በኢትዮጵያ እዴሳ ወይም ህዳሴ ዘመን ሁለተኛ ደረጃ ያጠናቀቀ ወይም ያለፈ ኢትዮጵያዊ መጠየቅ የሚችል ሁለት ቀላል ጥያቄዎች፥
በባህል የኖረ ሕዝብ፣ በፀሎት የኖረ ሕዝብ የለመደዉን ባህል ያስተምራል፣ የሰማዉን ፀሎት ይፀልያል፣ ያስቀድሳል።
የባህል እንቨስትመንቱን፣ የፀሎት እንቨስትመንቱን ዉጤት ይጠብቃል።
የዕዉቀት ምንጩ ባህሉም፣ ፀሎቱም ነዉ።
መደበኛ ትምህርት እና ይህን ትምህርት የዕዉቀት ምንጭ ማድረግ በባህል ለኖረ ሕዝብ በኣጭር ግዜ የሚመጣ ኣይመስለኝም።
ይህ ሂደት ግዜ እንደሚወስድ ያለፉት ሃምሳ ዓመታት ገደማ ኢትዮጵያ ያለፈችበት ዉጥንቅጥ በቂ የታሪክ ማስረጃ ነዉ።
ባህል በሰላም ኣብሮ ያኖረን ሕዝብ የመደበኛ ትምህርት ዕዉቀት በደንብ ስር ሳይሰድ ተናወጠ ቢባል ማጋነን ኣይመስለኝም።
የመደበኛ ትምህርት በሃገር ዉስጥ መስፋፋት መጀመር እና የሃገር በራሷ ልጆች መናወጥ ዘመን መገጣጠም በቂ የታሪክ ማስረጃ ነዉ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርዚቲ ካፍቴርያ መከፈት እና ከካፍቴርያዉ የተመገቡ ተማሪዎች በዚህ ዘመን ዉስጥ ጉልህ ሚና መኖር በቂ የታሪክ ማስረጃ ነዉ።
የዉጪ ተፅዕኖ ኣለበት ቢባል የለእነሱ ተሳታፊነት ኣይዴለም። በቅንነት ነዉ ቢባል እንኳ ያሳተፏቸዉ ዘመናዊ ትምህርት ዉስጥ ረጅም ልምድ የነበራቸዉ መሆኑም በቂ የታሪክ ማስረጃ ነዉ።
በቅንነት ለለፉት እና ለከፈሉት ዋጋ ወቀሳ ሳይሆን ወደፊት የምያራምድ ላይ ማተኮር ያለፍንበትን ቀላል ኣመላካቾች በማስታወስ ጭምር ነዉ ለማለት ነዉ።
ከርቀት ሆኜ እንደሚገባኝ ነፃነት ያሉት ሉዓላዊ እና እኩልነት ባሉት ተሸንፈዉ ሃገር በኮሪደር ልማትም ይሁን መስመር ያዘች እንጂ በዕዉቀት ስር የሰደደ መሠረት ኣልያዘችም።
የኢትዮጵያ እዴሳ ወይም ህዳሴ ዘመን የሕዝባችን ዕዉቀት ስር የሰደደ እንዲሆን ነዉ። ለሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ ወይም ከዛ በላይ የኖረን አቧራ በማራገፍ።
ለዚህ አቧራ ማራገፍ ጥረት ቅምሻ እንዲሆን በቅርቡ የበለጠ ግልጽ የሆነልኝ ምሳሌ ይሀዉ፥
ኩት (ኦሮምኛ)
ኩረት (ቁረጥ) (አማርኛ)
ከት (እንግልዘኛ)
ይህ ለምሳሌ ያልኩኝ ወደፊት ብዙ የሳይንስ ጥናቶች መፍለቅ እንደሚችሉ ኣመልካች ነዉ።
ለዚህ ነዉ ሁለተኛ ደረጀ ትምህርት ኢትዮጵያ ዉስጥ ያጠናቀቀ ወይም ያለፈ ኢትቶጵያዊ ሁለት ቀላል ጥያቄዎችን መጠየቅ የምያስፈልገዉ።
ኣብሮህ ወይም ኣብራህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፈተና ተፈትኖ ወይም ተፈትና ከፍተኛዉን ዉጤት ያገኘ ወይም ያገኘች ወይም ያገኙ ማን እንደሆነ ወይም እንደሆነች ወይም እንደሆኑ ታስታዉሳለህ ወይም ታስታዊሽያለሽ?
ካስታወስክ ወይም ካስታወሽ ዛሬ የት እንዳለ ወይም እንዳለች ወይም እንዳሉ ታዉቃለህ ወይም ታዉቂያለሽ?
ይህን ማወቅ ወይም ማስታወስ የፀሎት መጽሓፍ ዉስጥ ከሚታወሱ ስሞች በላይ ከባድ ነዉ?
እዴሳ በብዙ ነገሮች ላይ ቦግ ባይ ነዉ። ብርሃን ስለሆነ። በሪሳ ስለሆነ።
Re: በኢትዮጵያ እዴሳ ወይም ህዳሴ ዘመን …
ከሃያ ኣንድ ዐመታት በፊት ሰዉ የወጋገን ምስል እንድስልልኝ ጠይቄዉ ሳለልኝ።
ያኔ ለታየኝ ወጋገን በቅርቡ ኣጋጥሞኝ ያየሁት ቦምቤና የሚል የወላይትኛ የባህል ዘፈን ዉስጥ ያየሁኝ ብርሃን ለእኔ በቂ ነዉ። ወጋገንን ኣልሜ ብርሃን ኣሳየኝ ኣስብሎኛል። ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደዛ ብርሃን እንዲሆንም ኣስመኝቶኛል።
በዚህ ግዜ የዐቅሜን ያህል የማደርገዉ ጥረት በሚቀጥሉት ሃያ አምስት ዐመታት በአለም ደረጃ የተከበሩ እና ተሰሚነት የሚኖራቸዉ የኢትዮጵያ ሳይንቲስቶችን እንድናፈራ ነዉ። ወሬን እና ፍሬን ለይተዉ የምያዉቁ።
ሳይንስን እንዴት ማራመድ እንደሚቻል ኣዉቃለሁ። ዝንባሌዉ ላላቸዉ ቀላል መሆኑንም ኣዉቃለሁ። ከቀላሉ ሲጀመር።
ከብዙዎቹ ኣንድ ቀላል ምሳሌ ከኣሁን በፊት ደጋግሜ የጻፍኩኝ ነዉ።
ኩት (ኦሮምኛ)
ኩረት (ቁረጥ) ( አማርኛ)
ከት (እንግሊዘኛ)
እስከዚህ ዘመን ድረስ የተጻፈዉ የሰዉ ዘር ታሪክ በኣብዛኛዉ በመጀመርያዉ ሬይነሳንስ ቅርጽ የያዘ ነዉ። አዉሮፓ ዉስጥ ተጀምሮ አዉሮፓን መሠረቱ ኣድርጎ ቅርጽ የያዘዉን የተሟላ የሰዉ ዘር ታሪክ ኣስመሰለዉ።
የዚህ ዘመኑ ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የነበረዉን የሰዉ ዘር ታሪክ ከመሠረቱ መርምሮ የሚስተካከል የምያደርግ ነዉ።
ከቀላሉ ምሳሌ ብንነሳ ኣንድ ጥልቅ ጥያቄ ኩት የምለዉን ኩሽ ማለትን፣ ኩረት የሚለዉን ሴም ማለትን፣ ከት የሚለዉን ኣንግሎ ሳክሰን ማለትን እንዴት ማብራራት ይቻላል በማለት ሊጀምር ይችላል።
ይህ ቀላል ምሳሌ እና ጥልቅ ጥያቄ ለሳይሳዊ ጥናት ለቅምሻ ያህል ነዉ።

ብዙ ነገሮችን ኣስተዉዬ ኣሁን ሳስብ የሳይንስ ዝንባሌን ከልጅነት ዕድሜ ጀምሮ ማስተዋል የሚቻል ይመስለኛል።
ትምህርት ቤት ገብቼ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነበር ኣንድ በጣም ቀላል ጥያቄ በትክክል ስለመለስኩኝ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር የነበረዉ ለብቻዬ ና ብሎ ከጀማሪ ክፍል ወደሚከተለዉ ክፍል ያስተላለፈኝ።
በዕድሜም በአካልም ከእኔ የሚበልጥ የዘመድ ልጅ ጋ ተቀምጬ ነበረ። ዳይሬክተሩ ለብቻዬ ና ሲለኝ ማለፉ ደስ ቢለኝም ከዘመድ ልጅ አጠገብ መለየቱን ኣሰብኩኝ።
ያቺን ቀላል ጥያቄ በትክክል ያልመለሰ ሌላ ጀማሪ ክፍል ተማሪ ኣለመኖሩ እና የዳይሬክተሩ ያቺን ቀላል ጥያቄ በትክክል መመለስን እንደ ቁም ነገር ቆጥሮ ና ብሎ ወደሚከተለዉ ክፍል ማስተላለፉ ሁሌ ይገርመኛል።
ያ ዳይሬክተር ከሶስተኛ ክፍል መጨረሻ ወደ አምስተኛ ክፍል ኣስዘልሎኝ አምስተኛ ክፍልን ግማሽ ዓመት ከተማርኩ በኋላ ወደ ስድስተኛ ክፍል እለፍ እና የስድስተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዉሰድ ኣለኝ።
ጥያቄዉን ገና እንደሰማሁኝ ተገርሜ ኣይ ኣልኩት። አረተኛ ክፍል ኣለመማሬ እየከነከንኝ አምስተኛ ክፍልን ግማሽ ዓመት ተምሮ፣ ስድስተኛ ክፍልን ግማሽ ዓመት ተምሮ ብሔራዊ ፈተናን መዉሰድ ማስተዋል ኣልመሰለኝም።
እምቢ ማለቴ ወሬ ተሰምቶ አባቱ ለአዝመራዉ ሲል ወደ ከተማ እንዳይርቅ ከለከለዉ ተብሎ ተወራ። በልጅ ዉሳኔ አባት ተወቀሰ። ሰምቶ ቢሆን ምናልባት እሺ ይል ይሆን ነበር። ምክንያቱም የመጀመርያዉ ዓመት ማገባደጃ ቀን ተገኝቶ ስለነበረ እና የእኔ ዉጤት ከብዙዎቹ ስለበለጠ ዳይሬክተሩ ሙጫን ኩን እስን ቦደ ገሌ እስን ብረ ደብሬ ማለቱን ሰምቶ ብዙ ግዜ በደስታ ያስታዉስ ነበር። ትምህርት የጀመረዉ መስከረም ሲሆን እኔ የተቀላቀልኩኝ የየካቲት ልደታ ቀን ነበር።
ምናልባትም ወደ ስድስተኛ ክፍል መዝለልን እምቢ ባልል በሚቀጥለዉ ዓመት ብሔራዊ ፈተናን በሙሉ ፐርሰንታይል ባላለፍኩ ነበር። ባላገር አዝመራን እያገዙ ብሔራዊ ፈተናን ከተማ ከተመቻቸላቸዉ ጋር ተወዳድሮ በሙሉ ፐርሰንታይል ማለፍ በራስ መተማመንን ይጨምራል።
ይህ የኣንድ ግለሰብ ማስታወሻ የሳይንስ ዝንባሌን ከልጅነት ዕድሜ ጀምሮ ለማስተዋል ይጠቅም ይሆናል።