Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6038
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

መለኮት ለብቻ። ሳይንስ ለብቻ። ፖለትካ ለብቻ።

Post by Naga Tuma » 17 Mar 2025, 00:08

ይህን ሀሳብ እና አስተሳሰብ እዚህ መድረክ ወይም ፎረም ላይ የተለያየ ግዜ ፅፌኣለሁ።

እኔ ሳይንቲስት ነኝ ባይ ነኝ። አስተሳሰቤ ሳይንሳዊ ነዉ ማለት ነዉ።

በቅርቡ የተገለጠልኝ የመለኮታዊ አሰራር ጥልቀትን ማብራራት ከአቅሜ በላይ ነዉ። ማብራራት የሚችል ኣንድ ሰዉ እዚህ ምድር ላይ የሚገኝ ኣይመስለኝም።

መቼ እንደተጻፈ ባላዉቅም የተጻፈ ትንቢት መኖሩን ኣዉቃለሁ። ተፈጸመ እንደሚባልም ኣዉቃለሁ።

መለኮታዊ ጥልቅ አሰራር በሁለት ቃላት ይደመደማል። ተጻፈ። ተፈጸመ። ይህ መላ ምት ኣይዴለም።

ጥልቅ አሰራሩ ለዘላለም ይዘከራል። ተጻፈ እና ተፈጸመ የማይፋቁ ናቸዉ።

የቫቲካን ፖፕ የማናዉቀዉ ዕዉቀት ኣለ ብሎ ላዉዳቶ ሲን እ አ አ በ2015 ኣወጣ።

ፖፕ ሆኖ በሁለት ዓመታት ዉስጥ ነዉ ያን እንሲክሊካል ያወጣዉ።

የማናዉቀዉ ዕዉቀት ኣለ በማለት በር ከፍቷል። በሩ ከዛ በፊትም የተከፈተ መሆኑን ጠንቅቆ እንደምያዉቅ እገምታለሁ። የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ በርገድ ኣድርጎ ነዉ የከፈተዉ።

እነሱ ጠንቅቀዉ የምያዉቁትን ተምረናል የሚሉ የሃገሬ ሰዎች ፍንጭ እንደሌላቸዉ ማስተዋል ኣስደንጋጭ ነዉ።

ፖፕ ሆኖ በሁለት ዓመታት ዉስጥ የማናዉቀዉ ዕዉቀት ኣለ ብሎ ላዉዳቶ ሲን ለሕዝብ ይፋ ያደረገዉ ኣሁን ደግሞ የካቶሊክን ድርጅት ለማሻሻል ወይም ሪፎርም ለማድረግ የሶስት ዓመት ግዜ ዕቅድ እንዳለዉ ለሕዝብ ይፋ ኣደረገ።

ኣንድ የቫቲካን ፖፕ የማናዉቀዉ ዕዉቀት ኣለ ብሎ ላዉዳቶ ሲን ፖፕ ሆኖ ተሹሞ በሁለት ዓመት ግዜ ዉስጥ ለሕዝብ ይፋ ካደረገ የዚህ ዘመን መላዕክቶች የመለኮትን ጥልቅ አሰራር በማስተዋል እና ምስክርነታቸዉን ከጫፍ እስከ ጫፍ በመስጠት ኪዳነ ዘለዓለምን ማዘጋጀት ኣይችሉም?

ከመቶዎች ዓመታት በፊት ተበርግዶ ጸሓይ የሞቀዉን በር እንቀርቅረዉ ማለት ከምን ዐይነት ኣእምሮ የሚመጣ ነዉ? ከምን ዐይነት ትምህርት የሚመጣ ነዉ? ምን ዐይነት ሳይንስ ነዉ?

ብሉይ ኪዳን ተብሎ አዲስ ኪዳን ከተባለ፣ አዲስ ኪዳን ተብሎ ኪዳነ ዘለዓለም ወይም ቴስታመንት ፎር ኤተርኒቲ ማለት ኣይቻልም?

ዝንፍ የማይለዉ ሳይንስ ስለ መለኮታዊ አሰራር ጥልቀትም ኣመልካች ሆኗል። ማብራራት የማይችለዉ አሰራር ነዉ።

ዝንፍ የማይለዉ ሳይንስ ትንቢቱ ኣልተጻፈም ማለት ኣይችልም። ኣልተፈጸመም ማለትም ኣይችልም። በጥልቁ መለኮታዊ አሰራር ስር ነዉ ዝንፍ የማይለዉ።

ፖለትካ ሳይንስን መተካት የማይችል የፖሊሲ ጥናት እና ተግባር ይመስለኛል።

ለዚህ ነዉ እኔ መለኮት ለብቻ፣ ሳይንስ ለብቻ፣ ፖለትካ ለብቻ ናቸዉ ያልኩኝ እና የምለዉ።