Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9545
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

አቦይ ስብሀት ነጋ ዝምታቸውን ሰበሩ፡፡

Post by MINILIK SALSAWI » Today, 08:48

አቦይ ስብሀት ነጋ ዝምታቸውን ሰበሩ፡፡ አንጋፋው የሕወሓት መስራች አቦይ ስብሀት ዘለግ ካለ ዝምታ በኋላ በአንድ የትግረኛ ሚዲያ ተከስተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአሜሪካ ድጋፍ ነው ስልጣን የያዙት በሚል ንግግራቸው የሚታወሱት አቦይ ስብሀት፤ ተክደናል፣ በደም የገነባናት ኢትዮጵያ ትመለስልን፣ መታጠቅ መደራጀት አለብን የሚሉ እና መሰል ሀሳቦችን ሲያንጸባርቁም ተደምጠዋል፡፡

የቀድሞው የህወሓት ሊቀመንበር እና መስራች አቶ ስብሀት ነጋ በደም የገነባናት ፌደራላዊት ኢትዮጵያ ትመለስልን በማለት በትግረኛ በሰጡት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል። አማራ ኦሮሞ እያሉ ህዝብን እንደጠላት ማየት የጠላትን ፍላጎት ማሳካት ነው ሲሉም ተደምጠዋል። ትግላችንም ይህ መሆን አለበት የሚሉት አዛውቱ ፖለቲከኛ፤ ከወረዳ አስመላሽ ኮሚቴነት እንውጣ ብለዋል። አቶ ስብሀት አማራ ኦሮሞ እያልን ህዝብን እንደ ጠላት ማየት ይብቃ የሚል ሀሳብ ሲያነሱ ቢደመጡም፤ እሳቸው የመሰረቱት ድርጅት ግን ለረጅም አመታት አንድን ህዝብ እንደ ጠላት ፈርጆ የሚንቀሳቀስ ነበር፡፡ አሁን ታድያ ያንን የድርጅታቸውን ሀጢያት ሳይናዘዙ ህዝብን እንደ ጠላት ማየት ይብቃ ማለታቸው ጥያቄ አስነስቶባቸዋል፡፡

የሆነው ሆኖ አዛውንቱ ፖለቲከኛ ስለ ወቅታዊው የሕወሓት ሽኩቻ ተክደናል ሲሉ ይናገራሉ፡፡ የአሁኑ እና የቀድሞው የሕወሓት ክፍፍል የተለያየ ነው የሚሉት አቶ ስብሀት፤ የበፊቱ ከክህደት ሳይሆን ከድክመት የሚመነጭ ነበር የአሁኑ ግን በክህደት የተፈፀመ ነው ሲሉ ያብራራሉ። በክህደት የወነጀሉት የትኛውን ወገን እንደሆነ በግልጽ ባያስቀምጡም ‹‹ያሁኖቹ ከጠላትም ጠላት የሆኑ ስዎች ናቸው›› በማለት በትግራይ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ የፈፀሙ ወታደሮችን እሰከመፍታት ደርሰዋል በማለት ወንጅለዋል።

ሕወሓትን ወደ ብልፅግና ለመቀየር የሚጥሩና የትግራይ ብሔር እንዳይኖር ደምሳሽ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሀይለች የፈጠሩት ነው ሲሉም ወቅታዊውን የህወሓት ቀውስ ገልፀውታል ። ፖለቲካችን በርዕዮተ አለም መመራት አለበት ያሉት አቶ ስብሃት ለዚህም ከ46አመታት በፊት በመጀመሪያው የህወሓት ድርጅት መስራች ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን አሁንም መልሶ ማየትና መተግበር ይጠቅማል በማለት ተናግረዋል፡፡ እነዚያ ዉሳኔዎችም ማንቃት ፣ ማደራጀት ፣ማስታጠቅ ፣ማሰማራት እና መገምገም ናቸዉ በማለት ዘርዝረዋቸዋል። አክለውም ከህዝብ መራቅ የለብንም መመካከር አለብን በማለት በትግረኛ በሰጡት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል፡፡

Abere
Senior Member
Posts: 12857
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አቦይ ስብሀት ነጋ ዝምታቸውን ሰበሩ፡፡

Post by Abere » Today, 09:43

ስብሃት ነጋ መቀሌ ለሚገኙ ወያኔዎች ከወረዳ አስመላሽነት እንውጣ ማለታቸው እንድሁም የጎሳ ሽኩቻ ይብቃ ማለተቻው በጎ ነገር ነው -ከሆዳቸውም ይህን ከአንገታቸው። የመጡበት ያለፉበት መንገድ ሁሉ እጅግ የተበላሸ መሆኑን ቢያንስ አምነዋል።

ችግሩ ግን ለምን ወያኔ የሚባል እንደ ድርጅት ከትግራይ መጥፋት አለበት አላሉም? ለምን የኢህ አደግ ዘመን ይመለስልኝ ይላሉ? ለምን ከነ አካቴው የጎሳ ፌደሬሽን ይፍረስ፤ የኢትዮጵያ ሉዋላዊት ግዛት ይመለስ አይሉም? ኢትዮጵያን የባህር በር እና የወሎ ጠቅላይ ግዛት የአውሳ አውራጃ አካል የሆነውን ዓሰብ ለኤርትራ አሳልፈው በመስጠታቸው አልተጸጸቱም -የኢትዮጵያ ነው አላሉም ?

የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ ለውጥ የሚያስፈልገው ህዝብ ነው። ወያኔ በመጀመሪያ የትግራይ ህዝብ ጥላት በመቀጠል የኢትዮጵያ ህዝብ ቋሚ ጠላት ነው። ይህ ድርጅት ወንጀለኛ ድርጅት ስለሆነ መፍረስ ነው ያለበት። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም እና ሉዋላዊነት የሚጓዳ ድርጅት ነው።

እነኝጅ ሶስት ወንጀለኛ ድርጅቶች (ወያኔ፤ሻዕብያ፤ኦነግ) የኢትዮጵያ ሶስት ጣምራ ጥላቶች ናቸው።

MINILIK SALSAWI wrote:
Today, 08:48

Post Reply