Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9546
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

አብይ አሕመድ ጊዜው ያለፈበት የተበላሸ ማዳበሪያ ለገበሬው እያከፋፈለ መሆኑን ታከለ ኡማ አጋለጠው

Post by MINILIK SALSAWI » 08 Feb 2025, 01:54

የኢትዮጵያ መንግስት ጊዜው ያለፈበትን expired የሆነ ማዳበሪያ ከግብፅ በማስገባት ለገበሬው እያከፋፈለ መሆኑ ተደርሶበታል።

ይህ ማዳበሪያ ሲከፋፈል የተጋለተለ ታከለ ኡማ የተባለው የአብይ አሕመድ ባለስልጣን በማሕበራዊ ድረ ገፁ ለጥፎት በነበረበት ጊዜ ሲሆን ወዲያው ልጥፉን ቢያጠፋውም ምስሉ አስቀርተነዋል።


ፎቶው ላይ እንደሚታየው የማዳበሪያው expire date 2022 ይላል በነጮቹ አቆጣጠር እኛ አሁን ያለነው 2025 ነው። expired ከሆነ ሶስት አመት አልፎታል ማለት ነው። የተበላሹ ምርቶችን ማከፋፈል ወንጀል መሆኑ እየታወቀ የአብይ አገዛዝ የተበላሹ ምርቶችን ለዜጎች በማከፋፈል ትውልድን እየገደለ ይገኛል።


ታከለ ኡማ ይህን ፎቶ የለጠፈው ማዳበሪያ ከውጭ እያስገባን ነው ብሎ በፃፈው ፖስት ላይ ነበር። ነገር ግን expire date 2022 የምትለዋን ልብ አላለም።


እናም የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበትን ማዳበሪያ ጥቅም ላይ ማዋል በጣም አደገኛ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ሲሆን ይህንንም ድርጊት መፈፀም በራሱ ወንጀል ነው። በጣም የሚያሳፍረው እና የሚያሳዝነው ህዝብን እናገለግላለን የሚሉ ሰዎች በህዝባቸው ላይ እንዲህ አይነት ግፍ ሲፈፅሙ ማየት በጣም ያማል።

ማዳበሪያ ለማምረት ጥቅም ላይ የሚውለው አደገኛ የሆነ uric acid ሲሆን ይህ ደግሞ exired ሲሆን የሚኖር ጉዳት እጅግ ከባድ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።