Djibouti drone strike kills at least 8 near Ethiopian border
By Mohamed Olad Hassan
Monday February 3, 2025
File photo of Djiboutian forces.
Djibouti's security forces executed a drone strike near the Ethiopian border, killing eight members of what it calls a terrorist group and harming an unspecified number of civilians, officials said on Sunday.
"A drone attack was carried out against a terrorist group at Addorta, a Djiboutian locality some six kilometers from the border with Ethiopia," a statement from the Djibouti defense ministry said.
The statement said that the defense ministry confirmed that "eight terrorists were neutralized," but also noted that "collateral damage was unfortunately reported among Djiboutian civilians," without providing further details.
In comments to AFP, Alexis Mohamed, an adviser to President Ismael Omar Guelleh, identified the militants as members of the Armed Front for the Restoration of Unity and Democracy, or FRUDA, which Djibouti classifies as a terrorist organization.
The government said the group was involved in "hostile actions" that posed "a potential threat to our advanced posts."
An Ethiopian newspaper, the Addis Standard, reported that the drone strike occurred on Ethiopian territory — an assertion Djibouti rejected. Mohamed maintained that the attack took place within Djibouti's borders.
Djibouti security officials did not respond to requests from VOA Somali to provide further details regarding the incident.
In October 2022, an attack on barracks at Garabtisan, in the north of Djibouti, resulted in the deaths of seven soldiers and the kidnapping of six others.
Officials in Djibouti blamed the attack on FRUD, the political arm of FRUDA. The abducted soldiers were released several weeks later.
In 1991, FRUD, which originated in the Afar community in northern Djibouti, launched an anti-government insurgency, claiming to represent Afar interests against the Issas, the other major ethnic group in the tiny Horn of Africa country.
Later, the group broke up, joining a four-party coalition that backs President Guelleh, but its armed wing, called FRUDA, has continued to carry out attacks against government forces.
Several countries, including the United States and China, have military installations in Djibouti. The country sits on the west side of the Bab El Mandeb Strait, in East Africa. along one of the world's busiest maritime routes where the Red Sea meets the Gulf of Aden.
Djibouti’s news comes two days after U.S. aircraft took aim at the Islamic State affiliate in neighboring Somalia, hitting what officials described as high-ranking operatives in the terror group's mountainous stronghold.
Ramadan Jama contributed to this report.
-
- Member
- Posts: 4279
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: Djibouti drone strike kills at least 8 near Ethiopian border
Afar people are the big majority in the tiny Djibouti. However, they have been marginalized and murdered mercilessly for the last several decades. To make matters worse, the OPDO government allowed Djibouti to bomb the Afars in their own country, Ethiopia. The regime in Addis Ababa is a threat to all Ethiopians and the HOA region at large.
-
- Member
- Posts: 4279
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: Djibouti drone strike kills at least 8 near Ethiopian border
Reports confirm Djibouti drone attack killed in Afar, Ethiopia
esidents in the Afar region of Ethiopia confirm that a Drone attack that the Djibouti government carried out has killed eight civilians including a child.
Six others have been injured. Borkena reported, on saturday, about it a few days ago and the number of those wounded was indicated to be only three. Those wounded are hospitalized in Dubti.
BBC Amharic reported on Monday that it has confirmed the story from residents in the region.
The incident occurred in Zone 1 of the region, Elidar district, Siaro kebele, last Thursday in the evening.
According to residents who spoke to the source, the drone attack was carried out twice. In the first round, three civilians were killed on Thursday evening. Another drone attack targeted civilians who were gathered on Friday morning to bury the three people who were killed in the first attack. Five were killed.
One of those killed is a woman, one is a child and the remaining six are men. And from those in hospital four are female and two are children, according to the source.
The Djibouti government has released a statement confirming the drone attack. But it said it was carried out within its territory targeting rebel groups which it calls “terrorists.”
The source cited AFP , which cited the Djibouti Defense Force, as saying that the attack was carried out about six kilometers from the Djibouti-Ethiopia border in the Adorta area.
It is said Djibouti government statement admitted the death of civilian Djiboutians without specifying the numbers,
The Ethiopian government or the Afar regional government have not yet remarked about the incident.
https://borkena.com/2025/02/03/ethiopia ... t-in-afar/

Nonsense Somalis are the absolute majority 80 percent of Djibouti population is Somali . Afar is a small minority we give them positions if we take that away there is nothing they can do the frud rebels were destroyedZa-Ilmaknun wrote: ↑04 Feb 2025, 11:46Afar people are the big majority in the tiny Djibouti. However, they have been marginalized and murdered mercilessly for the last several decades. To make matters worse, the OPDO government allowed Djibouti to bomb the Afars in their own country, Ethiopia. The regime in Addis Ababa is a threat to all Ethiopians and the HOA region at large.
Dr Zackovich
-
- Member
- Posts: 4279
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: Djibouti drone strike kills at least 8 near Ethiopian border
ከሰሞኑ የጂቡቲ መንግሥት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበር ጥሶ በንፁኃን ዜጎች ላይ የፈጸመው የድሮን ጥቃት በዝምታ ሊታለፍ እንደማይገባ፣ በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳሰቡ፡፡
የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባርና የአፋር ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ የጂቡቲ መንግሥት ከሰሞኑ በአፋር ንፁኃን አርብቶ አደሮች ላይ የፈጸመውን ጥቃት የኢትዮጵያ መንግሥት በዝምታ ማለፉን ተቃውመዋል፡፡
‹‹በሰላማዊ አርብቶና ለፍቶ አደሮች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በጭራሽ ይቅር የምንለው አይሆንም፤›› ያሉት ፓርቲዎቹ፣ ‹‹ጥቃቱን በእጥፍ እንበቀላለን›› በማለት በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡
ወንጀሉ የተፈጸመው በአፋር ክልል መንግሥትና አርብቶ አደሮች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ተደፍሯል ሲሉ አክለዋል፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ታስከብር አታስከብር የምናውቀው ነገር ባይኖርም፣ የአፋር ክልል የዜጎቹን መገደልና የግዛቲቱን መደፈር ቸል ሊል አይገባም፤›› ብለው፣ ክልሉ በዝምታ ያልፋል ብለው እንደማያምኑ አክለዋል፡፡
የጂቡቲ መንግሥት የኢትዮጵያን ግዛት አልፎ ዜጎችን ሲገድል ይህ የመጀመሪያው አይደለም በማለት በመግለጫቸው ያሠፈሩት ፓርቲዎቹ፣ ባለፈው ዓመት እብኖ በተባለ አካባቢ የጂቡቲ መደበኛ ሠራዊት ገብቶ ንፁኃን ዜጎችን መጨፍጨፉ የሚረሳ አይደለም ተብሏል፡፡
ባለፈው ዓመት የተፈጸመውን ጥቃት ዓይኔን ግንባር ያድርገው ብሎ የካደ መንግሥት የሰሞኑን የድሮን ጥቃትም ለመካድ መሞከሩ አይቀርም ያሉት ፓርቲዎቹ፣ ይህ ግን በድሮን የተፈጸመ ጭፍጨፋ በመሆኑ ሊካድ የሚችል አይደለም፡፡ የጂቡቲ መንግሥት ከሰሞኑ በድንበር አካባቢ የፈጸመውን ጥቃት ወደ ሌሎች የክልሉ ቀበሌዎች ስላለመድገሙ ምንም ዋስትና እንደሌላቸው፣ የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ መሐመድ አወላ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
ጥቃቱ በዝምታ ከታለፈ ነገ አሳይታና ዱፍቲም ሊመጣ ይችላል ያሉት አቶ መሐመድ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥቃቱን በፅኑ ሊቃወም እንደሚገባና ለተጎዱ ዜጎችም ካሳ መቀበል አለበት ሲሉ ገልጸዋል፡፡
‹‹የአፋር ሕዝብ የድንበር ተሻጋሪዎችን ወረራ ድሮም ይመክት እንደነበረው አሁንም ዝም አይልም፤›› ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ፣ ይህንን የግፍ ወረራ መንግሥትም ግብረ መልስ ሊሰጠው ይገባል ብሎ ፓርቲያቸው እንደሚያምን አስረድተዋል፡፡
ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም. በአፋር ክልል አውሲ ሩሲ ዞን ኤሊዳአር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ በጂቡቲ ድንበር አቅራቢያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የስምንት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ አሥር ያህል ሰዎች መቁሰላቸውን የክልሉ ፖሊስ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
የጂቡቲ መንግሥት መከላከያ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የድሮን ጥቃቱን መፈጸሙን ያመነ ሲሆን፣ ነገር ግን ጥቃቱን የፈጸመው በጂቡቲ ግዛት ውስጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ማክሰኞ ምሽት ማተሚያ ቤት እስክንገባ ድረስ በፌዴራል መንግሥት በኩል የተባለ ነገር የለም፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/138044/

የጂቡቲ ጥቃትና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጥያቄ
February 5, 2025
ዓርብ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. የጂቡቲ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቆ ገብቶ በአፋር ክልል ጥቃት አደረስ የሚለው ዜና ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ነው የሰነበተው፡፡
የጂቡቲ ጥቃትና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጥያቄ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የጂቡቲ መንግሥት ጥቃቱን ያደረሰው በድሮን መሆኑ መነገሩ፣ እንዲሁም በጥቃቱ በርካታ ሰላማዊ ዜጎች ተጎዱ መባሉ ጉዳዩ የበለጠ ትኩረት እንዲስብ አድርጎ ነበር፡፡ ዓርብ ዕለት ጂቡቲ በኢትዮጵያ ድንበር ጥቃት አደረሰች የሚለው ወሬ የተጎዱ ሰዎችን ከሚያሳዩና ለማየት ከሚያሰቅቁ ፎቶግራፎች ጋር ተያይዞ፣ በማኅበራዊ ገጾችና በተለያዩ የዜና አውታሮች መሠራጨቱ ትልቅ ትኩረት ቢስብም ነገር ግን ጥቃቱ ከዚያን ቀን ቀደም ብሎ ሐሙስ መካሄዱን ዘግይተው የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን በሁለት ወራት ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው የተባለው ጥቃት ነፍሰ ጡርና ሕፃናትን ጨምሮ በትንሹ ለስምንት ሰዎች ሕልፈት ምክንያት መሆኑ ተነግሯል፡፡
የተለያዩ ፖለቲከኞችን ጨምሮ የአፋር ተወላጅ ማኅበራዊ አንቂዎችና ሌሎችም፣ ይህን የጥቃት ዜና አባሪ በማድረግ ኢትዮጵያ ድንበሯም ሆነ የአየር ክልሏ ተጥሶ ዜጎቿ በጎረቤት አገር መንግሥት የሚገደሉባት ሉዓላዊነቷን መጠበቅ ያቃታት አገር እየሆነች ነው የሚል መረጃ በሰፊው ማጋራት ቀጠሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ የአፋር ክልል መንግሥትና ሌሎችም የሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ኦፊሴላዊ መረጃ ስለጉዳዩ ሳይሰጡ ቆይተዋል፡፡
ይሁን እንጂ የጂቡቲ መንግሥት የመከላከያ ሚኒስቴር ቅዳሜ ጥር 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው ኦፊሴላዊ መግለጫ ለጥቃቱ ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡ የጂቡቲው መግለጫ ጥቃቱ አዶርታ በተባለና በጂቡቲ ሉዓላዊ ግዛት ሥር በሚገኝ መንደር መፈጸሙን ጠቁሟል፡፡ ቦታው ከኢትዮጵያ ድንበር ስድስት ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ መሆኑን በመጥቀስ ለሳምንት ቅኝት በማድረግ፣ በአሸባሪ ድርጅት አባላት ላይ ክትትል በማድረግ፣ ዒላማ የሆኑ አሸባሪዎችን በጥንቃቄ በመለየት የተፈጸመ ነው ሲልም አስታውቋል፡፡ በአጠቃላይ ስምንት አሸባሪዎችን መግደሉንና ጥቃቱ የተፈጸመበት ቦታም የአሸባሪ ቡድኑ አባላት ሰላማዊ ሰዎችን ለማገት፣ መሠረተ ልማትን ለማውደም፣ እንዲሁም የአሳሌ ሐይቅና የታጁራ ወደብ የንግድ ኮሪደርን ለማወክ ማዕከል አድርገው የሚጠቀሙበት ቦታ እንደሆነ ገልጾ ነበር፡፡ በጥቃቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ አላስፈላጊና ያልታሰበ ጉዳት መድረሱን ያመነው የጂቡቲ መከላከያ መግለጫ፣ የጉዳቱን መጠን ለማወቅ ምርመራ መደረግ መጀመሩንና ከዚህ ጎን ለጎንም ለተጎጂዎች ሰብዓዊ ዕርዳታም መላኩን አመልክቶ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ሪፖርተር ያናገራቸው የአፋር ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የጂቡቲ መንግሥትን መግለጫ ፈጽሞ ሐሰት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ የአፋር ሕዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ መሐመድ ዳውድ ድርጅታቸው ከሌላኛው ከአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር ጋር ሆኖ በጉዳዩ ላይ የጋራ መግለጫ ማውጣቱን ገልጸዋል፡፡ የጥቃቱን ምንነትና የደረሰውን ሁኔታ መረጃ ሲያሰባስቡ መሰንበታቸውን፣ ከጥቃቱ ቆስለው የተረፉና በዱፍቲ ሆስፒታል በሕክምና የሚገኙ ሰዎችን በማነጋገር ጭምር መረጃ መሰብሰብ መቻላቸውን ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ በመነሳት ጥቃቱ የደረሰው በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ መሆኑን ማረጋገጣቸውንና የጂቡቲ መንግሥት መግለጫ ሐሰት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
‹‹ጥቃቱ የተፈጸመው በአፋር ክልል ዞን አንድ ውስጥ በሚገኘው ኤልዳር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ቦታ ለጂቡቲ ቅርብ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ ነው ያለው፡፡ የጂቡቲ መንግሥት በየጊዜው ድንበር ጥሶ ገብቶ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ጥቃት ማድረሱ እየተለመደ የመጣ ድርጊት ሆኗል፡፡ በቅርብ ወራት በተመሳሳይ አፋምቦ ወረዳ ገብቶ በዲሽቃና በሞርታር ጥቃት አድርሷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ዝምታ ቢመርጥም ነገር ግን ይህን መሰል ጥቃት በአፋር በኩል ከጂቡቲ መንግሥት በተደጋጋሚ ጊዜ እየተቃጣ ይገኛል፡፡ ጉዳዩ የፖለቲካ ጨዋታ ያለው ይመስላል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ድንበሩን መጠበቅ ሲገባው የውጭ መንግሥት የፀጥታ ኃይል ድንበሩን አልፎ ጥቃት መፈጸሙ በእኛ አመለካከት ተቀባይነት የለውም፡፡ የጂቡቲ መንግሥት ለምንድነው በግዛቴ ውስጥ ነው ጥቃት ያደረስኩት እያለ ተራ ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ ዝም የሚባለው? የአፋር ክልል መንግሥትም ቢሆን ይህንን ነገር ማጋለጥ አለበት፤›› በማለት ነው የተናገሩት፡፡
አቶ መሐመድ ሁለቱ ፓርቲዎች በጋራ መግለጫው ይህን በተመለከተ ግልጽ አቋም መያዛቸውንና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲከበር መጠየቃቸውን አስረድተዋል፡፡ የጂቡቲ መንግሥት በተለምዶ ፍሩድ (Front for the Restoration of Unity and Democracy/FRUD) የሚባለውን ትጥቅ አንግቦ የሚንቀሳቀሰውን የአፋር ተወላጆች የፖለቲካ ቡድንን ለመውጋትና ምሽጎቹን ለመደምሰስ በሚል ዘመቻ እንደሚያደርግ መናገሩን በመጥቀስ፣ የአሁኑ ጥቃትም የዚሁ አካል ስለመሆኑ የተጠየቁት አቶ መሐመድ ጉዳዩ እንደዚያ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
‹‹አፋር ክልል ውስጥ የተባለው ቡድን በፍፁም አይንቀሳቀስም፡፡ አሁን ጥቃት በፈጸሙበት አካባቢ የተባለው ቡድን በፍፁም የለም፡፡ እነሱ ያሉት ኤርትራ ግዛት ውስጥ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ የአፋር ክልል መንግሥት ቡድኑን እንደሚደግፉት አንዳችም ማረጋገጫ የለም፡፡ ቡድኑ ይልቁንም የኤርትራ አፋሮች ወገን ነው፡፡ እኛ የምናውቀው የኤርትራ መንግሥት እንደሚደግፋቸው ነው፡፡ በኤርትራና በጂቡቲ መካከል እስከ ዛሬም ያልተፈታ የድንበር ይገባኛል ውዝግብ አለ፡፡ በዚያ አካባቢ ነው የቡድኑ እንቅስቃሴ ያለው፡፡ የጂቡቲ መንግሥት ይህን አሳቦ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃት መፈጸሙ ሆን ተብሎ የተደረገና ሰላማዊውን የአፋርን ሕዝብ ለማሸበር ነው፡፡ ነገሩ ዝም መባሉ ደግሞ የሕዝቡን ቁጣ ሊቀሰቅስ የሚችል ችግር ይሆናል ብለን እንገምታለን፤›› ብለዋል፡፡
የጂቡቲ ፓርላማ በትጥቅ የሚታገለውን የፍሩድ ቡድን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2022 ነበር በሽብርተኝነት የፈረጀው፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ ቡድኑ ከጥቂት ቀናት በፊት በአንድ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ጥቃት ከፍቶ ሰባት ወታደሮችን ገድሎ አራት ደግሞ ማቁሰሉን፣ እንዲሁም ስድስት ወታደሮች የገቡበት አለመታወቁን ተከትሎ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት የጂቡቲ ፓርላማ በሰጠው ድምፅ በከፍተኛ ድጋፍ የፍሩድ ቡድንን አሸባሪ ኃይል ነው ሲል ፈርጆታል፡፡ በጂቡቲ መቀመጫውን ያደረገው ቀጣናዊው ድርጅት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ማኅበር (ኢጋድ) ጥቃቱን ወዲያው አውግዞት የነበረ ሲሆን፣ በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያም በተናጠል የቡድኑን ጥቃት ማውገዟ ይፋ ተደርጎ ነበር፡፡
ትንሽቱ አገር ጂቡቲ የቀጠናው ኃያል አገር ስትባል የኖረችውን ኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት ጥሳና የአየር ክልልም አልፋ በኢትዮጵያውያን ላይ ጉዳት ስታደርስ ለምን ዝም ተባለ የሚለው ቁጭት ከአፋር የተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል ብቻ ሳይሆን፣ ከብዙ አቅጣጫዎች ሲንፀባረቅ ነው የሰነበተው፡፡ ከሁለት ወራት ቀደም ብሎ የጂቡቲ መንግሥት በተመሳሳይ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ጥቃት አደረሰ ከመባሉ እንዲሁም ከዚያ ቀደም ይሰሙ ከነበሩ ተመሳሳይ ክሶች ጋር ተዳምሮ ጉዳዩ የተጋጋለ ሙግት ሲደረግበት ነው የሰነበተው፡፡ ጂቡቲ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ተደጋጋሚ ጥሰት የፈጸመችው የኢትዮጵያን ውስጣዊ አለመረጋጋት ተገን አድርጋ ነው የሚለው መላምት ደግሞ ብዙዎችን ሲያስቆጭ ነው የሰነበተው፡፡
ኢትዮጵያ ከጂቡቲ ጋር ድንበር ከመዋሰን ባለፈ ከ90 በመቶ በላይ የወጪና የገቢ ንግዷን የምታካሂድበት ወደብም ናት፡፡ ሁለቱ አገሮች አንድ አገር ሆነው የኖሩበት ዘመን እንደነበር ታሪክ ቢያስረዳም፣ ተነጣጥለው ሁለት ሉዓላዊ አገር ከሆኑ ወዲህም ቢሆን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊና ሁለንተናዊ ግንኙነታቸው ሳይነጣጠል የዘለቀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያና ጂቡቲ ከወደብ አገልግሎት በተጨማሪ በሕዝቦቻቸው ማንነትና ቋንቋ የተሳሰሩም ናቸው፡፡ ጂቡቲ ውስጥ አፋርና ሶማሌዎች በዋናነት እንደሚኖሩት ሁሉ፣ በኢትዮጵያም ሁለቱ ሕዝቦች በሰፊው የሚኖሩ ማኅበረሰቦች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ ተዛምዶ በሁለቱ አገሮች መካከል የመኖሩን ያህል እንደ ሰሞኑ የድሮን ጥቃት ሁሉ የሁለቱን አገሮች የሚፈታተኑ ችግሮች መከሰታቸው ተደጋግሞ ይጠቀሳል፡፡ አንዳንዶች የዚህን መነሻና ምንጭ ሲናገሩ ጂቡቲ ቀን ጠብቃ ጎረቤት ኢትዮጵያን የሚጎዳ እንቅስቃሴ ስታደርግ የቆየች መሆኗን ያስረዳሉ፡፡
የምሥራቅ አፍሪካ ተመራማሪውና የዲፕሎማሲ ታሪክ አጥኚው በለጠ በላቸው፣ ‹‹ኢትዮጵያና ጎረቤቶቿ የትብብርና የውዝግብ ታሪክ›› በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ስለጂቡቲ በርካታ ሐሳቦችን አስፍረዋል፡፡ ‹‹ከተቀሩት የጎረቤት አገሮች ጋር ሲነፃፀር ኢትዮጵያ ለጂቡቲ የምትሰጠው ቦታ በእጅጉ ይለያል፡፡ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት የግለሰቦችና የፓርቲ ግንኙነት መደረጉ ይበቃ ይሆናል፡፡ ከሱዳንና ከሶማሊያ ጋር ለሚኖራት ግንኙነት ደግሞ ከተወሰኑ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር የሚፈጠሩ ተግባቦቶች በቂ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ከጂቡቲ ጋር ግን ከግለሰብና ከቡድን ባለፈ የአገር ለአገር (የመንግሥት ለመንግሥት) ግንኙነት ከማድረግ የተለየ አማራጭ የለም፡፡ ከኤርትራ፣ ከሱዳንና ከሶማሊያ ጋር ያለው ግንኙነት ቢበላሽ የኢትዮጵያ ህልውና ከመቀጠል አይስተጓጎልም፡፡ አንዳንዴም በተሻለ መንገድ የሚመራበት ዕድል ጭምር ተከስቷል፡፡ ጂቡቲን በተመለከተ ግን የተሻለ አማራጭ የለም፡፡ ይልቁንም ጂቡቲ ኢትዮጵያ ከምትፈልጋት በላይ ኢትዮጵያ ጂቡቲን ትፈልጋለች፡፡ በተለይም አሁናዊ ነባራዊ ሁኔታ ሲታይም ኢትዮጵያ በጂቡቲ ላይ ያላት ጥገኝነት በማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል፤›› በማለት ጽፈዋል፡፡
በለጠ (ዶ/ር) እንደሚተርኩት ኢትዮጵያ በውስጥ ፖለቲካዋ መዳከሟ ወይም መጠናከሯ ከጂቡቲ ጋር ያላትን ግንኙነት ደረጃ ሲወስን ቆይቷል፡፡ ‹‹በተለይ የኢትዮጵያ መንግሥታት በአንፃራዊ መልኩ ሲዳከሙ ከጂቡቲ ወገን የሚመጡ ጫናዎች ሲበረክቱና የሚከፈሉ መስዋዕትነቶችም ሲጨምሩ በተደጋጋሚ ተስተውሏል፡፡ ኢትዮጵያ ጠንካራ መንግሥታዊና አገራዊ ቁመና ስታበጅ የትብብርና የወዳጅነት አዝማሚያው ከጂቡቲ ወገን ሲጨምር ነው የታየው፤›› በማለት ተመራማሪው አክለዋል፡፡
ያም ቢሆን ግን ኢትዮጵያን መዳከሟን እያየ ሊጎዳት የማይፈልግ የጎረቤት አገር ጥቂት መሆኑን ብዙዎች ያወሳሉ፡፡ ለምሳሌ የትግራይ ጦርነት በፈነዳበት ወቅት ሱዳን ቀን ጠብቃና አጋጣሚውን ተገን አድርጋ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት አድርሳለች የሚለውን ሐሳብ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጭምር በቅርብ ዓመታት ተናግረውታል፡፡ ሱዳኖች የትግራይ ጦርነትን መቀስቀስ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ድንበር መግባታቸውንና አወዛጋቢውን የአልፋሽቃ መሬት መያዛቸውን ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ ይህን ሲያደርጉ ደግሞ በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃት መክፈታቸውን፣ ያሸተ ሰብልና ብዙ ንብረት መዝረፋቸውን ይጠቅሱታል፡፡
የትግራይ ጦርነት መቀስቀስ ለኤርትራም የቆየ ቂም መወጫና በቀል መፈጸሚያ አጋጣሚ ፈጥሮላታል የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ የኤርትራ መንግሥት ኃይሎች ድንበር አልፈው በትግራይ ጦርነት የተካፈሉት በሕወሓት አስገዳጅ ጠብ አጫሪነትና ጦርነቱን ቀጣናዊ የማድረግ ፍላጎት የተነሳ መሆኑን ብዙዎች ይከራከራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩን ከዚህ በተቃራኒ የሚያዩት ወገኖች ኤርትራ አጋጣሚውን ተጠቅማ በሕወሓት ላይ ያሳደረችውን የቆየ ቂም ለመወጣት፣ አለፍ ሲልም በትግራይ ሕዝብ ላይ ወረራና ዘረፋ ለመፈጸም አውላዋለች የሚለል ጠንካራ መከራከሪያ ሲያቀርቡ ይደመጣል፡፡
ከደቡብ ሱዳን የተነሱ ታጣቂዎችም ቢሆን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብዙ ኪሎ ሜትሮች ዘልቀው ገብተው የወርቅ ዘረፋና ወረራ ያደረጉት፣ የኢትዮጵያን መዳከም አስልተው ነው የሚል ሐሳብ የሚያነሱ አሉ፡፡ ሶማሊያም ብትሆን የኢትዮጵያን አለመረጋጋት በማየት ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለማድረስና የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይልን አልፈልግም ብላለች የሚሉም አሉ፡፡ ኢትዮጵያ ደከም ባለችባቸው የታሪክ አጋጣሚዎች ሁሉ እንደ ኬንያ ካሉ ጎረቤቶቿ በስተቀር ዙሪያዋን የከበቡ ብዙ አገሮች መንግሥታት ሊያጠቋትና ጫና ሊያደርጉባት ሞክረዋል የሚሉት እነዚህ ወገኖች፣ የጂቡቲም ሰሞነኛ ዕርምጃ ከዚህ የተለየ አለመሆኑን ነው የሚያክሉት፡፡
የጂቡቲ የአገርነት አፈጣጠር ታሪክ እንደሚጠቁመው ከሆነ እ.ኤ.አ. በ1977 ነበር ራሷን የቻለች ነፃ አገር ለመሆን የበቃችው፡፡ በወቅቱ ዋና ዋና ጎሳዎች በሆኑት አፋርና ኢሳ ማኅበረሰቦች መካከል የፖለቲካ ሥልጣን ይገባኛል ፉክክር ከፍተኛ እንደነበርም ይነገራል፡፡ ያም ሆኖ የአፋር ማኅበረሰብን እወክላለሁ የሚለው ፍሩድ የተባለው ኃይል እ.ኤ.አ. በ1994 የሰላምና የብሔራዊ ዕርቅ ስምምነት ከመንግሥት ጋር በመፈራረሙ የጂቡቲ ችግር ይፈታል የሚል እምነት አሳድሮ መቆየቱ ይጠቀሳል፡፡ ይሁን እንጂ ቃል የተገባው የሥልጣን ክፍፍል ባለመተግበሩና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በጂቡቲ ባለመፈጠሩ ቡድኑ ከመንግሥት ጋር ዳግም ወደ ግጭት እንዲገባ እንዳደረገው ይነገራል፡፡ ሥልጣን በአንድ ጎሳ በተለይም በኢሳ ማኅበረሰብ የበላይነት ወደቀ የሚል ሙግት የሚያነሳው የአፋሩ ቡድን በሒደት በትጥቅ ወደ መታገል መግባቱም ይገለጻል፡፡
ጂቡቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ ይህን ቡድን እያሳበበች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ጥሳ ገብታ ጥቃት ትፈጽማለች የሚለው ክስ ጎልቶ ቢደመጥም፣ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ለዚህ በቅጡ ምላሽና ማብራሪያ ሲሰጥ እስካሁን አልታየም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ዝምታን የመረጠው ደግሞ ጂቡቲ ለኢትዮጵያ ያላትን ቁልፍ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ላለማጣት ሲል እንደሆነ ይነገራል፡፡
ይሁን እንጂ ጂቡቲ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ የምትገባውና ሉዓላዊነት ስትጥስ የምትታየው ሌላም ድብቅ አጀንዳ የጂቡቲ መንግሥት ስላለው እንደሆነ የአፋር ሕዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲው ሊቀመንበር አቶ መሐመድ ይናገራሉ፡፡ ‹‹የጂቡቲ መንግሥት ከሶማሊያ መንግሥታት ጋር አብሮ የታላቋ ሶማሊያ አጀንዳን ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ በአፋርና በሶማሌ ክልሎች መካከል የወሰን ይገባኛል ውዝግብ መነሳት ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ሆን ብሎ ጣልቃ በመግባት፣ ከሶማሌ ክልል ኃይሎች ጋር ወግኖ በአፋር ክልል ላይ ጥቃት ማድረስ መቀጠሉ ይታወቃል፡፡ የጂቡቲ መንግሥት በኢትዮጵያ የውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ መግባቱና በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ ጥቃት ማድረሱ ሁሉ መላው ኢትዮጵያን የሚፈታተን ችግር ነው፤›› ይላሉ፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ዝም መባል የለበትም የሚሉት ፖለቲከኛው፣ ጂቡቲ በዚህ ከቀጠለች የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ችግር በአፋር ክልልም ሆነ በሌሎች አጎራባች ክልሎች ውስጥ ሊፈጠር እንደሚችል ነው ሥጋታቸውን ያስረዱት፡፡
ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የባህር በር አጀንዳን ለፓርላማ አባላት ይፋ ሲያደርጉ በታሪክ፣ በጂኦግራፊ፣ በኢኮኖሚና በዘር ባሏቸው መነሻ ምክንያቶች ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት እንደሚገባት ተናግረው ነበር፡፡ ‹‹አፋሮች ጂቡቲም አሉ፣ ኤርትራም አሉ፡፡ እስከ ዛሬ ዓመት ድረስ አፋሮች ሡልጣን ሲመርጡ የጂቡቲና የኤርትራ አፋሮች መጥተው በውክልና አሳይታ ነው ሡልጣናቸውን የሚመርጡት፡፡ ሆኖም ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚሆኑ አፋሮች በቀጭኑ ተሰምሮ ከቀይ ባህር ጋር እንዳይገናኙ ተደርጓል፤›› ማለታቸው አይዘነጋም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጀንዳ አርገው ያነሱት የባህር በር ጉዳይ በሒደት ደግሞ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ጎልቶ እንዲነሳ ተደረገ፡፡ ይህ ደግሞ ከሶማሊያ በኩል ጠንካራ ምላሽ የፈጠረ ሲሆን፣ ሶማሊያ ኤርትራና ግብፅን ጭምር አሰባስባ በኢትዮጵያ ላይ ከባድ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ስታደርግ ቆይታለች፡፡ በዚህ ወቅት ጂቡቲ ገላጋይ መስላ ስትቀርብ፣ ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን በመጠቀም ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት እንድትተውና ከሶማሊያ ጋር መግባባት እንድትፈጥር የጂቡቲ ባለሥልጣናት ሐሳብ ሲሰጡ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ጂቡቲ ከአስታራቂነት ይልቅ ከሶማሊያ ጎን የመቆም አዝማሚያ ይታይባታል ያሉ አንዳንድ ወገኖች፣ ታጁራ ወደብን ለኢትዮጵያ ተጠቀሚ ብትልም የባህር ኃይል በወደቡ ማስፈር እንዳትችል መከልከሏን አንድ ምክንያት አድርገው ሲያቀርቡት ቆይተዋል፡፡ ጂቡቲ ከዚህ በተጨማሪም ከቻይና እስከ አሜሪካና ፈረንሣይ በድምሩ ወደ አሥር ለሚጠጉ አገሮች የባህር ኃይል የጦር ሠፈር የፈቀደች ሲሆን፣ ለጎረቤቷ ኢትዮጵያ ግን ተመሳሳይ ፈቃድ ለመስጠት ማመንታቷ አገሪቱ ለኢትዮጵያ ተአማኒ ጎረቤት እንዳልሆነች ማሳያ ነው ሲሉም ተከራክረዋል፡፡ ይህ ሁሉ ከሰሞኑ ጂቡቲ እየፈጸመችው ነው ከተባለው ጣልቃ ገብነትና የሉዓላዊነት ጥሰት ጋር ተዳምሮ፣ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ወዴት ይወስደዋል የሚለው ጉዳይ የሚጠበቅ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/138098/