላፊነትን እንቀበላለን። ይህም ኃላፊነት አገሪቱ ላይ ስላሉ ህብረተሰቦች፣ ስለአገሪቱ ዳር ድንበር መከበር፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ስለመቅረፍ፣ የአገሪቱን መልካም ስም ስለመገንባት፣ ለመጪው ትውልድ የሚሆን መልካም ስራን ስለመስራትም ጭምር ነው። ታዲያ እነዚህን ሁሉ ኃላፊነቶች ልንወጣ የምንችለው በመምራት ብቻ መስሎ ከተሰማን በጣም ተሳስተናል። መሪነት ኃላፊነትን ለመቀበል የተዘጋጀ ጽኑ ልብን ይጠይቃል። ጽኑ ያልሆነ መሪ ግን ለራሱ ጥቅም ብቻ ከማደሩም ባሻገር ከእርሱ በፊት የተሰሩ ስራዎችንም ጭምር ልክ እንደ እንቧይ ካብ ይንዳቸዋል።” ገጽ 93-94 - ጽኑ መሪ መሆን ለአህጉራዊና ዓለማዊ ህጎች መገዛትንም ያጠቃልላል፣ አይደል? እኛም ያልነው የድንበሩ ብይን ይከበር፣ የናንተም የኛም ዳር ድንበር ይከበር፣ ይሰመር ነው። ጽኑ ያልሆነ መሪ ከእርሱ (ከእርሷ) በፊት የተሰሩ ስራዎችንም ጭምር ልክ እንደ እንቧይ ካብ ይንዳቸዋል (ትንዳቸዋለች)፣ አይጣል ነው የሚያስብል፣ ከዚህስ ይሰውረን።
“የሰው ልጆች ኑሮ በሁለት ዓለም ውስጥ ነው። የመጀመሪያው ሁሉም ዓይነት አካላት ለእይታ ምርኮኛ የሆኑበት ውጫዊው ገፅታ ብቻ የሚታይበት ዓለም ነው። ነገር ግን ከዚህ እይታ ጀርባ የተደበቀ፣ እነዚህ አካላት በእርግጥ እንዴት እንደሚከወኑ፤ ሥሪታቸውን፣ ክፍሎቻቸውን እና ጠቅለል ያለ ውህደታቸውን የያዘ ሌላ ሁለተኛ ክፍል አለ። ይህ የዓለም ዓይነት በቶሎ ምርኮኛ የማይሆኑለት፣ ለመረዳት ከባድ የሆነ፣ እውነታን ለማየት የሚጥር አዕምሮ ብቻ እንጂ በዓይን ሊታይ የማይችል ነው። በሳል መሆን ትልቅ የሆኑና ደርዝ ያላቸውን ነገሮች ማውራት ብቻ ሳይሆን ጥቃቅን የሚባሉ ጉዳዮችን ጭምር መረዳት ሲጀመር ነው።” ገጽ 101-102 - ድንቅ አገላለጽ። በሳል መሆን - - “ጥቃቅን የሚባሉ ጉዳዮችን ጭምር መረዳት ሲጀመር ነው። ለምሳሌ፦ ህዝቡ ምን ይላል፣ የኤርትራዉያንስ ሰልፍ ለምንድን አጋጠመኝ? ከአሁን በኋላስ በየሄድኩበት የድጋፍ ወይስ የተቃውሞ ሰልፍ ነው የሚጠብቀኝ? የኤርትራን ልዑላዊነት በተመለከተ ካሁን በኋላ ለሚቀርብልኝ ጥያቄ “እንቅጯን” መናገር አለብኝን? “Demarcation Now! የሚል መፈክር ይዘው ቢመጡብኝስ ምን ብየ ነው እውነተኛና ግልጽ መልስ የምመልሰው? ብለው ራስዎን መጠየቅ ይገባዎታል፤ ምክንያቱም የነገ ተነገ ወዲያ የኤርትራዉያን መሰረታዊ ጥያቄ ይህ ስለሆነ፤ ለምን ቢባል ሌላ እልቂት ላለማየት አንድ ዋስትናችን ስለሆነ፤ ለምን ቢባል በፍትህ አደባባይ የተወሰነልን መሬት በእጃችን ውስጥ መግባቱ ርትዓዊነት ስላለው። “ዘይተርፈካ ጋሻስ አጥቢቕኻ ሰዓሞ” ይላሉ ያገራች ሰዎች፣ ትርጉሟን መቸም አይስቷትም፡ ከበድ ካለችዎት ደግሞ ትግራዮቹን ጠይቋቸው።
እውነተኛ ፍትህ፣ ፍትህን እጅግ ለተጠሙ ዜጎች በሙሉ!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ፈረንሳውያን፡ አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑06 Nov 2018, 00:44የክቡር ዲራአዝን መጠሐፍ እየዳሰስን አምስተኛ ምዕራፍ ደርሰናል፣ ይዘቱ ተማሪ ቤት ስለ መሪነት ሲማሩ ካጠኑት መጠሐፍ ቃል በቃል የወሰዱት ዝርዝሮችን ያጠቃለለ ይመስላል፣ ብዙውን እየተገበሩት እያየን ነው፣ ለዛሬ 11ዱን ነጥቦች እናያለን። ለመዝናናት ያህልም አንዳንድ እይታዎቻችንንም አስፍረናል፤ መቸም “ለምን እንደኛ አታይም?” እንደማትሉ በማመን ነው፣ ምክንያቱም እይታዎቻችን የግድ መመሳሰል ስሌለለባቸው። መልካም ንባብ።
ምዕራፍ 5 ሲጨምቅ - “አንድ ሰው መሪ መሆን ፍላጎቱ ከሆነ የሚከተሉትን ነጥቦች በልቦናው ሊኖራቸው ይገባል፡ በአእምሮው ያመላልሳቸው በምግባሩም ይፈፅማቸው ዘንድ ግድ ነው፡” በማለት 11ዱን ነጥቦች ከገጽ 78- 95 እንዲህ አስቀምጠውታል።
“1) ከእለታት አንድ ቀን ከሚል ቅዥት መውጣት! - አዳዲስ ልምዶችንና ሀሳቦችን በማፍለቅ ሌሎች ሊከተሉት የሚፈልጉት ዓይነት ሰው ሆነው ይገኛሉ። ባሉበት ቦታ ሁሉ ሰዎችን የማነቃቃት ኃይላቸውን ይጠቀሙበታል። - የበላዮቻቸውን ሃሳብ ሳይቀር የማስለወጥና ነገሮችን በተለየ አቅጣጫ እንዲሄድ ማድረግ ይችላሉ። - መሪ መሆን የሚችሉ ሰዎች ራዕይ ያላቸው ሲሆኑ ወደ ራዕያቸው የሚያደርሳቸው ትልቁ መሳሪያ ደግሞ ለራዕያቸው ታማኝ መሆናቸው ነው። ለራዕያቸው እውን መሆን ማድረግ ያለባቸውን ነገሮች በሙሉ ከማድረግ ወደኋላ አይሉም።” (ገጽ 80) - ከእለታት አንድ ቀን ሳይሆን እስቲ ከዛሬ ጀምረው ፈርጠም ብለው የትግራዮቹን ወያኖችና ርዝራዦቻቸውን ተኤርትራ ምድር መውጣት እንደሚገባቸው በቃላት ገረፍ ገረፍ ያድርጓቸው፣ ዞሮ ዞሮ ይህን ማለት ግዴታዎ ነው፣ ይህን ከማለት ወደኋላ አይበሉ። እርስዎ እንደሆኑ ወርዶብዎት በኤርትራ መሬት ለመንሰራፋት መመኘትዎትን ትተውት ይሆናል ብለን እናምናለን!
“2) ሰዎችን መያዝ - መሪ መሆን የሚፈልግ ጎበዝ ሁሉ እኔ ከማንም ምንም ዓይነት እርዳታ የማልፈልግ ለራሴ የበቃሁ ሰው ነኝ! ብሎ ማሰብ የለበትም፤ በፍጹም። አብሮን የሚሆን፣ ስህተታችንን የሚነግረን፣ አስፈላጊም ሲሆን የሚረዳን ሰው ያስፈልገናል። የሚያማክረን ፕሮፌሽናል የሆነ ሠው ቢኖረን ደግሞ እጅግ መልካም ነው። እነዚህ ከኛ ጋር የሚሆኑ ሰዎች ዓላማችንን ከግብ ለማድረስ የየራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረክቱልናል። ነገር ግን፣ ማን በምን ሁኔታ ሊያግዘን እንደሚችል ማወቅ ብልህነት ነው። ምክንያቱም ሰው ለራሱ የሌለውን ሊሰጠን አይችልምና! የኔ ፍላጎት ምንድነው? ታዲያ ይሄንን ነገር ከማን ላገኝ እችላለሁ? ብሎ ራሥን መጠየቅ ከብዙ ድንቅፍቅፍታ ይታደገናል።” (ገጽ 81) – “ሰዎችን መያዝ” ሲባል ሰዎችን አጋርህ ማድረግ ማለት እንጂ እንደ የትግራይ ወያኖችና መሰሎቻቸው እንደሚመስላቸው ‘መያዝ’ ማለት ‘ማሰር፣ መቀፍደድ’ ማለት እንዳይመስለን።
“3) በምናደርጋቸው ነገሮች በሙሉ ወደ በለጠ ብቃት ለመምጣት መጣር - ራሥን ለማንኛውም ነገር ብቁ ነኝ! ብሎ ከመኮፈስ ይልቅ ገና ልንለማመዳቸው የሚገቡ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ማሰብ ሩቅ የሚያስጉዝ ሁነኛ መንገድ እንደሆነ ማወቅ ይገባል። - መሻሻሎችን ለመገምገም የግድ የሌሎችን ምስክርነት ማግኘት አይኖርብንም። የሚሻሻሉ ነገሮችን ዘርዝረን ያሻሻልናቸውንና ገና መሻሻል ያለባቸውን ነገሮች በአትኩሮት በመመርመር ራሣችንን መመዘን እንችላለን።” (ገጽ 82) - የብዙ የአለማችን መሪዎች ችግር “ከኔ ወዲያ ላሳር” የሚል እኩይ አመለካከት ወንበር ላይ ቁጢጥ ሲሉ አእምሯቸው ላይ ስለሚፈናጠጥባቸው ነው፤ ራሳቸውን ለመመዘን ግዜ ስለማይወስዱ ነው። ያገጠጠ ችግር እያለባቸው ችግሩ ተቀርፏል ብለው ራሳቸውን ስለሚያሳምኑ ነው።
“4) የሹፍርናውን ወንበር ያዝ - ንግግርህ አሳማኝ፣ ርዕሱን የጠበቀ እንዲሁም ጠንካራ ይሁን። ያልተገባ ነቀፋን ከማስተላለፍ የተቆጠብክ ሁን። በሌላ አባባል ደግሞ የሌሎችንም ክብር የምትጋፋ ሰው አትሁን።” (ገጽ 82-83) - ምርጥ አባባል ነው! ዘመዶቻችን “ክቡር የኽብረኻ መጠን ነፍሱ፣ ሕሱር የሕስረኻ መጠን ነፍሱ” ያሉት ለዚህም እማይደል! አሁን አሁን እርስዎን መንቀፍ ገታ እያደረግን “እስዎን አንታዘዝ የሚሉትን የትግራይ ወያኔና ርዝራዦቻቸው ላይ እናነጣጥራለን” እስዎንም ሚነቀፉበት ጉዳይ ሲያጋጥም ከመንቀፍ ወደ ኋላ አንልም፣ ሹፍርናውን ቢይዙም አሾፋፈርዎን እየታዘብን እንደ ባለሙያ ትራፊክ ሕግ ዚጥሱ “አረ በሕግ አምላክ ወይም ዓገብ” እንላለን። የመንጃ ፈቃድዎን ካላሳደሱም እንዲሁ እንጠይቅዎታለን። ደግነቱ እርስዎ ለምን ተጠየቅኩ አይሉም!
“5) ራስህን የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም አስተዋውቅ - ሥራዎችህ ላይ ያስመዘገብካቸውን ድሎችም ጭምር ሚዲያዎች እንዲያራግቡት አድርግ። ነገር ግን በሥራህ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሰዎችን በገሃድ ማመስገንህን አትርሳ።” (ገጽ 83) - ለሚገባው ሰው ድንቅ ምክር ነው! እርስዎ ለማ መገርሳንና እነ ገዱንና ያረፉትን የባህርዳሩ ሰውየ ሲያሞግሱ አይተናል። በርግጥ የተማሩትን በተግባር አውለዋል። ጎበዝ ነዎት፣ በስርዎ ያሉትን የትግራይ ወያኖች ግን ታገሬ ተኤርትራ መሬት እንዲወጡ ይንገሯቸው፣ የኛው ትግርኛ አልገባ ብሏቸዋል መሰል። መሬታችንን ረግጠው ባህርና ምድራችንን የሚመኙትን የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸውን በደንብ አድርገው የሕግን የበላይነት ያስተምሩልን።
“6) ለሌሎች ያለንን የተቆርቋሪነት መንፈስ ማሳየት - መሪ እንድንሆን ከሚያበቁን ነገሮች አንዱ ለሰዎች ያለን የተቆርቋሪነት መንፈስ ነው። ለእነሱ ያለን ሀዘኔታ፣ ፍቅር እንዲሁም መልካም አስተሳሰብ የበለጠ ወደኛ እንዲሳቡ ያደርጋቸዋል። - ፍቅር ነገሮችን በሌሎችም ዓይን እንድንመለከት ይረዳናል። ፍቅር ከሌለን ግን መሪ ብንሆን እንኳን የራስን ጥቅም ከማሳደድ በቀር በህዝቡ ህይወት ላይ ጠብ የሚል ነገርን ልናደርግ አንችልም። (ገጽ 83) - ይህማ ካልሆነ እኔ ብቻ ነኝ እውነተኛ፣ ለኔ ያልታየኝ አንዳችም ነገር የለም፣ እኔ ብቻ ያልኩት ነው ትክክል እኔ ብቻ ያየሁት ነው ሓቅ፣ ሓቅ ለኔ ብቻ ነው የተገለጠችልኝ፣ የእኔ ዕውቀት የተትረፈረፈ ነው፣ ከኔ በላይ ላሳር ወደሚል ግትርነት ውስጥ ያስገባል። እኛ ግን የስዎ መንግስት ፋታና ሰላም እንዲያገኝ ብንሻም “በእርስዎ ስር ያሉት የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸው ባገራችን መሬት እስካሉ ድረስ ድምጣችንን ከማሰማት የሚያግተን አንዳችም አካል የለም።” ካብ ዓመታ ደርሖስ ሎም ዘመን እንቋቕሖ ይላሉ ያገራችን ሰዎች፣ መጀመርያ ታገራችን ልዑላዊ መሬት የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸው ይውጡልነና ተዚያ በኋላ ስለ ትልቁ ስዕል ስለ ያፍሪካ ቀንድና ስለ መካከለኛው ምስራቅ አረ ካስፈለገም ስለ ዓለም እናስባለን፣ ሁሉንም በፍቅርና በሰለጠነ መንገድ እንጠይቃለን። ተዚህ በፊት ለሌሎች ተቆርቁረን “ነደኩም ማይ ውረዱላ” ተብለናል ማለትም “ባጎረስን ተነክሰናልና” ነው!
“እዚህ ላይ አብይ ትኩረት ሊቸረው የሚገባው ጉዳይ ግብን ከደረሱበትና ድል ካደረጉ በኋላ መቼ ማቆም እንደሚገባ መማር አስፈላጊ መሆኑን ነው። በአብዛኛው ጊዜ የድል ቅፅበት እጅግ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ የሚገባበት ቅፅበት ነው። ድል በሚሟሟቅበት ጊዜ እብሪተኝነትና ከልክ በላይ በራስ መተማመን በግብ ደረጃ ያስቀመጡትን ጥሰው እንዲያልፉ የሚገፋፋ ነው። ከታቀደው በላይ መጓዝ ድል ካደረጓቸው ጠላቶች በላይ ተጨማሪ ጠላቶች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ስኬትን ከፊት ቀድሞ እንዲሄድ ማድረግና በጥንቃቄ ለታቀደና ለተነደፈ ዕቅድና ስልት ተለዋጭ ማስቀመጥ አያስፈልግም። ግብን በማስቀመጥ ሲደርሱበት ማቆም ይገባል። (ገጽ 84) - ዘመናችን እንደሆነ ብዙ ምሳሌዎችን በቀጠናችን አሳይቶናል! እኛም በሙሉ ነጻነት የምንለው፣ ምንም እንኳን ለመንግስትዎ ፋታ ለመስጠት መታገስ ቢገባንም ነገር ግን አሁንም “የትግራይ ወያኖችንና ርዝራዦቻቸውን” ከፍትህና ርትዕ አዃያ ታገራችን ተኤርትራ መሬት ለአንዲት ደቂቃም ሊሰፍሩ ስለማይገባ፣ ከነሱ ጋር በተሰበሰቡ ቁጥር የኤርትራውያን ፍትሓዊ ጥያቄ በፊትዎ ድቅን እንዲልና የትግራይ ወያኖችንና ርዝራዦቻቸውን በቃላትም ገረፍ ገረፍ እያረጉ እንቅልፍ እንዲነሷቸው ነው። ታገራችን መሬት እስቲወጡ ድረስ ድምጣችንን እንደምናሰማ ደግመን ልንገጽልዎ እንወዳለን።
“7) ጥሪ ማዳመጥ - አለምን ስለመቀየር ከማሰብ ይልቅ ራስን ለመቀየር መወሰን ታላቅነት እንደሆነ የተናገረውን ሊቅ ድንቅ ሃሳብ እንዳለ መውሰዱ ብልህነት ነው፤ ምክንያቱም ራሱን ያላወቀ ማንንም፣ ምንንም ሊያውቅ አይችልም።” (ገጽ 88) - እንዲያ ነው እንጂ! ትልቁን የዓለም እድፍ ከማጠብ በፊት ውስጣዊ እድፍን ማጠብና ማጽዳት ይገባል። ታገሬ ተኤርትራ ጋር በፍቅር ብዙ ማድረግ የሚቻል ቢሆንም ቅሉ፣ በእርስዎ ስር ያሉት የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸው ተጠራርገው ከምድሬ እስቲወጡ ድረስ ተኤርትራ ምድር ገደብ የሌለው ፍቅር እቸራለው ብለው አያስቡ። ኤርትራዊ መሬቱን እንጂ የሰው አገር መሬት ይሰጠኝ ብሎ ድምጡን የማያሰማ ጨዋ ህዝብ መሆኑን ደግሞ አይስቱትም።
“8) ዝንባሌን የማግኘት መሰረታዊ ዕቅድ - የቡድሂዝም እምነት መሥራች እንደሆነ የሚነገርለት ሲድሃርታ ጉተማ የተወለደው ለንግስና ቅርብ ከሆኑ ቤተሰቦች ሲሆን ገና ሳይወለድ በወደፊት ህይወቱ ዙሪያ ሁለት ትንቢቶች እንደተነገሩለት ይገለፃል። በህልሜ አየሁ ብሎ ስለሚወለደው ህፃን (ሲድሃርታ ጉተማ) ዕጣ ፈንታ አንድ የአካባቢው ሰው አባቱ ዘንድ ቀርቦ ሲናገር፣ ወደፊት ጉተማ ስመ ገናና እንደሚሆን እና ዘውድ ቢጭን ጀግና መሪ ሊሆን እንደሚችል፣ ወደ መንፈሣዊው ዓለም ቢዘልቅም ተከታዮቹ የበዙለት መሪ እንደሚሆን ገልፆ ነበር። ቤተቦቹ፣ ልጃቸው የትኛውን መንገድ ቢከተልላቸው ደስተኛ እንደሚሆኑ መገመት አያዳግትም። ታዲያ፣ እንደ ቤተሰቡ ፍላጎትና ጥረት ቢሆን ኖሮ ያ ህፃን ወደ ንግሥናው መንደር አምርቶ ምናልባትም በመቶዎች ዕድሜ ውስጥ የሚረሳ መናኛ ንጉሥ ሆኖ ያልፍ ነበር። ዳሩ ግን፣ ጉተማ ከመሣፍንቱና ከመኳንንቱ ጎራ መሰለፉ ደስታን የሚያስገኝለት አልነበረም፤ ስለዚያም የህይወት ጥሪውን አጥብቆ ፈለገ . . . ይሄው፣ ቡድሃ (የበራለት/ የተገለጠለት) ሆነና በሺዎች የሚቆጠሩ ዘመናት አልፈውም በሚሊዮናት/ቢሊዮናት ከሚቆጠሩ ሰዎች ልብ ውስጥ እንደነገሠ ዘልቋል። (ገጽ 90) - ጉታማ ነው ወይስ ጉተማ? ጉተማ ሲሉት እኮ ትንሽ የቅርብ ዘመዳችን አስመሰሉት! ጉተማ ከዓለማዊ ንግሥና ይልቅ መንፈሣዊ አገልግሎትን የመረጠ ጥሪውን ያዳመጠ ጀግና መሆኑን እንስማማበታለን!
“9) ራስህን መግዛት መለማመድ - በምንኖርበት ዓለም በጣም አጓጊና ጊዜያዊ በሆኑ ጉዳዮች ተሸንፈው ትልቁን ሥዕል ለማጣት የበቁ ጥቂቶቹ አይደሉም። (ገጽ 92) - ሊባል የተፈለገው መልካም ነው ግን አማርኛዋን ትንሽ አወላግደዋታል መሰል! ለማጣት ደግሞ መብቃት ያስፈልጋል እንዴ። ያጡ ተብሎ ይታረም የምን “ለማጣት የበቁ” ብሎ ነገር ነው ደግሞ? መንግስትዎ ራሱን መግዛት ሊለማመድ ይገባዋል፣ በተለይም የትግራይ ወያኖችንና ርዝራዦቻቸውን በደንብ አድርጎ አደብና ስርዓት ማስያዝ ይጠበቅበታል፣ ምክንያቱም እነዚህ የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸው በሀገሬ ምድር እስከዛሬ ድረስም ከፍትህና ርትዕ አፈንግጠው ሰፍረው ይገኛሉና። ይሰማል።
“ትልቅ ዋጋ ያለው በውስጣችን ባለ ሥጋዊ ፍልጎት አንጻር ሳይሆን የመጨረሻዋን እርምጃ የመራመድ ድፍረታችን ላይ ነው። በተመሳሳይ በሌላ የሩቅ ምስራቅ አፈ-ታሪክ ውስጥም የመጨረሻዋን እርምጃ ጠብቆ የመራመድ ጥቅም ሲነገር እንሰማለን። ተስፋቢስነት የማያወጣና የሠነፍ ሰው መገለጫ ባህሪ ሊሆን ይችላል። ጠቢብ ሰው ስለ አካባቢው ሁኔታ ቀድሞ መጠየቅና መመርመር እንዲሁም ስለ መጭውም ጊዜ መገመትና መተንበይ ይፈልጋል። (ገጽ 92) እርግጥ በተለይ ከባድ እርምጃ የመራመድ ድፍረት እርስዎ አሳይተዋል፣ የድንበሩን ብይን በመቀበል ረገድ፣ ሀገሬ ላይ የተበየነው አግባብነት የሌለውን ማዕቀብ እንዲነሳ ያደገሩት ያላሰለሰ ጥረት እጅጉኑ ያስመሰግንዎታል፣ ትልቅ እርምጃም ነው፣ የኤርትራ ህዝብ ለዚህ ድርጊትዎ ላቅ ያለ ክብር ይሰጠዎታል። የርስዎ በዚህ አጭር የስልጣን ዕድሜዎ ለበርካታ የዓለም መንግስታት አርአያ የሚሆን ደፋር እርምጃዎችን አድርገዋል ያስመሰግንዎታል፤ ቢሆንም “የሰው ወርቅ አያደምቅ” እንደሚባለው፣ አገሬ ምድር ውስጥ ሰፍረው ያሉትን የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸውን አደብ ማስገዛት ብቻ ሳይሆን ታገሬ ተኤርትራ ምድር እንዲወጡ ያለችዎን ሚጢጢም ትሁን ጫና ማድረግ ግን ይጠበቅበዎታል።
“10) መሥመርን መለየት እና እሱንም እስከመጨረሻው አጽንቶ መያዝ - አንዳንድ መሪዎች ደግሞ ለገንዘብ ባላቸው ጥብቅ ፍቅር የተነሳ የአገራቸውን ህልውና ጉዳት ላይ የሚጥል ተግባር ሲከውኑ ይታያሉ። በተለይም የአፍሪካ መሪዎች በውጭ አገራት ባንኮች ውስጥ ያላቸው ገንዘብ አገር ላይ ሊሰራበት ቢችል ትልቅ ተዓምር መፍጠር የሚችል እንደሆነ ጥርጥር የለውም። እንዲከተሉት ከተመረጠ ትክክለኛ ፍኖት በማፈንገጥና ሌላ መንገድ በመከተል ምንም አይነት መልካም ነገር ሊገኝ እንደማይቻል ማወቅ ይገባል። ምክንያቱም በበርካታ የተደበቁ ህመሞችና ስቃዮች ክፉኛ የመጠቃት እድል እንዲያመዝን ያደርጋል። በገንዘብ ተሳሳቶ ወይም ቶሎ በመበልፀግ ጉጉት ተገፍቶ ከትክክለኛው መንገድ ለማፈንገጥ ሙከራ ሊደረግ ይችላል። ይህ ጉጉትና ፍላጎት ምንጩ ከቀናኢ ልብ አይደለምና ቀስ በቀስ መጨረሻው በህይወት ውስጥ እርካታ አጥቶ ሁሉንም የህይወት መልክ መሰልቸትንና ትርጉም ማጣትን ያከናንባል ሌላው ቀርቶ ያጋበስነውን ገንዘብ በውል ሳንጠቀመው እንዲሁ ባክኖ እኛንም አባክኖን ይቀራል። ልቅ የሆነ የገንዘብ ፍላጎታችን እንደልክፍት እየባሰ ከቀደመው ጊዜ እጅግ ባጠረ መንገድ ገንዘብ የሚያስገኙ ሌሎች አማራጮችን እንድናገኝ ያቅበዘብዙናል። የኋላ ኋላ የሚፈጠረው የባዶነት ስሜት ከአቅም በላይ ስለሚሆን እርሱን ለመሙላት የትኛውም ዓይነት የእምነት ሥርዓት፣ አደንዛዥ ዕፆች ወይም ሌላ ማንኛውም ማዘውተሪያ ሥፍራ የማይመክቱት ድብታ ውስጥ መውደቃችን እርግጥ ይሆናል። በእንዲህ መልኩ ነገር ካከተመ በኋላ ወደ ትክክለኛው መንገድ የመመለሱ ሂደት ፈታኝና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ይሆናል። ገጽ (94-95) - እንዲህ አይነቶችን ስግብግብ መሪዎች እስቲ ባንድላይ ሆነን ‘ተመለሱ’ እንበላቸው አሻፈረን ካሉ ደግሞ እንረግማቸዋለን፤ ተዚያም እንደ የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸው የሰረቁትንም በወጉ እንዳይበሉት ዘወትር በስጋት ውስጥ ግቢ ነፍስ ውጪ ነፍስ እንዲሉ እናደርጋቸዋለን። የኤርትራ ህዝብ መሥመር “ልዑላዊነቷ የተረጋገጠ፣ አንዲትም ስንዝር ከመሬቷ ይሁን ከባህሯና ካየሯ ያልተሸራረፈች ፍትሀዊት ሀገር መመስረት ነው።” ይህም እውን እንዲሆን በስርዎ ያሉት የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸው ከፍትህ ውጭ ሰፍረውበት ተሚገኙት ያገሬ ምድር እንዲወጡ ሊያሳስቧቸው ይገባል።
11) ኔትዎርክ መዘርጋት (የግንኙነት መስመር-ድር ማበጀት) - ምንም ዓይነት መቅናት ሳይኖር እውቀትና የተግባር ልምድን ከተለያዩ ምንጮች ለማግኘት ዓመታትን ሊያባክኑ ይችላሉ። በዚህ ፈንታ በባለ ጥልቅ ዕውቀት ባለኔቶች የተጠቀሙትን ምሳሌዎች መከተልና ተገቢውን መካሪና ተቆጪ ማግኘት ግድ ይላል። - (ገጽ 95) - መካሪና ተቆጪ የሌለው መሪ ልጓም እንደሌለው ፈረስ መጋለብ ነው የሚያምረው። ሁሌም ላስደንግጥ ሁሌም እኔን ስሙኝ የሚል ሁሌም እኔ ብቻ አዋቂ የሚል ከሆነ ነገር እጅግ ይበላሻል። የተቆጣውንና የመከረውን በጎሪጥ ማየት ከጀመረ ደግሞ መጨረሻው አያምርም። ስለዚህ እኛም ስርዎ ያሉትን የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸውን ታገራችን መሬት በሰላም እንዲወጡ በዘረጉት ኔትዎርክ አድርገው ቁርጡን ይንገሯቸው ስንል በታላቅ ትህትና ነው።
“በራሥ እርምጃ አስር ዓመታት የሚወስደው ምናልባት ቀድመው ከተጓዙበት ምክር ማግኘት ከግማሽ ባነሰ ጊዜ ሊጠናቀቅ ይችላል።” - ገጽ 96 - ድንቅ ብሂል። እርስዎ በዚች አጭር የስልጣን ዘመንዎ ብዙዎች በዕድሜ ልካቸው ያልከወኑትን ክንውን አከናውነዋል፣ ይህን ሓቅ ማንም ሊፈርደው የሚችል ነው፣ ምክንያቱ ደግሞ ከስዎ በፊት አድካሚውን ጉዞ ከተጓዙት ከበርካታዎች ትምህርት በመቅሰምዎና የቀሰሙትን ትምህርት ለመተግበር ቅን ልብ ስላለዎ ነው፣ በርግጥ ሊመሰገኑ ይገባዎታል። ይህም ሲባል በስርዎ ያሉት የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸውን ታገሬ ተኤርትራ መሬት እንዲወጡ ጫና መፍጠርዎን ግን እንዳይዘነጉ ማሳሰብ እወዳለው።
“ይልቁንም፣ በማኬያቪሊ የኃይል መወጣጫና ሥልጣን ማስጠበቂያ ፍልስፍና የተጋረደውን አጥፊ አካሄድ ከውስጣችን አስወግደን ለአንድ ዘመንና ወቅት ከሚያገለግል አሠራር ወጥተን ዘመናትን በተደላደለ መሠረት ላይ ለማቆም የነፍስ ዕውቀት መሠረት ያደረገውን ምስራቃዊ ፍልስፍና ሣይንሳዊ አቅጣጫን ከተከተለው የምዕራብ ፍልስፍና ጋር በማስተሳሰር ኃይልና ሥልጣን በፅኑ መሠረት ላይ እንዲቆም መትጋት ይኖርብናል። ገጽ (96-97) - ድንቅ ብሂል ነው። ያ ኃይልና ሥልጣን የሚቆምበት ፅኑ መሠረት ፍቅር በተባለ የማዕዘን ድንጋይ፣ ሕግ በተባለ ስሚንቶ፣ ፍትሕ በተባለ አሸዋና፣ መከባበር በተባለ ውሃ የተቦካ ታልሆነ ምን ዋጋ አለው! የምስራቁም ፍልስፍና ሆነ የምዕራቡ ፍልስፍና ታባቶቻችን “ተረት” መች ይበልጥና! ለማንኛውም “የሰው ወርቅ አያደምቅምና” በስርዎ ያሉት የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸው ታገሬ ምድር በሰላም እንዲወጡ የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ። ያኔ የኤርትራዉያንና የኢትዮጵያዉያን ፍቅርና ወንድማማችነት በፅኑ መሠረት ያውም በፍቅር፣ በህግ፣ በፍትሕ፣ በመከባበር ላይ የታነጸ ይሆናል። አበቃሁ። በሚቀጥለው ክፍል የተሳካላቸው መሪዎች መገለጫ ባህሪያት ተብለው በመጣህፍዎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች ለመቃኘት እሞክራለው።
ክብር በትግራይ ወያኖች ተንኮልና ደባ የተጠነሰሰውን ማዕቀብ በፅናት በመመከትና በማክሸፍ ላይ ላለው የኤርትራ ህዝብ!
ክብር በኤርትራ ላይ የተጫነውን ማዕቀብ በመፍታት ድንቅና ደፋር እርምጃ በመውሰድ ላይ ላለው ለጀግናው ጠቅላይ አብይ አሕመድ!
ክብር የትግራይ ወያኖችና ርዝራዦቻቸውን ዕንቅልፍ በመንሳት ላይ ለሚገኙት ፋኖዎች!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ፈረንሳውያን፡ አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑16 Nov 2018, 02:19ለዛሬ ክቡር ‘ዲራአዝ’ ማለቴ ጠቅላዩ በተጠና መልኩ ግፈኞችን በድፍረት ወደ “ማረፊያ ቤት” እያስገቡ ስለሆኑ፣ እያደረጉት ያሉትን ቀንደኞቹን ሙሰኞች ወደ አዲሱ ‘ተማሪቤት’ በቶሎ የማስገባት ሂደት ለማበረታታት የዛሬውን ንኡስ ክፍል፣ ጠቅላዩ በቃላቸው “ሲጠቀለሉ” የሚለውን “ሲጠቀልሉ” ብላችሁ እንድታነቡ በአክብሮት እንጠይቃለን። የዛሬው ጥሁፍ በብዛት ስለ ‘ጋዜጠኝነት’ ነው የሚገልጥ እንግዲህ ቀስ እያልን መጎንጨት እንጂ!
“- - - - ‘የባህል አብዮት’ ነፃ (ራስ ገዝ) አስተሣሠብንና ትችት ማቅረብን በማስወገድ ገዢ የሆነውን መደብ ብቻ በጭፍን እንዲያገለግሉ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። ገዢው መደብ ላይ የሚስተዋሉ ጉድፎችንና እንከኖችን በቀላሉ በብዙሀን ትኩረት ውስጥ እንዳይወድቁ ቀላል የሆነ የሚዝናኑበት ነገር (ከእውነት የራቀ እምነት) ለህዝቡ ማቅረብ ላይ ደፋ ቀና ሲያበዙ ይስተዋላል።” (ገጽ 112-3) ልክ በሬዲዮም በቲቪም የአውሮፓን ስፖርትና የምዕራብ ፊልም ረዢም ግዜ ሰጥቶ ማውራትና ማሳየት፣ 24 ሰዓት ዘፈንና ጭፈራ ለወጣቱ ትውልድ ምን ይሆን የሚጠቅመው! ትምህርት አዘል ፕሮግራም እንደማብዛት ዘፈን ብቻ 24 ሰዓት መልቀቅ’ስ ትውልድን በከባድ መሳርያና በመርዝ ጭስ ከመደምሰስ በምን ይለያል! ከምን’ስ ይቆጠር ይሆን? ነጻ ጋዜጠኛነት በአፍሪካ ቀንድ ቢኖር ኖሮ የትግራይ ወያኖች አመራርን በጥያቄ መወጣጠር በተቻለ ነበር፣ ዳሩ ግን ትግርኛችንን የሚሰሙት አይመስሉም? ለማንኛውም እምቢተኛውን የትግራይ ወያኖች ሰራዊት ታገሬ መሬት የሕግ ልዕልናን በማክበር እንዲወጣ ጠቅላዩ ሊያሳስቡት ይገባል።
“ውስን ሀብታችን ውራጅ እና ራሳቸው ባለቤቶቹ ለጣሉት ዕሴት ሳይሆን ለላቀው ከፍታ መነሳሳት መዋል ይኖርበታል።በሙዚቃ ስም የቁሳቁስ ጩኸት፣ በስፖርት ስም እርግጫ፣ በማነቃቃት ሥም ድባቴ ውስጥ የሚያስገቡን፣ እራሳችንን እድናውቅ ሳይሆን እንድንረሳ፣ . . . የሚያደርጉን ከመሆን ይልቅ፣ የጋራ ዕሴቶቻችንን እንድናጎለብት የሚያግዙ መሆን ይኖርባቸዋል። ገጽ 115 - ይህ ኮርስ ለአፍሪካ ቀንድ መገናኛ ብዙሀን ሃላፊዎች ቢሰጥ መልካም ነው። ምን ምን የመሰሉ ተወዳጅ ሙዚቆችን በሰማንበት ጆሮ “የቁሳቁስ ጩኸትና የሙዚቃው ይዘትም እዚህ ግባ የማይባል፣ ስፖርቱም የጦርነት ሜዳ የመሰለበት ዘመንን እየታዘብን ነው። ያም ሆነ ይህ ግን ስለ ሙዚቃ፣ እርግጫ፣ ድባቴ እያወሩ ያገሬን መሬት ማረሳሳት አይቻልም። የትግራይ ወያኖች ሰራዊት ታገሬ መሬት በሰላም ወጥቶ፣ የሕግ የበላይነትን የሚያስተጋቡ ሙዚቃዊ ቅንብሮችን ለመስማት እንዲሁም በፍቅርና የወዳጅነት መንፈስ የተለያዩ ስፖርቶችን በግራ የምንጫወትበትን ግዜ ብቻ ፈጠን ፈጠን እያሉ ያመቻቹ! ሰራዊትዎንም ታገሬ ምድር ያውጡ።
“ዘርፉ በእድሜው ለጋነትና በትምህርትም ያልተደገፈ ከመሆኑ ባሻገር በአመዛኙ ከመሪዎች ጋር ተቀጥላ ሚና ሲጫወት በመኖሩ ዘለቄታ የሌለው፣ ነባሩን አዲስ ባላተራ የሚተካው እንጂ የሚማርበት ባለመሆኑ፣ በኅብረተሰቡ ብቻ ሳይሆን በራሳቸው በጋዜጠኞቹም ጭምር ሙያው በክብር የሚታይ ሳይሆን የቸገረው ጊዜ የሚገፋበት ተደርጎ ይቆጠራል። ይህ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ወጣቶች እንዳይቀላቀሉት ጋሬጣ ፈጥሮ የቆየ ሲሆን ተአማኒነት የሌለው፣ ህዝብን የማያንቀሳቅስ፣ ወደ ተሻለ ምዕራፍ መምራት የማይችል ሽባ አድርጎት ቆይቷል። ይህን ገጽታ ለመቀየር አብሪዎችን ለማሳየት ሙያው እንደ ሕዝባዊ አገልግሎት ተይዞ በአገራዊ ልማት ተጋድሎ ላይ ገድል መፈፀም የሚያስችል የተከበረ የሙያ ዘርፍ ተደርጎም ሊቆጠር ይችላል።” ገጽ 115 ጋዜጠኝነት ሐቅን የማይገልጥ ከሆነ በኅሊና የማይገዛ ተሆነ፣ ሆድ አደር ጋዜጠኝነት ይባላል። ከሆድ አደር ጋዜጠኛ ይሰውረን፣ ምክንያቱም ነጩን ጥቁር ጥቁሩን ነጭ ብሎ ስለሚዘግብ። ማን ነበረች ያቺ ፍጡም የሺጥላ ያሏት እንዲያ ነች መሰል! ምን እሷ ብቻ ስንትና ስንት ከያኔ ነኝ የስነጥበብ ባለሙያ ነኝ አክቲቪስት ነኝ እያለ ለገንዘብ ሲል ኅሊናውን የሸጠ ሞልቶ የለ! ቢሆንም የትግራይ ወያኖችና በሙስና የነቀዙት አመራሮቹ ሲያደናቅፉት የነበረው የድንበር ብይን በአፋጣኝ መተገበር ይገባዋል። ሙሰኛን በማሰር ሰራዊትዎ የሰፈረበትን ያገራችንን ልዑላዊ መሬት ማረሳሳት አይቻልምና!
‘በእርግጥ የፖለቲካ አመራርንና የጋዜጠኛነት ሙያ አንዳች ቁርኝት ያላቸው ይሆን? ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርገን ሌላም እውነታና ሕያው ተምሳሌት አለ። “ - - - የቀድሞው የጋና ፕሬዝዳንት የነበሩ ኩዋሜ ኑክሩማ - የ’Accra Evening News’ መስራችና አሳታሚ ነበሩ። ጋዜጣውንም የልማት ጋዜጠኝነት ተልዕኮን እንዲወጣ አድርገውታል። ዶ/ር ናንዲ አዙኪዌ (1904-1996) የመጀመሪያው የናይጄሪያ አፍሪካዊ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ‘African morning Post’ ጋዜጣ መስራችና አዘጋጅም በመሆን አገልግልለዋል። ጆሞ ኬይታ (1894-1978) በመራር ትግል ኬንያን ከኣንግሊዝ የቅኝ አገዛዝ ቀንበር ያላቀቁ ታላቅ አፍሪካዊ አርበኛ ናቸው። የመጀመሪያው የነፃይቱ ኬንያ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በተጨማሪ የ ‘He Who Brings Together’ ጋዜጣ መስራችና አሳታሚ ነበሩ። ጁሊየስ ኔሬሬ (1922-1999) የአፍሪካ ሶሻሊዝም ፅንሰ-ሃሳብ አፍላቂና አቀንቃኝ የነበሩ ታላቅ መሪ ናቸው። እኚህ ስመጥር የአፍሪካ ሰው የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት የነበሩ ሲሆኦን ለአፍሪካ ህብረት መቋቋም ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ‘Unhurt’ የተሰኘው የፓርቲያቸው ጋዜጣ መስራችና አሳታሚ አበሩ። - ቤንጃሚን ሃሪሰን (1833-1901) 23ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩ ሲሆን በስልጣን ዘመናቸው ለኣአፍሪካ አሜሪካዉያን ዜጎች የመምረጥ መብትን ከማጎናፀፋቸው በላይ በጋዜጠኛነት ሙያቸውም ስለነፃነት አቀንቅነዋል። ዌት አይዘንሀወር (1890-1969) በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ላይ የተሳተፉና የህብረቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ በመሆን ያገለገሉ ታላቅ የጦር ሰው የነበሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ ከ1953-1961 በነበሩት ጊዜያት 34ኛው የኣሜሪካን ፕሬዘዳንት በመሆን ያገለገሉና ጋዜጠኛም በመሆን የሰሩ ታላቅ መሪ ናቸው። ቤኔቶ ሞሶሎኒ (1883-1945) ጋዜጠኛ እና የጣሊያን የብሄራዊ ፊሲስት ፓርቲ መሪ ነበሩ። ከ1922 እስከ 1943 ድረስም የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስቴር በመሆን አገልግለዋል። ኒኮሎ ማኪያቬሊ (1469-1527) ጣሊያናዊ ዜግነት ያለው የፖለቲካ ፈላስፋ፣ ገጣሚና ሙዚቀኛ ነው። ‘The Prince’ በተሰኘ መፀሃፉ ላይ ባሰፈራቸው የፖለቲካ ንድፍ ሀሳቦች በዓለማችን ከፍተኛ ተፀእኖ ካሳረፉ ሥራዎች መካከል አንዱ ነው። ካርል ማርክስ (1818-1883) The Communist Manifesto and Des Kapital፣ በተሰኙ የፖለቲካና የኣኢኮኖሚ ንድፈ ሀሳብን የያዙ ሥራዎቹ ዓለም ከአዲስ የፖለቲካና የኣኢኮኖሚ ቅኝት ጋር ያስተዋወቀ ፈላስፋ፣የኢኮኖሚ ሊቅ፣ የታሪክ ምሁርና አብዮተኛ ሲሆን የጉልምስና እድሜውን በአመዛኙ በጋዜጠኝነት ያሳለፈ፣ ‘New York Tribune’ንን ጨምሮ በአውሮፓና አሜሪካ ተነባቢ ለነበሩ ከስድስት ላላነሱ ታዋቂ ጋዜጦችም ቋሚ አምደኛ ነበር። ” (ገጽ 115-117) - ወይ ጋዜጠኝነት ለካ ይህን ያህል የረቀቀ ሙያ ስለሆነ ነው፣ በርካታ የዓለም መንግስታት ለህሊና የሚሰሩ ጋዜጠኞችን እንደ እሾህ የሚፈሯቸው፣ ያ በሳውዲአረቡ ‘ውርንጭላ’ የሚመራው መንግስት ያን አንድ ጋዜጠኛ እንዲያ አድርጎ በዘግናኝ መልኩ ያጠፋው ለካ፣ እውነተኛ ጋዜጠኝነት ምን ያህል እንደሚፈራ ነው የሚያሳየን! ያም ሆነ ይህ ታገሬ መሬት የትግራዩ ወያኖች ሰራዊት በአፋጣኝ እንዲወጣ ጠቅላዩ እውነትን አንግበው ለፍትሕ ሲሉ ወጠር ወጠር ያድርጉት እንጂ ጉዳዩን! ዛዲያሳ! ።
“ወደ ብርሃን ለመሸጋገር የምናደርገው ጉዞ የሌሎችን ዱካና ፈለግ በመከተል የሚገኝ አይደለም። ራሳችን ጨለማ ውስጥ የጣልነውን መግቢያ ቁልፍ እዚያው ጨለማ ውስጥ በመሆን ለመራመድ የሚያግዙንና ተፈጥሮ ያደለችንን ብርቅ የሆኑ ፀጋዎች ፈልገን በማግኘት ወደ ሁለንተናዊ እድገትና ልማት በሚያሸጋግር ሂደት እንዲታጀብ ማድረግ ይኖርብናል።” (ገጽ 117) አገሬ ላይ በተንኮል የተጠነሰሰ ሴራ ተደርጎ ማዕቀብ የሚባል ነገር እንዲጫንባት የተደረገው በወያኖች ሴራ ነበር፣ አሁን ደግሞ አገሬ ካደረገችው ትግል በተጨማሪ የእነ ዲራአዝ ያላሰለሰ ጥረት ታክሎ ያሴራ ተበጣጥሶ ጉድጓድ ውስጥ ገብቷል። ባገሬና በጦቢያዉያን ቦለቲከኞች አንድ መልካም ተግባር ተከናውኗል። ሌላ አንድ ትልቅ ተግባር ግን ይቀራል፣ ያላገሩ የሰፈረ ሰራዊት ወደ ሃገሩ መመለስና ድንበሩን በማያወላውል አኳኋን ማስመር። ሙሰኛን በማሰር ሊረሳሳ የማይችል ትልቅ የቤት ስራ።
“እኛ ሻማዎች ነን። ከእኛ የሚጠበቀውም የሻማነታችንን ያክል ማብራት ነው። ቀሪው የሥራችን ስኬት ላይ ፈጣሪ ይታከልበታል። የአንዲት ትንሽ ሻማ መብራት ወይም የክብሪት እሳት ጫካ ሙሉ እሳት እንደምትፈጥር ሁሉ በእያንዳንዳችን ያለች የብርሃን ምሳሌ ስናውቅም ሳናውቅም ለሌሎች ህይወት መለወጥ ምክንያት ትሆናለችና ብርሃናችንን ሳናሳንሳት እንድትበራ እድል እንስጣት።” (ገጽ 118) ድንቅ አባባል ነው። አሁን ተማሪቤት የገባው ጀኔራል እንደባውዛ አበራ ነበር ብሎ ስለ ራሱ ያስብ ኖሮ ይሆናል፣ እንበል ለመቶዎች ወይ ለሺዎች እጅግ ደምቆ አብርቶ ይሆናል ግን ግን ግን ስንትና ስንት ማለትም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ምስኪን ሻማዎችን እንዳጠፋ ግን ለሱ አይገባውም! የጦቢያ ህዝብ መቶ ምናምን ሚሊየን ከሆነ፣ ጄነራሉ እንደሁ ምን ግዱ “መቶ ምናምን ሚሊየን ሻማ” ማለትም “100% ቢጠፋ” ምን ግዱ፣ “ ‘መቶ % ቢሆንስ’ ነበር ያለው በዕብሪት የተሞላው ቃለምልልሱ ወቅት”።ለማንኛውም ይህን አሳማ ጄነራል አንጠልጥሎ ያስረከበውን ሻማ የሆነ ፍትሓዊ እጅ አለማመስገን አይቻልም፣ ያም ሆኖ ክቡር ዲራአዝ የድንበር ብይኑን ትግባሬ በደንቡ ማስተግበር ይጠበቅበዎታል፣ ታልሆነም እስዎንም “በቦለቲካዊ ሙስና” ማለትም ያሉትን ባለመተግበር እንደ ቃልዎ ባለመሆን ያስጠይቀዎታል!
“ዕድገት ቅብብሎሽ ነው። እኛ ማድረግ የምንችለውን ሰርተን ለተገቢውና ለሚጠበቅብን ስናስረክበው እሱም በፈንታው ዳር ያደርሰዋል። ሻማዋ ለፋኖሱ እንዳቀበለችው ማለት ነው። ይህ ነው፣ ለዕድገት የድርሻን መወጣት ማለት፤ ሻማነታችንን ማበርከት፤ የሚጠበቅብንን መወጣት። ገጽ 118 ድንቅ አባባል፣ አንዳዴ ሻማዋ ለፋኑሱ ብርኋኗን ከማቀበል ይልቅ እኔ ብቻ ላብራ ብላ ጭራሽ እስክታልቕ ድረስ ሙጭጭ ስትል ግን አያስተዛዝብ ይላሉ? እስቲ አዲሱን ትውልድ ምንም የማያከራክር ድንበርን ሜዳው ላይ ወርደው በወጉ አስምረው ያስረክቡና፣ ለትውልድ ቁርሾ እንዳይወራረስ የሰላም ቅብብሎሽ ያድርጉ።
“የዘመናዊ ጋዜጠኝነት ልክ - - - ስለ የተሞላው የብርጭቆውን ክፍል ከመናገር ይልቅ ስለጎደለው አብዝቶ እንደሚያወራው ሰው ነው። ገጽ 115 - እንዲያማ መሆን የለበትም ስለ ተሞላውም ስለጎደለውም ማውራት አለበት። ለምሳሌ ስለ ኤርትራና ኢትዮጵያ ሁኔታ ስለተፈጠረው ሰላም ስለተጀመረው የንግድ እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን ስላልተተገበረው የድንበር ብይንም በደንብ አድርጎ መነገር አለበት እንጂ፣ እውነትን ፍርጥርጥ አድርጎ አለመግለጽ እኾ በጋዜጠኝነት ሙያ አንጻር ብቻ ሳይሆን በታሪክም ያስጠይቃልና!
ምዕራፍ ስድስት “ነብይ በሀገሩ አይከበርም፤ ታላቅ መሪም ሁልጊዜ በህዝቡ አይወደድም፣” ገጽ 121 - የሜቴኩ ጀኔራልና ዘመዶቻቸው እንዲሁም በሙስና የተዘፈቁ የተለያዩ ‘ተቋማት” መሪዎችና ጥቅም ተጋሪዎቻቸውም እኾ ይችን ጥቅስ ይጠቅሷት ይሆናል፣ አያፍሩም! ለማንኛውም የትግራይ ህዝብ ጎብዞ በጉያው ወሽቋቸው ያሉትን ወንጀለኖችን ለሕግ ልዕልና ሲል ተከፈተ እየተባለ ወዳለው ‘ትምህርት ቤት’ ይላክ፣ ተማሪቤቱ እንደሆነ በሰፈሩት ቁና መሰፈር ምን እንደሚመስል ባግባቡ በፍቅርና ኅሊና ባላቸው መምህራኑ ታግዞ ለማስተማር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ‘ጋዜጠኞች’ እየተቀባበሉ ዘግበውታል! የሆኖ ሆኖ “ሳዕስዕሞ ሓዳርኻ አይትረስዕ” ስለሆነ ነገሩ ተሃገራችን ተኤርትራ ምድር የሕግ የበላይነትን በመጣስ ያለመሬቱ ሰፍሮ የሚገኘውን የጦቢያን ሰራዊት አካል በሙሉ በይፋና በወጉ ያስወጣ ዘንድ ይመከራል። በቀጣይ በምዕራፍ 6 እንረማመዳለን፣ ለዛሬ ግን ይህም በዝቶብናል!
ወዳጃችን፣ ስለ ማበረታታትዎ ከወንበራችን ተነስተን እጅጉኑ አድርገን እናመሰግንዎታለን!
በደሀው ሕዝብ ንብረትና ላብ በሙስና የተጨማለቁትን “አሳማዎች” አሳዶ በመያዝ ላይ ያሉ የፍትህ አካላትን አምላክ አብዝቶ ይባርክ!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ፈረንሳውያን፡ አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
Re: “እርካብና መንበር”፡ እንዲሁም ድንበር፡ የ2018ቱ ዘመን ተሻጋሪ ኤርትራዊ እይታ!
Meleket wrote: ↑22 Nov 2018, 02:37የክቡር ‘ዲራአዝ’ን ጥሁፍ ምዕራፍ 6 “ነብይ በሀገሩ አይከበርም፤ ታላቅ መሪም ሁልጊዜ በህዝቡ አይወደድም፣” የሚለውን ክፍል ጀማምረነዋል። ስለ አመራርና ስለ ሙሴነት በመጣህፍዎ በርካታ ሐቆችን ገልጠዋል እስቲ እኛ ደግሞ ባንድላይ እንረማመድበት፦
“መግቢያና መውጫው፣ መዋያና ማደሪያው የጨነቃት አንዲት ወፍ ከሰው አንደበት ተውሳ እንዲህ ተናገረች አሉ፡ - ‘እትዬ የት ልደር፣ እካብ ላይ ብሰራ እባቡ መከራ፣ እዛፍ ላይ ብሰራ አሞራው መከራ፣ ምድር ላይ ብሰራ እረኛው መከራ። በኃይማኖታዊም ሆነ በማህበራዊ ሣይንስ አስተምህሮት፣ የሰው ልጆች ሁሉ ቅዱስ ተፈጥሮና ነፍሳዊ ፍላጎት ነጻነት እንጂ ባርነት አለመሆኑ ተቀባይነት ያለው እሳቤ ነው። (ገጽ 121) አ/አ ብንቀመጥ የብዙኃን ድምጽ መከራ፣ መቀሌ ብንቀመጥ የሚጢጢዋ ኅሊናችን ድምጽ መከራ፣ ሁመራ ብንሄድ ቢጫዋ ሂሊኮፕተር መከራ ታድያ የት እንሂድ ነው ያሉት እነዚያ በትዕቢት የተወጠሩትና በስርቆት የተካኑት የወያኔ መሪዎች! የዓለም መሪዎች ለህዝባቸው ከእውነተኛ ነጻነት (ሃሳብን እንዳሻህ በኃላፊነት መንፈስ ከመግለጽ፣ ከመደራጀት ነጻነት፣ ያሻህን የመምረጥ፣ እንደፈለግከው በነጻነት የመንቀሳቀስና የመስራትን መብቶች) ገድበውና ደፍጥጠው፣ ነጻነት ለዜጎቻችን አምጥተናል ብለው የሚያስቡ አመራሮች ዓለማችን አስተናግዳለች እያስተናገደችም ነው። አይ አመራር! ቀን ሲከዳቸው የሜቴኮቹ ቢጤ አመራሮች እንደ ወፊቱ ቢናገሩ ማን ይገረማል! እነሱ እንደሆኑ እንዳሻቸው የመስረቅ ነጻነታ ያላቸው ነው የሚመስላቸው።
“ . . . የፍጡሮች ሁሉ ባለቤት የሆነው ፈጣሪ የፈጠራቸውን ፍጥረታት ለፈጠራቸው ዓላማ የሚያድሩ እንዲሆኑ ለማድረግ እሳቤውንና መሻቱን በውስጣቸው ከማኖር ይልቅ ጥሩውን ከመጥፎ፤ ጠቃሚውን ከጎጂ፤ እውነቱን ከሀሰት፤ ብርሃኑን ከጨለማ ይለዩበትና ይመርጡበት ዘንድ ነፃ የሆነ ፈቃድንና ምርጫን ማጎናፀፍ መርጧል።” (ገጽ 122) - ነፃ ምርጫ ሰጥቶ እያለ ፍጡራን ግን የዜጎቻቸውን ነፃነት፣ በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ በነፃነት ያመንክበትን ሃሳብ የመግለጥ መብት ሲነፍጉ ግን አያሳተዛዝብ ይላሉ? ለአብነት ድሮ በደርጉ ዘመን የኢሰፓ አባላት ብቻ ነበር አሉ እንዳሻቸው ወዳሻቸው ቦታ ያለ ምንም ጥያቄ የሚሄዱና የሚበሩ የሚፈነጩም፣ ሌላው ምስኪን ዜጋ ግን ተያዥ አምጣ፣ ገንዘብ ክፈል ምናምን እየተባለ እክል ይፈጸምበት ነበር አሉ። ታሪኩ እንዲያ እያለ ነው የሚቀጥለው አሉ! “ለውጥ መቸ መጣ” ነበር ያለው ብላቴናው! አይ ያፍሪካችን መሪዎች፣ የህዝብን የነፃነት መብት ደፍጥጣችሁ መሪ ነን ትሉ ይሆናል እኮ! ስታሳዝኑ፣ ከናንተ በላይ ሊታዘንለት የሚገባ ፍጡር መቸም አይኖርም። አሁንም ያገርዎ ሰራዊት ባገሬ ሰፍሮ ብርሃኑንና ጨለማውን እኔ ልምረጥላችሁ እያለን ነው፣ እስዎም የተባበሩት ይመስላሉ፣ ምክንያቱም እስከ ዛሬ ለሰራዊትዎ ቁርጡን አውቆ ከኤርትራችን ምድር እንዲወጣ በይፋ መልእኽት አላስተላለፉም። በዚህ ተግባርዎም የሕግን ልዕልና አላስከበሩም፣ የትግራዩን ‘ጄነራል’ በገንዘብ ስርቆት ወንጀል ተጠያቂ ሲያደርጉ እስዎ ኮለኔሉም ቶሎ ብለው ፈውሱን ካላገኙ በሀገር ስርቆት (የኤርትራችንን ልዑላዊ መሬት ለመስረቅ በመቋመጥ) ከተጠያቂነት አያመልጡም፣ ተግባራዊ እርምጃዎች መውሰድ ኣስካልጀመሩ ድረስ ሓቁ ይህ ነው።
“ይህ የራስ ፍላጎትና ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነገሮችን የማግኘት ነፃነት የሰው ልጅ የህይወቱ አስኳል፣ የመኖሩ ምስጢር እንዲሁም መሠረታዊ የፍጥረቱ ክፍል ነውና የሚፈለገውን ነገር ለማግኘት የሌሎችን ይሁንታ የሚናፍቅ ጠባቂ ሳይሆን ተፈጥሮ ያበረከተችለትን የነፃነት አክሊል በራሱ እንዲሁም በጭቁኖች ላይ ለመድፋት ክቡር የሆነውን ህይወቱን ለመሰዋዕትነት እስከማቅረብ የደረሰና የሚደርስ ሆኖ እናገኘዋለን።” (ገጽ 122) - እርግጥ ነው ብዙዎች ለዚህ ቅዱስ ዓላማ በእምነት ተሰውተዋል፣ ያስቸገሩት ይህን በበጎ ፈቃድ የተፈጸመን መስዋዕትነት ዋጋ የሚያሳጡ በህይወት አለን የሚሉ በድን መሪዎች በዓለማችን መኖራቸው ነው። የህዝብን መብት በመገደብ ብቻ ደስታ የሚያገኙ ወፈፌ መሪዎች እጅግ በጣም ሊታዘንላቸው ይገባል። የመንቀሳቀስ የመደራጀት ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብቶችን የሚገድቡ፣ ምን ማምረት እንዳለበት ገበሬውን ሊያስገድዱ የሚሹ፣ ገበሬው ማጀት ድረስ ዘልቀው ለጥፋት የሚገቡ፣ ነጋዴውን እንዳሻው እንዳይነግድ እክል የሚፈጥሩ፣ ቡሆ ሳይሆን ወሃ ቀጠነ የሚሉ፣ በዘርና በኃይማኖት ሰበብ ህዝብን የሚከፋፍሉ አመራሮችን ያየች ዓለማችን እጅግ የሚያስተዛዝብ ታሪክን ሰንዳለች! እንዲያው ባጭሩ እያሱን እንኳ መሆን አቅቷቸው ሳሉ ሙሴ ነን ብለው የሚያስቡ መሪዎች እጅግ ያሳዝናሉ!
“ከዚህ የእውነታ መሠረት በመነሳት ሰብዓዊነትን ወደ ትክክለኛ መሠረቱ ለመመለስ የምናደርገው ትግል በጭቆና ሥር ያሉ ሕዝቦች እስካሉ ድረስ ትክክለኛ ጊዜው ዛሬ ሊባል የማይችል፣ ተከታይና ደጋፊ ደቀ-መዝሙር የማያጣ መሆኑ ይታሰባል። በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ሕይወታችን ውስጥ የጋራ ተጠቃሚነታችንን የሚያረጋግጡ እርምጃዎቻችን ሰፊ ተቀባይነትን የሚያተርፉ ቅዱስ ተግባራት በመሆናቸው በዙሪያችን የሚኮለኮለው ጋሻ ጃግሬ እልፈ ኣእላፍ ሠራዊት እንዲሆን ይጠበቃል።” (ገጽ 122) -ጠቅላዩ በዚህ ረገድ ላገርዎ ጭቁን ህዝብ ያደረጉት ገድልና መስዋዕትነት ለዘመናት ታግለናል ካሉ ነገር ግን ወደ ሌባነት ከተቀየሩት አሳማዎች ጋር ሲነጻጸር ብዙ ድንቅ ተግባራትን አከናውነዋል። ቢሆንም ታገሬ ተኤርትራ መሬት የወያኖቹን ሰራዊት ባለማስወጣትዎ ግን ተወቃሽ ነዎት። ፍቅር የሰውን አይመኝም። ዛድያ ታገሬ መሬት ሰራዊትዎን ማስወጣት ላይ ካልተጉ እኮ የሰው መሬት ተመኝተዋል ማለት ነው፣ ይህ ደግሞ የፍቅር ስራ ሳይሆን የድሮ ተስፋፊዎችን ቕዠት የሙጥኝ እንደማለት ነው የሚቆጠረው፣ ወደዱም ጠሉም ይህን እብሪተኝነት ገደብ ሊያደርጉለት ይገባል።
“የሙሴ የመሪነት ታሪክ ውስጥ ጥልቅና ሰፊ የአርነት ትግል፣ ጥበብ የተሞላበት ጉዞ፣ ያለ በቂ ዝግጅትና እሳቤ ለነፃ አውጪነት መሪ ሆኖ መመረጥ የሚፈጥረውን መደናበር . . . ወዘተ ተንፀባርቀውበት እናገኛለን። ነፃ ወጪው አካል ስለነፃነት ያለው እንጭጭ የሆነና ያልበሰለ ዕውቀት ትዕግስት ከማስጨረስ አልፎ ተስፋ አስቆራጭ መሆኑ፣ ከሥልጣን ተገዳዳሪዎቹ የሚሰነዘሩ ፈተናዎችና ነፃነትን ለመቀዳጀት በሚደረገው ትግል ላይ የሚፈጥረው ውክቢያና እክል፣ እንዲሁም ለተግዳሮቶቹ መፍትሄ ለመስጠት የትግል ስልቶችና አቅጣጫዎችን መቀያየር ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው።” (ገጽ 123) ይቺ ዓለማችን ስንት ሙሴዎችን ሰልቅጣ ይሆን! ነጻ ወጪው ብቻ ሳይሆን ነጻ አውጪ ነኝ የሚለውን ስለነፃነት ያለው አመለካከት የተንጋደደና የተወላገደ እኔ ብቻ በማስበዉ አካሄድ ይኬድ የማለት አባዜ፣ ‘ነፃ ያልወጡ ነፃ ኣውጪዎች’ እንዳሉት አቶ አንዳርጋቸው፣ በስም ነፃነት አውጪነት ህዝቦች ላይ ውክቢያ የበዛበትንና እፎይታ የማይታወቅበትን ኑሮ ሲቆልሉ ግን እጅግ ያሳዝናሉ! ነፃ ወጪውን ሳይሆን ነፃ አውጪ ነኝ የሚለውን በስርቆት የተዘፈዘፈ አካልን ትዝብት ውስጥ ይጥላል። የእያሱን ሚና በቅጡ መጫወት ያልቻሉ መሪዎች ራሳቸውን እንደ ሙሴ መቁጠራችው ደግሞ ያስተዛዝባል። ለማንኛውም ታገሬ ተኤርትራ ምድር ሰራዊትዎን ያውጡ እንጂ!
“እሥራኤላውያኑ በፈርኦኖቹ የሚደርስባቸው ገደብ አልባ የሆነውን ግፍ፣ መከራ እና እንግልት የህይወታቸው ክፋይ የሆነ ዕጣ ፋንታቸው እስኪመስል ድረስ በፀጋ ተቀብለውት ይኖሩ ነበር። ቅጥ ያጣ የባርነት ሥርዓት ውስጥ በመሆን ይደርስባቸው የነበረው መራር እንግልትና መገፋት፤ መዋረድና ዝቅ መደረግ፤ ስቃይና ሰቆቃ፣ መሠረታዊ የሰው ልጅ ፍጥረት ክፋይ የሆነውን በራስ ፈቃድና ነፃነት ያሻውን የማግኘትና የመሆን ፍላጎት እንዲዘነጉትና ራሳቸውን ለመበደልና ለሌሎች መገልገያ የተፈጠሩ አቅመ ቢስ እንደሆኑ እንዲያስቡ ጫና ፈጥሮባቸዋል።” (ገጽ 123) መሰረታዊ የሰው ልጆችን መብት ገፈው፣ አገር እያስተዳደርን ነን ብለው የሚያስቡ ወፈፌዎች በበዙባት ዓለማችን ይህን የመሰለ አንቀጽ በመጻፍ ሓቅን መግለጥዎ በእርግጥ ያስመሰግንዎታል፣ ቢሆንም የጦቢያን ሰራዊት ካገራችን ከኤርትራ ማውጣት ግን ይገባዎታል። ምክንያቱም የሕግ ልዕልና ይከበር ሲባል የገንዘብ ሌባ-አመራርን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን የሰው ምድር ሊሰርቅ ያቆፈቆፈን የመሬት ሌባንም ይመለከታል። ያለ መሬቱ ሰፍሮ ያለን የመሬት ሌባ አደብ ያስገዙ፣ ታልሆነ ግን እርስዎም የሌብነቱ አካል ወይም ሌባ ነዎት ለማለት እንገደዳለን። ሓቁ ይህ ነው።
“. . . በመገፋት ጠፍር ተተብትበው፣ በባርነት ቀንበር ታስረው፤ ህይወት ማለት ማጣት እንጂ ማግኘት፣ ማጎብደድ እንጂ ቀና ማለት፣ ማገልገል እንጂ መገልገል፣ ማዳረስ እንጂ መድረስ መሆኑ ትርጉሙ ተዛብቶባቸው ሲኖሩ ህይወት አንዱን መልኳን ብቻ እያሳየች በእኩይ አለንጋዋ ስትገርፋችው የምትኖር ይመስላል። ታዲያ ይህን ጊዜ በእንግልት ብዛት የደከሙ ገላዎች፣ በመዋረድና በመናቅ የተጎዱ ሥነ-ልቦናዎች፤ በጥላቻና በጭካኔ ግፍ የተፈፀመባቸው፣ ሰብዓዊነቶች ማረፊያ ይሆናቸው ምቹ ምኩራብ፣ ማገገሚያ ይሆናችው ዘንድ እውን የሚሆን ተስፋ እንዲሁም መካሻ እንዲሆናቸው ዋጋው ከፍ ያለ ክብር ማግኘት የሚያስችል ነፃነትን ማለምና ተስፋ ማድረግ ይጀምራሉ።” (ገጽ 124) - ከፍትሕ አንጻር ስናየው እርስዎ ለብዙዎች መካሻ ሆነዋል። ብዙ አፍሪካውያን ምሁራን ግን መካሻ ከመሆን ይልቅ የምሁር አጎብዳጅ ሲሆኑ ነጩን ጥቁር ጥቁሩን ነጭ እያሉ ኅሊናቸውን በርካሽ ዋጋ ሽጠው ሲስተዋሉ ግን እጅጉኑ ያስተዛዝባል፣ ቀን ሲጥል ደግሞ እጅግ አረ እጅግ በጣም አሳዛኞች ይሆናሉ። ለማንኛውም የምሁር አጎብዳጅ ከመሆን ይሰውረን። እስዎም ወለም ዘለም ሳይሉ የትግራይ ወያኔ መሪዎችን ሰብስበው የጦቢያ ሰራዊት ከሕግ ውጪ ሰፍሮበት ካለው ካገሬ መሬት እንዲወጣ ያሳስቡ። ለስዎም ያልተዋጠችልዎን ድንበርም የሕግ ልዕልና መከበር ስላለበት በወጉ ያስምሩ።
“እሥራኤላውያኑ ይኖሩበት ከነበረው የባርነት ቀጠና ፈጣሪ ወደ ነፃነት ግዛት እንዲያሻግራቸው ግፈኞች በሆኑት ፈርኦኖች እንክብካቤ ያደገውን ሙሴ ከመካከላቸው መርጦ ነፃ አውጪና መሪ አድርጎ አስነሳላቸው። ሙሴም ከፈጣሪው ዘንድ እሥራኤላውያኑ እየደረሰባቸው ካለው ግፍና ጭቆና ነፃ በማውጣት ሕዝቡንም ይዞ ወተትና ማር ወደ ሚፈልቅባት የራሳቸው ወደ ሆነችው የተስፋይቱ ምድር እንዲያመራ ትዕዛዝን ተቀበለ። ለዚህ ታላቅ ገድል እጩ የሆነው ሙሴ ተጨቋኝ ለሆኑት እስራኤላውያን ባዳ ያልሆነ የአብራካችው ክፋይ የሆነ መልዕክተኛ ነበር። . . . ” (ገጽ 124) እርስዎ ለብዙሃኑ ጦቢያዊ ሙሴ ነዎት ሲባል ሰምቻለው። ያ ባህርዳር ላይ ከድል ዋዜማ ያረፈውን የተቀበረው የብአዴኑን ታጋይና መሰሎቹን እንደ ሙሴ ከወሰድናቸው ግን እርስዎ እንደ እያሱ ነዎት! ያም ሆነ ይህ ‘ቆራጡ’ ሳይሆን ‘ርህሩሁ’ አመራርዎ ለኤርትራውያኑም ተርፏል፣ ቢሆንም ሰራዊትዎን ታገሬ ተኤርትራ ምድር ስላላወጡ ገና ያልተከናወነ ትልቅ ስራ ይቀራዎታል።
“ለዘመናት በባርነት ቀንበርና በመብት አፈና ተረግጠው ለቆዩት እሥራኤላውያን መድህን ተደርጎ በፈጣሪ የተመረጠውና የተላከው ሙሴ ለዚህ ታላቅ ኃላፊነት መታጨቱን በይሁንታ ለመቀበል በከፍተኛ የስሜት መናወጥ ውስጥ ማለፍ ግድ ሆኖበት ነበር። በሰዎች ስብስብ ዙሪያ ሃሳቡን በሚገባ ለማስተላለፍ ዓይናፋርና ኮልታፋ የሆነን ግለሰብ ታላቅ ባለግርማና ተፈሪ ወደሆነ የብዙኃን ንጉሥ ማሸጋገር ከባድ ይመስላል፤ “ሕዝብን ከፍጡር ባርነት ወደ ፈጣሪ ባርነት እንዳሻግርና ወደ ተስፋይቱ ምድር እንድመራቸው ፈጣሪ ልኾኛልና ልቀቅ! ፈጣሪህ እኔንም አንተንም ያስገኘ ህያው የዓለማት ጌታ መሆኑን አበስርሀለሁ!” ብሎ የአምላክን ጥሪ እንዲያስተጋባ ትዕዛዝ መቀበልም እጅግ ፈታኝ ነበር። . . . ” (ገጽ 125) - እስዎ ትንሽ ኮልታፋ ነዎት አይደል! የፈጣሪን ስምም በይፋ ባደባባይ ያውም በመስቀል አደባባይ የጠሩ ብርቅና ድንቅ ወጣት መሪ ነዎት። ሙሴ ሙሴ ይሸታሉ ማለትም ይቻላል። ቢሆንም ሙሴነትዎ ለጦቢያውያን እንጂ አገሬ ኤርትራ እንደሆነች ብዙ ሙሴዎች አሏት ያውም የተሰዉ የተስፋይቱን ምድር ሳይረግጡ ለዓላማ ለተልዕኾ የተሰው ሙሴዎች አሏት። በህይወትም ብዙ ሙሴዎች አሏት፣ እነዚህ በህይወት ያሉት ሙሴዎች ደግሞ አገራችው ምድሯን አየሯን ባሕሯን ሙሉ በሙሉ ያላንዳች መሸራረፍ በቁጥጥር ስር እስክታደርግ ድረስ በኃላፊነት ይሰራሉ። ሰራዊትዎን ታገሬ ምድር ማውጣትዎን አይዘንጉ። አለበለዚያ ከሙሴነት ወይ ከኢያሱነት ወደ ፈርዖንነት እዳይለወጡ እንሰጋለን! ስልጣን እንደሆን ያባልጋል። ወያኖች እንኳን ቶቢያን በያዙበት ወቅት በጥፊ ብትመታቸው ‘ዲሞክራሲያዊ መብቱ ነው” ብለው ዝም ነበር የሚሉት አሉ፣ የኋላ ኋላ ስልጣኗን ካደላደሉ በኋላ ግን መርከቡንም አየሩንም ምኑንም አግበስብሶ መስረቅ፣ የተቃወመን ደግሞ በጥይት ማጨድ ሆነ ስራቸው።
“ለዚህ ታላቅ ገድል መታጨቱን ከፈጣሪው በቀረቡ ልዩ ልዩ ተአምራት እንዲያረጋግጥ እና በውስጡም ምንም ዓይነት ፍርሃት ሊሰማው እንደማይገባ ከተደረገ በኋላ ግን ዕቅድና ትልሙን ያጋራው ይቀበለው ዘንድ ወንድሙ አሮን አጋሩ እንዲሆን ተደረገለት። ይህም ከፊቱ ለሚጠብቀው ብርቱ ትግል ከፍተኛ ብርታትና የራስ መተማመን አስገኝቶለታል።” (ገጽ 125) - አቦ ለማ ነው የሚባሉት አዎ አቦ ለማ አሮን አሮን ይሸታሉ እስዎ ደግሞ ሙሴ ሙሴ፣ ሚስትዎ ኢትዮጵያዊት ነች አይደል? እንደነ ዶ/ር ነጋሶ አይደሉም አይደል? ሚሪያም የምትባል ቅናታም እህት አለችዎት ወይ? ያም ሆነ ይህ ተምድራችን ተኤርትራ የወያኖቹን ሰራዊት ማውጣት እስከ አሁን ያልጀመሩት ትልቁ የቤት ስራዎ መሆኑን አቦ ለማም ሊነግሩዎት ይገባል። ሙሴ መቸም በህግ ልዕልና የሚያምን ነቢይ ነው የነበረው። ስንትና ስንት ሕግን ጽፎ የሰጠ እማደል! ይወገሩ፣ ዓይናቸው ይጥፋ ወዘተ የሚልንም ሕግ ያወጣ። ተኤርትራ ምድር ያልወጣ የጦቢያ ሰራዊትን ደግሞ እንደ ሙሴ ይወገር ዓይኑ ይውጣ ባንልም እንኳን በወጉ ግን ሰፍሮበት ያለው ምድር ምድሩ አለመሆኑ ገለጻ ተደርጎለት በግልጥና በይፋ ተመሰጋግኖ ሊወጣ ይገባል እንላለን።
ለሕግ ልዕልና የሚተጉትን ዜጎቻችንን አምላክ አብዝቶ ይባርክ!
ጣናንና ላሊበላን ለመታደግ የሚጥሩትንና የሚተጉትን ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ፈረንሳውያን ኣሜሪኮችንም ጭምር፡ አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!
በኤርትራ መሬት ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ሰራዊት በሰላማዊ ትግል ለማስወጣት የሚጥሩና የሚተጉትን ኤርትራዉያን አምላክ ኣብዝቶ ይባርክ!