Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Odie
Member
Posts: 2922
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

"ሳይህ ሳይህ መለስ ዜናዊ መስልከኝ"!

Post by Odie » 06 Feb 2025, 05:36

ሳይህ ሳይህ የተጭበረበረ መፅሃፍ ቅዱስ የተቀባ መለስ ዜናዊ መስልከኝ! :lol: :lol:

መለስ ዜናዊ ለባንድራና ለኢትዮዽያዊነት flat affect ቢኖረውም አገርን ደፍሮ አልበተነም:: ቢሆንም ሁለቱም ወራዶች ናቸው ( በመለስ ዜናዊ በራሱ ቋንቋ ተውስን):: ይሄኛው እንደውም በራሱ መንገድ የባስ ተወዳዳሪ የሌለው ያልሆነውን ለመሆን የሚደክም እንደ ይሁዳ ከፊት ስሞ ከጀርባ የሚሽጥ ገዳይ ነው!

ወላጁ የገዛውን አዲስ ደብተር ላይ ዝም ብሎ ሳይገባው የሚሞነጭርና የሚያበላሽ ወይም out right ደብተሩን የሚተረትር ህፃን ነው የሚመስለው:: ካላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ለቅላቂ ነገር! ወርቅና ኮትሮባንድ ነጋዴ የደም ጀነራሎችን ተተግኖ አገር ላይ የሚጫወት ዘረኛ ፋሽስት:: ጥቁሩ ሙሶሎኒ!! ሙሶሎኒ ጥሩ ልጅ አገኘ!! ምንሊክን ከርሱ በላይ የሚጠላ:: ነገስታቱን የሚጠላ:: ቀብተን ቀባብተን ሙዚየም አረግናቸው ከእይታ እናነሳቸዋለን ነው ያለው? ህም! ቢያየው ቢያየው ህዝቡ ይዘምርለታል ምን ያርግ እርሱ? እየተበላ በዘር ተከትፎ ማልቀስ እንኳን ያቃተው ህዝብ:: ለትግራይ የተላከው "የፍቅር" ደብዳቤውስ ነገር አጃኢብ አይደል? ፍቅርሽ ቢያነደኝ አንዴ በጠብ መንጃ ደግሞም በ valentine የተፃፈ የፍቅር ደብዳቤ!!

አገር ሞታለች ማለት ይሄም አይደል? ጅቡቲ በድሮን ኬንያ በባታሊዮን ሱዳን በዘራፊዎች በአካፋ ሲዝቁን ማን ይምጣ? የቀረችው ግብፅ አይደለች? እርሷም ከስሞኑ ያቅሟን አንድ ብልት ትወስዳለች ተብሎ ይጠበቃል!

አይ ጎንደሬው አዝማሪ! ያንተ ነገር ነው የሚገርመኝ:: አማች ነኝ ኩርማን ህዝቀ ስላሴ ፕሬዝዳንት ነው ፋሲላደስን ነጭ ቀለም ለቀለቁት ኮሪደር መጣ ብለህ መስንቆ የምትከረክረው ነገርስ? ጥሩ ማደንዘዣ ተወግተሃልና አንኮራፋ!

ክፉ ገልባጭ/plagarist ስምህንም ጭምር ይገለብጥና አገር በቀል ሃሳብ ነው ይላል አሉ!

ስውየው መንግስቱንም መለስ ዜናዊንም የኦሌፉ ጃራንም ኢየሱስንም....ገልብጠው ቁጭ:: እንግዲህ እስኪወርድ ወይም እስኪፈርድ ክፍል ሁለት ድራማውን ለመኮምኮም ተከምረናል!!

ማነህ! አለቃቀስክ ላልከው ሆዳም ካድሬ!
ስላንተ ድንቁርናና ውንብድና እንጂ እኔ ስለአገሬ አላለቃቅስም!
ተው ጥራኝ ዱሩ የሚሉ ጀግኖች ልጆች አሏትና!

ቀጀላ! አሁንስ ተስማምቶሃል?


https://m.youtube.com/shorts/e5_cnjb1JZY