የኤርትራውያኖች ዋጋ ለምን ረከሰ ?
በሊቢያ የታገቱ 266 ስደተኞች ተለቀቁ
#Ethiopia | በሊቢያ ውስጥ በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ታግተው የነበሩ ሁለት መቶ ስልሳ ሶስት ስደተኞች መለቀቃቸው ተገለፀ፡፡ የሊቢያ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የተለቀቁት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሱማሊያ ዜግነት ያላቸው መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
ቢሮው በመግለጫው ባደረገው ዘመቻ እነዚህን ስደተኞች ለማስለቀቅ መቻሉን አስረድቶ በወቅቱ አብዛኛዎቹ በድብደባና ሌሎችም ስቃዮች ሰውነታቸው ተዳክሞ እንደነበር አስረድቷል፡፡ ሁሉም በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች እጅ የነበሩ መሆናቸውንና ለመልቀቅ ለቤተሰቦቻቸው የገንዘብ ጥያቄ ቀርቦ እንደነበርም ገልጿል፡፡
እንደምሳሌም ለሱማሊያዊያኑ ስደተኞች አጋቾቹ አስራ ሰባት ሺህ ዶላር ሲጠይቁ እንደነበርና ለኤርትራዊያኑ ደግሞ አስር ሺ ዶላር እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ጠቅሷል፡፡
እነዚህ ስደተኞች በሚለቀቁበት ወቅት ሁለት ህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችም አብረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢሮው መግለፁን ሊቢያ ሪቪው ዛሬ ዘግቧል፡፡
Source: https://www.facebook.com/getu26