Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 34733
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ችግር ፈጠራን ትወልዳለች ፤ ቀውስ እድልን!

Post by Horus » 07 Feb 2025, 16:06

ትራምፕና ኢሎን መስክ የቆሰቆሱት ሽብር እዚም እዛም አቧራ እያስነሳ ነው! የሚባሉት ነገሮች የምር የሚሆኑ ከሆነ ብዙ ያሳዩናል!

የኢትዮጵያ መንግስት በኣባይ ግድብ ነጻ አስተዳደር ላይ ያለውን ጽናት ወይም ለትራፕና ሲሲ ግፊት መምበርከኩን የምናይበት ይሆናል!

የአቢይ አህመድ ኦሮሙማ ቡድን ምን ያክል ከአሜሪካ ተራድኦና አለም ባንክ ተጽኖ ላይ እንደ ቆሙ የምንለካበት ግዜ ላይ ነን

ያሜሪካ ፍጹም ተላላኪዋ ግብጽም የጋዛ ፍልስጤሞች ነቅላ በግብጽ በረሃ ታሰፍር እንደ ሆነና አለያም ለትራምፕ የማንበረከክ እንደ ሆነ የምናይበት ይሆናል!

ማንዴላ ከአፓርታይድ ያላቀቃት ደቡብ አፍሪካ እንደ ገና በአፍሪካነሩ ኢሎን መስክ ወደ ቀድሞ አፓርታይ ለመመልስ የተነሳውን ድራማ አፍሪካዊያን እንዴት እንደ ሚመክቱት ይታያል! 7% የሚሆኑት ነጮች 73% የሚሆነው መሬት ባለቤት ናቸው!

ፑንትላን ከወዲሁ የጋዛ ፍልስጤሞችን ለመቀበል በመስማማቷ የሱማሌን ፖለቲካ አምሳዋለች!

ሱማሌላድ የአሜሪካን እውቅና ለማግኘት ተመሳሳይ ታደርግ ይሆን?

ቁም ነገሩ ትራምፕ የሱማሌን ዘይት ፈልጎ ስለሚሆን ይህ ሁሉ ከቱርክና ኢሚሬት ጋር የተሸረበ ሊሆን ይችላል!

በዚህ ሁሉ የሱማሌ ዝምታ ምን ማለት ነው?

የኢትዮጵያ ወደብና ባህር ኃይል ጉዳይስ?

ቀውስ ሁልግዜ የተደበቁ እድሎችን ይዞ ይመጣልና ብዙ እናያለን!