በእጅም በእግርም የሚጫዎቱት ቅሪተ-ወያኔዎች - አንድ ጊዜ ኤርትራዊ- ሻዕብያ ሌላ ጊዜ ኦሮምያዊ -ኦነግ። ትግራይ የትርዕይት ምድር - ኢትዮጵያዊ የሆንሽ ዕለት መቅበዝበዝሽ ይሰክናል - አረን
በእጅም በእግርም የሚጫዎቱት ቅሪተ-ወያኔዎች - አንድ ጊዜ ኤርትራዊ- ሻዕብያ ሌላ ጊዜ ኦሮምያዊ -ኦነግ። ትግራይ የትርዕይት ምድር - ኢትዮጵያዊ የሆንሽ ዕለት መቅበዝበዝሽ ይሰክናል - አረንጓዴ፤ብጫ፤ቀይ ያሸንፋል!
ሰሞነኛው ቅሪተ-ሞት ወያኔዎች ሻዕብያዊነት ግርሻት ትኩሳታቸው ጨምሮ እኛ ኤርትራ ክ/ሀገር ሰዎች ነን፤ ኤርትራ ክ/ሀገር ትገነጠል ዘንድ መስዋዕት ሁነን ደም ገብረናል፤ መቀሌ መሀል ከተማ የተቆለለው የድንጋይ ሃውልት(እርኩሳን ሃውልት) ታሪካችን ነው ይላሉ፤ ሌሎች ቅሪተ-ሞት ወያኔዎች ደግሞ በዛኛው ጉንጫቸው እኛ የኦሮምያ መንግስት ደጋፊ ነን ኦነግን የሳደግነው፤ ሌሎችን ቆርጠን ቆራርጠን ኦሮምኛ ተናጋሪ ሻዕብያ በምድረ-ኢትዮጵያ የፈጠርን ነን፡ ስለዚህ የዐባይ ትግራይ ህልማችን በኦሮምያ-ኦነግ እንደሚሳክ ግልጽ ነው - የአማራ ምድር እና ህዝብ ወልቃይት፤ራያ ወዘተ ይሰጠናል። ከሀገረ ኦሮምያ የሚጣላን ነገር ቢኖር ኦነግ ኢትዮጵያ እኔ አቃርጣለሁ (እየቦጨቅኩ ዋና ድርሻ እወስዳለሁ) ማለቱ እኛ ደግሞ ደደቢት ህገ-መንግስት ፈጣሪ ስለሆን እኛ ነን የሚል ነው - ከዚህ ግባ የማይባል ልዩነት ነው። ቁም ነገሩ ኢትዮጵያ የምትባለውን ባለ 3000 አመት ታሪክ በጋራ የማፍረስ ችሎታ ነው።
ምድረ-ትግራይ ውስጥ ለማንኛውም 2 የተለያዩ ቀለማት ያላቸው ማልያ (ዩኒፎርሞች ) በበቂ ሁኔታ መኖር አለባቸው - ቢቻል 3 ቢሆኑ ጥሩ ነው። 1ኛው መለዮ ሻዕብያ 2ኛው ) ኦሮምያ። ተጫዋቹን እያየን እንለብሳለን። 3ኛው መለዮ ሱዳናዊ መሆን ይኖርበታል። ብቻ የኢትዮጵያ መለዮ እንዳይኖር። የኢትዮጵያ መለዮ የለበሰ የማርያም ጥላት ነው - እርሱ ፋኖ ነው። እንደ ደደቢት ማኒፌስቶ አማራ ፋኖ የትግሬ ቋሚ ጥላት ነው። ይህ ነብር በሀገረ ኦሮምያ እንዳይታይ ብዙ የተሰረቁ ኦሮሙማዎች ይበላል፤ ትግራይ መቀሌ ዘልቆ ደደቢት በርሃ አስበርግጎ እንዳስገባ ሊረሳ አይገባውም - አብይ አህመድ ባይኖር አንድም ለወሬ ነጋሪ ባልተረፈን። ያላሉ እነ እሥስቶች ባለብዙ መለዮዎች -ሲፈልጉ ጆባይደን ይዘፍናሉ፤ ማይክ-ሀመር ውዳሴ ይዘበዝባሉ፤ ሲመቻቸው ሻዕብያ ሻዕብያ ይጫዎታሉ፤ ወይም ኦሮሙማ ኦሮሙማ ይፈክራሉ ( አሸንዳዬን በአጀንዳ ይቀይራሉ) - የትግራይ ምድር እግዜር መቸ ይጎበኛት ይሆን? ወይ ፋኖ ልኮ ያስጎበኛት ይሆን?